የተጀመረው ሕዝባዊ እንቢተኝነት እንቅስቃሴ ለግብ እንዲበቃ የድርሻችንን እንወጣ! – ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

Print Friendly, PDF & Email

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ሰኞ ታሕሳስ ፳፬ ቀን ፪ሺህ ፱ ዓ.ም. ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፴፫

የተጀመረው ሕዝባዊ እንቢተኝነት እንቅስቃሴ ለግብ እንዲበቃ የድርሻችንን እንወጣ! (To read the PDF , click here )

የትግሬ-ነፃ አውጭ ግንባር (ወያኔ) የዐማራውን ሕዝብ በጠላትነት ፈርጆ ላለፉት 42 ዓመታት የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል የፈጸመበትና አሁንም እየፈጸመበት እንዳለ በግልጽ ይታወቃል። በመሆኑም በነዚህ ዓመታት ከአምስት ሚሊዮን በላይ ዐማሮችን ከምድረ-ገጽ እንዳጠፋ የተለያዩ መረጃዎች ያስረዳሉ። በርካታ ቁጥር ያለው በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ ፣ በምሥራቅና በመሀል አገር ይኖሩ የነበሩትን ዐማሮች፣ ሀብት ንበረታቸውን ነጥቆ በማፈናቀል ለከፍተኛ ችግር የዳረጋቸው እንደሆነ ዓለም በዝምታ እየተመለከተው ያለ የዘመናችን፣ በሰዎች ላይ የተፈጸመ አሳዛኝና ዘግናኝ ወንጀል እንደሆነ በአሰቦት፣ በበደኖ፣ በአርባ ጉጉ፣ በወተር፣ በመቻሬ፣ በጉራ ፈርዳ፣ በምሥራቅ ወለጋ፣ በመተከል፣ በቤንቺ ማጅ፣ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በጠለምት ፣በራያና ቆቦ ወዘተ የተፈጸሙት የዐማራ ዕልቂቶች አፍ አውጥተው እየተናገሩ ነው።

ከሁሉም በላይ፣ ወያኔ የትግራይና የጎንደር የተፈጥሮ ወሰን የሆነውን ተካዜን ተሻግሮ፣ ለምና ድንግል መሬቶች የሆኑትን የወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ሰቲት ወረዳዎችን ወደ ትግራይ አካሎ፣ ሕዝቡን በኢኮኖሚ የደቀቀ፣ በፖለቲካው የተገለለ፣ በማኅበራዊ ሕይዎቱ ተዋራጅና ተሸማቃቂ የሆነ ማድረጉ አልበቃ ብሎት፣ ዐማራዊ ማንነቱን አውልቆ እንዲጥል በመገደዱ፣ ማንነቱን ለማስጠበቅ ሠላማዊና ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ጀምሮ እንደነበር አይዘነጋም። ሕዝቡ ያቀረበውን ሰላማዊና ሕጋዊ ጥያቄ ለሌሎች ማለትም፣ ለስልጢዎች፣ ለቅማንቶች፣ ለአገዎች(አዊ) እና በወሎ ውስጥ እንደሚኖሩት ኦሮሞዎች ወዘተ ከመስጠት ይልቅ፣ ጥያቄው ከዐማራው ወገን በመቅረቡ ብቻ፣ ለዐማራማ ይህን ዓይነቱን ዕድል አንሰጥም በሚል የጠላትነት ስሜት ተነሳስቶ፣ የሕዝቡ ወኪሎች የሆኑትን የወልቃይት ጠገዴ የማንነት አስተባባሪ ኮሚቴዎች በመግደሉና በማፈኑ ሰላማዊ እንቅስቃሴው ወደ ኃይል እንዲሸጋገር ማድረጉ ይታወቃል።

ወያኔ የወልቃይት ጠገዴን የማንነት ሕዝባዊና ሰላማዊ እንቅስቃሴ በኃይል ለመጨፍለቅ ባለው ዓላማ መሠረትም፣ በዐማራ ሕዝብ ላይ የአስቸኳይ አዋጅ አውጆ፣ መጠነ ሠፊ የሆነ ዕልቂትና ግፍ እየፈጸመበት ይገኛል። በዚህ ዐማራን ፈጽሞ የማጥፋት ወታደራዊ አዋጅ እስካሁን ከሰላሳ ሺ በላይ የዐማራ ወጣቶች ታፍነው የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችለው የሥቃይ ዓይነቶችን እየፈጸመባቸው ይገኛል። በጎንደርና በጎጃም የተለያዩ አካባቢዎች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወጣቶች የሰው በላው የአጋዚ ሠራዊት ሰለባዎች ሆነዋል። ይህ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ወያኔ የሚያደርሰው ግድያ፣ እስራትና ድብደባ፣ «ነገም የእኛ ዕጣነው» ያሉ የዐማራ ወጣቶችን ዱር ቤቴ እንዲሉ አስገድዷቸዋል። በዚህም መሠረት በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋ እና በወሎ በአገራቸው በሰላም ወጥተው መግባት የተነፈጋቸው የዐማራ ወጣቶች የዐማራውን የተጋድሎ እንቅስቃሴ እየተቀላቀሉት ይገኛሉ።

