አክራሪ ብሄረተኛነትና የሚፈጥረው ከማንኛውም ነገር በላይ ለራስ ነገድ ጭፍን ታማኝነትን የማሳየት ዝንባሌ (በዶ/ር አሰፋ ነጋሽ)

Print Friendly, PDF & Email

አክራሪ ብሄረተኛነትና የሚፈጥረው ከማንኛውም ነገር በላይ ለራስ ነገድ ጭፍን ታማኝነትን የማሳየት ዝንባሌ

በዶክተር አሰፋ ነጋሽ —› የኢሜይል አድራሻ –› Debesso@gmail.com

Amsterdam (the Netherlands) – ሀምሌ 7 ቀን 2010 ዓ. ም.

ክፍል ሁለት —-› ከክፍል አንድ የቀጠለ

ብሄረተኛነትና የሚፈጥረው የራስ ነገድ አምልኮ፤ በሁሉም ነገር የእኔ ነገድ ብቻ ይቅደም!!!!!

ብሄረተኛነት ከማንም በላይ የራስን ነገድ ተወላጅ ማስቀደምን፤ የራስን ነገድ ከሌላው ሁሉ አብልጦ መውደድን፤ ለራስ ነገድ ማድላትን፤ የራስን ነገድ ማፍቀርን፤ በራስ ነገድ ማንነት ካለ ልክ መኩራራትንና ከራስ ነገድ ውጭ ያሉ ነገዶችን ማንነት ማናናቅን፤ መጥላትን ያስተምራል። በብሄረተኛነት መንፈስ የሚነዱ ሰዎች ከምንም ነገር በላይ ታማኝነታቸውን የሚያሳዩት ለዚያ የእኔ ነገድ ለሚሉት ወገን ነው እንጂ ለእውነት ወይም ለፍትህ ጉዳዮች አይደለም። ብሄረተኛነት ለራሱ ነገድ ጥቅም ታማኝና ሙት መሆንን ተከታዮቹ ለሆኑ የአንድ ነገድ ተወላጆች ያስተምራል። አንድ በብሄረተኛነት ስሜት የተለከፈ ወገን በማናቸውም ጉዳዮች ወገናዊነቱን የሚያሳየው ለዚያ የእኔ ነገድ ለሚለው ህዝብ ነው። አክራሪ ብሄረተኛነት የአንድ ነገድ ተወላጆች የሆኑ ሰዎች ከእነሱ ነገድ ውጭ ባሉ የሌሎች ነገዶች ተወላጆች ላይ የሚያደርሱትን በደል እንደ በደል እንዳያዩ ያደርጋቸዋል። አክራሪ ብሄረተኛነት ፍርደ-ገምድልነትን፤ ከራስ ነገድ ውጭ ላለ ሰው አለመራራትን፤ ከራስ ነገድ ውጭ ያለን ሰው እንደ ሰው ፍጡር አለማየትን ያስተምራል። አክራሪ ብሄረተኛነት የግለሰቦችን ማንነትና ህልውና በሚሸረሽር፤ የግለሰቦችን ህሊና በሚፍቅና በሚያጠፋ ፍልስፍና ላይ የተመሰረተ ስለሆነ አብዛኞቹ በዚህ የአክራሪ ብሄረተኛነት ስሜት ህሊናቸው የታወረ የአንድ ነገድ ተወላጆች የአንድ ዓይነት የአክራሪ ብሄረተኛ የፓለቲካ አስተሳሰብና እምነት ተሸካሚዎች ይሆናሉ። በዚህም ምክንያት በርካታ የአንድ ነገድ ተወላጆች የሆኑ የአንድ አክራሪ ብሄረተኛ ድርጅት ተከታዮች እንደ አንድ ሰው ማሰብ፤ እንደ አንድ ሰው ባንድ ዓላማ ስር መሰለፍ ይጀምራሉ።

