“ለኢትዮጵያ ሲባል መኖር የለብንም፣ ኢትዮጵያ ነች ለኛ ስትል መኖር ያለባት” የትግራይ ምሁር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም

Print Friendly, PDF & Email

የትግራይ የፓለቲካ ሳይንስ ምሁርና ተንታኝ አቶ ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ከአውራምባ ታይምስ ዊብሳት ባለቤት ከሆነው ከዳዊት ከበደ ጋር ባደረገው አጠር ያለ ቃለ መጠየቅ ትግርይ ለኢትዮጵያ ብላ እየተጎዳችና እየቶሳቆለች ነው። በመሆኑን አንቀጽ 39ኝ ተጠቅመን የራሳችን አገር መመስረት ይኖረብናል ይላል።

አቶ ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም በትግርኛ ከሰጠው ቃለ መጠየቅ ውስጥ የሚከተለው ይገኝበታል።

“ለኢትዮጵያ ሲባል መኖር የለብንም፣ ኢትዮጵያ ነች ለኛ ስትል መኖር ያለባት። መጀመርያ ራሳችንን በየትኛውም መንገድ ከጥቃት መከላከል ኣለብን። እስከ ኣሁን ድረስ የሰራንበትን ኢትዮጵያዊነት ሌሎቹ ኣንፈልገውም ካሉ እኛ ብቻችን ኣንድነት ልንገነባ ኣንችልም። እየተጠቃን፣ እየተገደልን ለኢትዮጵያ ስንል ታገስን መባል የለበትም። እኛ ነን ኢትዮጵያ እኛ ከሌለን ኢትዮጵያ የለችም። በጥላቻ ከተመረዙ ሊያጠፉን ጎራዴ ከመዘዙ ጠላቶች ጋር ኣብረን የመኖር ግዴታም የለብንም። “ኣንቀጽ 39″ የተቀመጠው ለዚህ ነው። ኣብሮነት የሚያገዳድለን ከሆነ መለያየት ኣማራጭ መሆን ኣለበት። ኣንዱ ከሌላው በታች ሌላው ከኣንዱ በላይ ስለ ኢትዮጵያዊነት ሊጨነቅ ኣይገባም።”

የአቶ ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ሙሉ ቃለ መጠየቁን ከዚህ በታች ያዳምጡ። ( ቃለ መጠየቁ በትግርኛ ቋንቋ ነው )