የ”ሕዝበ-ውሳኔው” ውጤት – ቅማንት አማራነቱን በድምጹ አስረግጧል!

Print Friendly, PDF & Email

በሁሉም ድምጽ በተሰጠባቸው ቀበሌዎች ዛሬ ጠዋት ውጤቱ ይፋ ተደርጓል። በዚሁ መሠረት 7ቱ ቀበሌዎች በነበረው ይቀጥላሉ፤ በጭልጋ ወረዳ ያለችው ኳቤር ሎምየ በቅማንት ልዩ ወረዳ ሥር እንድትሆን ተወስኗል። ወያኔዎች ልዩ ትኩረት ሰጥተውባቸው የነበሩት የቋራና የመተማ የሱዳን አዋሳኝ ቦታዎች ጎምዥተው ነው የቀሩት።
በ12 የሰሜን ምእራብ ጎንደር ቀበሌዎች እንዲካሄድ የተወሰነው የ “አማራ ወይንም ቅማንት” ህዝበ ውሳኔ በሕዝብ እንቢተኝነት በ4ቱ ቀበሌዎች ሊካሄድ ባለመቻሉ በስምንት ቀበሌዎች ብቻ በመደረጉ የሚታወስ ነው።

ከህዝብ ፍላጎት ውጭ በህወሃት/ብአዴን ፋላጎት ብቻ አማራ እና ቅማንት ተብለው እንዲወስኑ ሪፈረንደም እንዲደረግባቸው ከተባሉት 12 ቀበሌዎች ውስጥ የ4 ቀቤዎች ነዋሪዎች የህወሃት/ብአዴን ሴራ አቀድመው በመገንዘባቸው እኛ አማራ – ቅማንት እያላችሁ አትከፋፍሉን። ሪፍረንደም የሚባል ነገር አንፈልግም፣ እኛ ሁላችንም ለዘመናት ተወልዳን እና ተጋብተን ጎንሬዎች ነን በማለታቸው ምክንያት ሪፈርንደም የሚባል ነገር አልተደረገባቸው።

ትላንት እሁድ ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ በ 8 ቀበሌዎች ሲካሄድ የዋለው “የሕዝበ ውሳኔ” ምርጫ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት የተጠናቀቀ ሲሆን ለዚህ “ሕዝበ ውሳኔ” ዜጎች በነቂስ ወጥተው ድምጻቸውን ሰጥተዋል። ውቴቱ በትላንት ምሽት የታወቀ ቢሆንም የምርጫ ቦርዱ በይደር አሳልፎታል።

የህወሃት መንግስት በጎንደር አማራ እና ቅማንት በማለት ለዘመናት አብሮ የኖረውን ሕዝብ ለመከፋፈል ያቀደው ሴራ በሕዝብ ድምጽ ይክሸፍ እንጂ በህወሃት የተፈጠረው እና ለህወሃት የሚያገለግለው የምርጫ ቦርድ እንደተለመደው ውጤቱን ይገለብጠው ይሆናል ተብሎ ተሰግቷል።

የቅማንት ሕዝብ ያለፍላጎቱ ይህንን “ሕዝበ ዉሳኔ” እንዲሰጥ መደረጉ በራሱ፣ በህወሃት እና በብአዴን ባለስልጣናት የተዶለተ “የራስ አስተዳደር” ሴራ እንደሆነ ታዛቢዎች ይናገራሉ። ሕዝብ የዘረኞቹን ሴራ በድምጹ አክሽፎ በማንነቱ ላይ ወስኗል። ኮሮጆ የመገልበጥ አባዜ ያለው የምርጫ ቦርድ የሕዝቡን ድምጽ እንደገና ሊሰርቅ ቢሞክር አካባቢው ለከፍተኛ ብጥብጥ እንደሚዳረግ ሕዝቡ እየገለጸ ነው።

በዚህ ምርጫ የተሸነፈው የትግሬ ተስፋፊ ኃይል ነው። ያሸነፈው ደግሞ ሁሉም የዐማራ ሕዝብ ወይም ሁሉም የቅማንት ሕዝብ ነው።

ቅማንት ዐማራ ቤተሰባዊነት ለዘላለም ጸንቶ ይኖራ!!

ህዝበ ውሳኔ መረጃ 1

በመተማ ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች በተደረጉ ምርጫዎች

# ሽንፋ ቀበሌ – ድምፅ የሰጠው ጠቅላላ ህዝብ ብዛት 3465

– ለነባሩ አሰተዳደር ድምጽ የሰጡ 2444 (70.43%)
– ለቅማንት አስተዳደር ድምፅ የሰጡ 794 (22.5%)
– ዋጋ አልባ የሆነ 227 (6.5%)

2. አኩሻ ራቀበሌ – ድምፅ የሰጠው ጠቅላላ ህዝብ ብዛት 2163
– ለነባሩ አሰተዳደር ድምጽ የሰጡ 1968 (91%)
– ለቅማንት አስተዳደር ድምፅ የሰጡ 92 (4.2%)
– ዋጋ አልባ የሆነ ድምፅ 103 /6.5%)

4. ቱመት ቀበሌ – ድምፅ የሰጠ 3144
– ለነባሩ አሰተዳደር ድምጽ የሰጡ 2488 (79.4%)
– ለቅማንት አስተዳደር ድምፅ የሰጡ 446 (14.2%)
– ዋጋ አልባ የሆነ ድምፅ 210 (6.7%)

5. ጭልጋ ወረዳ – ነጋዴ ባህር ቀበሌ ወደ ነባሩ አስተዳደር ሲወስን – ኳቤር ሎምየ ቀበሌ ድግሞ ለአዲሱ የቅማንት አስተዳደር ድምፁን ሰጥቷል፡፡

6. በጎንደር – ከተማ በሶስቱም ምርጫ ጣቢያ ጠቅላላ የተመዘገ በ3074
– ለነባሩ አሰተዳደር ድምጽ የሰጡ 1798 ( 58.5% )
– ለቅማንት አስተዳደር ድምፅ የሰጡ 852 (27.7% )
– ዋጋ አልባ የሆነ ድምፅ 254 (8.3% )