በዛሬዋ ኢትዮጵያ ፈላጭ ቆራጭ የሆነው የወያኔ መንግስት ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት በኢትዮጵያ ታሪክ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት በደል በህዝብ ላይ የፈጸመ ቢሆንም አብዛኛዎቹ የዚህ መንግስት ደጋፊዎች የሆኑት የአንድ ነገድ ተወላጆች የዚህን መንግስት አጥፊነት፤ ሀገር አፍራሽነት፤ በሃይማኖትና በነገድ ከፋፋይነት፤ ዘራፊነት፤ ደም-አፍሳሽነት፤ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለባዕዳን አሳልፎ ሰጪነት፤ ጠብ-አጫሪነት፤ ተንኳሽነት ወዘተ ተረድተውና አይተው ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሆነው በተቃውሞ አልቆሙም። እንዲያውም ባብዛኛው የአንድ ነገድ ተወላጆች የሆኑት የዚህ መንግስት ደጋፊዎች ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በተጻራሪነት በመቆም ከማንም በላይ የባለመብትነት ስሜት (strong sense of entitlement) ሲሰማቸው አይተናል፤ ታዝበናል። የወያኔ ትግሬዎች በስፋት ተሰራጭተውና ህይወታቸውን መስርተው በሚኖሩባት ኢትዮጵያ ውስጥ በውዴታም ይሁን የወያኔ መንግስት በሚያደርስባቸው ተፅዕኖ ምክንያት የዚህ መንግስት ዓይንና ጆሮ በመሆን ከስርዓቱ ጋር እጅና ጓንት ሆነው ቆይተዋል። የወያኔ ትግሬዎች የሚለው አገላለጽ የወያኔ ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች የሆኑትን እንጂ ሁሉንም የትግራይ ተወላጆች የሚመለከት አይደለም። ይህ ሁኔታ ወያኔ ትግሬዎችን ገና ከጠዋቱ ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በጥርጣሬ ዓይን እንዲተያዩ አድርጓቸዋል። ዛሬ በአክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት ስሜት የተለከፉ በርካታ የወያኔ ትግሬዎች፤ ከፓትርያርክ እሰክ ተራ ምዕመናን፤ ከፕሮፌሰር እስክ መሃይሙ፤ ከሃብታሙ እስከ ድሃው፤ ከሼኩ እስከ ተራው ሙስሊም ወዘተ ድረስ የሚገኙበት ሁኔታ ይህ ነው። አብዛኞቹ የወያኔ ትግሬዎች ከወያኔ ስርዓት ጀርባ በመቆም ለስርዓቱ ያላቸውን ድጋፍ በጭፍነነት ሲገልጹ የምናያቸው በዚህ ምክንያት ነው። ሌላው ቀርቶ ይህችን ዓለም ንቀው ዋልድባን የሚያኽል እጅግ ታላቅ የሆነና የተከበረ የመናኞች ገዳም ውስጥ የገቡ አንዳንድ የትግራይ መነኮሳት ጭምር በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብለው የወያኔ መንግስት የዋልድባ ገዳም ታሪካዊ ይዞታ የሆነውን ሰፊ መሬት ወደ ትግራይ ክልል ከልሎ ይህንን የገዳሙን መሬት ለሸንኮራ አገዳ ማብቀያ (አዲስ ለተቋቋመው የስኳር ፋብሪካ) የሰጠበትን ህገ-ወጥ ድርጊት በአደባባይ ሲደግፉ ታይተዋል። አክራሪ ብሄረተኝነት እንኳን የምድርን ደስታ የሚመኘውን የዚህ ዓለም ሰው ቀርቶ ይህቺን ዓለም እንኳን ንቆና እንደ ሞተ ሰው ተቆጥሮ በቁሙ ፍታት ተደርጎለት፤ ተዝካር ወጥቶለት ዋልድባ ገዳም የገባውን የትግራይ መነኩሴ ጭምር ህሊና-ቢስና ይሉኝታ-ቢስ አድርጓል።  …… (Read more)

**************** ********************* ********************
ክፍል አንድ —-› አክራሪ ብሄረተኛነት ምንድነው? ተከታዮቹ በሆኑት የአንድ ነገድ ተወላጆችስ ላይ የሚያስከትለው ስነልቦናዊ ለውጥ ምን ይመስላል?
ክፍል ሁለት —-› አክራሪ ብሄረተኛነትና የሚፈጥረው ከማንኛውም ነገር በላይ ለራስ ነገድ ጭፍን ታማኝነትን የማሳየት ዝንባሌ
ክፍል ሶስት —-› አክራሪ ብሄረተኛነት የሚፈጥረው የራስን-ነገድ ብቻ እጅግ አብልጦ የመውደድ ስነልቦና ምን ይመስላል?
ክፍል አራት —-› አክራሪ ብሄረተኛነት በሰዎች ላይ የሚያስከትለው ስነልቦናዊ ለውጥና የሚፈጥረው ተፅዕኖ – በፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ ጽሁፍ አማካይነት የአክራሪ ብሄረተኛነትን ተፅዕኖ አሳያለሁኝ።

**************** ********************* ********************