የዐማራውን ኅልውና አስጠብቆ፣ የዘረኛውን የወያኔን አገዛዝ በማስወደግ፣ አንድነቷ የጠነከረ፣ ሰላሟ የተሟላ፣ ዕድገቷ የተፋጠነ ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ፣ የተጀመረው የዐማራ ተጋድሎ እንቅስቃሴ በሁለንተናዊ መልኩ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት እንደሆነ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ያምናል። ለዚህም ለታሠሩ፣ ለተፈናቀሉ፣ ለተገደሉና በወያኔ እየተሳደዱ ላሉ የዐማራው ልጆች የሚያስፈልጋቸውን እገዛና ድጋፍ በውጭ የሚኖረው ዐማራና የዐማራው ወዳጅ የሆነ ሁሉ፣ በቀና መንፈስ ወገንን ከጥፋት የመታደግ ጥረት የበኩሉን እርብርብ ሊያደርግ ይገባል። ዛሬ በወያኔ ለተጎዱ ወገኖ የምንሰጠው ድጋፍ ሕዝባዊ እንቢተኝነቱን በቆራጥነት ለተያያዙት ወገኖች የሞራል ስንቅ በመሆን የሚያገልግል ከመሆኑም በላይ፣ ትግሉን ለድል እንዲበቃ ጋንን በጠጠር የመደገፍ ያህል ነውና፣ የዐማራው ልጅ፣ የሚችለውን ሁሉ እንዲያደርግ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በአክብሮት ጥሪ ያቀርባል። ዐማራው ለወገኖቹ የሚሰነዝረው የድጋፍ እጁ ከሚፈለገው ቦታ እንዲደርስ ለማድረግ ሞረሽ ወገኔ የበኩሉን ዝግጅት ያደረገ በመሆኑ፣ ተጎጂ ወገኖቻችን ለመርዳት ፍላጎቱ ያላችሁ ወገኖች በየምትኖሩበት አካባቢ ላሉ የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት መሠረታዊ ማኅበራት፣ ወይም በባንክ፣ በእንሂድ እንደግፍ (https://www.gofundme.com/leamarategadlo-humanitarian-support) ወይም በቼክ፣ በፔይ ፓል (http://www.moreshwegenie.org/) መርዳት የሚቻልበትን መንገዶች አመቻችቷል።

ዛሬ ለወገናችን ማድረግ የምንችለውን ነገር ሳናደርግ ቀርተን፣ እንቅስቃሴው ቢገታ ፀፀቱ የእኛ ብቻ ሳይሆን፣ በልጆቻችን ተወቃሽ የሚያደርገን ስለሚሆን፣ የምንችለውን ያህል እጃችን ለወገናችን እንድንዘረጋ ግፍ በሚፈጸምባቸው ወገኖቻችን ስም ጥሪአችን እናቀርባለን!

የተጀመረው ሕዝባዊ እንቢተኝነት እንቅስቃሴ ለግብ እንዲበቃ የድርሻችንን እንወጣ! ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ሰኞ ታሕሳስ ፳፬ ቀን ፪ሺህ ፱ ዓ.ም. ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፴፫ ከላይ ለተዘረዘሩት የሚከተሉትም አድራሻዎች ትጠቀሙ ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን፦

(1) በባንክ ለመላክ

Moresh Wegenie Amara Organization
Bank of America
Account Number: 435030804511
Routnig Number: 051000017 (paper and electronic)

or

026009593 (wires)
Swift Number: BOFAUS3N

(2) በGoFundMe ለመላክ

Go fund me link: https://www.gofundme.com/leamarategadlo-humanitarian-support

Or,

በቼክ፣ በፔይ ፓል (http://www.moreshwegenie.org/) መርዳት የሚቻልበትን መንገዶች አመቻችቷል።
ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ የዐማራ ሕልውና ጥያቄ ነው!
ዐማራው ሕልውናውን በትግሉ ያስከብራል!