በጎንደር በሪፈንደሙ ለመሳተፍ ትግሬዎች “ቅማንት” ነን እያሉ የምርጫ ካርድ ለመውሰድ ሲሞክሩ እየተያዙ ነው

Print Friendly, PDF & Email

(Esayas Tamiru)

በሽንፋ ቀበሌ 28 ትግሬዎች ቅማንት ነን ብለው ምርጫ ካርድ ሲወስዱ ተየዙ
ሽንፋ በአጠቃላይ 5 ቀጠናዎች ያሏት ስትሆን ቀጠና 01 በተደረገው ምዝገባ የተገኘው የህዝብ ብዛት

ቀጠና 1 አማራ 2246፣ ቅማንት 8 ሰዎች ሲሆኑ
ቀጠና 02 አማራ 1865፣ ቀማንት 12 ነው።

በሌሎች ቀጠናዎችም ቁጥሩ የዚህ ተመሣይ ሥለሆነባቸው ከአሁን በፊት የቅማንት ነው ምርጫ አይደረግበትም ከተባለው ጉባይ ጀጀቢት ቀበሌ ወደሽንፋ አሥገብተው ካርድ ለማስወጣት ሢሞከር በአማራ ተአዛቢዎች 147 ተይዘው ተመልሰዋል።

ምርጫ ቦርድ ትግሬዎችም መምረጥ ይችላሉ ስለተባሉ በአምናው ግጭት መሽኛ ይዘው የሄዱ ትግሬዎች አሁን ለምርጫው ብቻ መጥተው 28 ሰዎች የተያዙ ሢሆኑ አሁን ከዛው የሚኖሩት መሽኛ ሳይዙ የሄዱት ትግሬዎች ይመጡ እየተባለ ነው። ምርጫውም እሁድ ይካሄዳል።

(ከዚህ በታች ያለውን ደግሞ የዘገበው Miky Amhara ነው)

ሪፈረንደም ይደረግባቸዋል ከተባሉ 8 ቀበሌዎች ውስጥ በጥቂቶቹ ለማመን አስቸጋሪ በሆነ መንገድ ከሌላ ቦታ የመጡ ሰዎች ተመዝግበው ተገኙ።

ለማጣራት በተደረገው ሂደት ለምርጫ የተመዘገበውን ያህል ቁጥር ቀርቶ 1/10ኛውን እንኳን ቅማንት የማይኖርባቸው አካባቢዎች ከየት እንደመጡና በምን መልኩ እንደተመዘገቡ ያልታወቁ ቁጥሮችና ስሞች ተገኝተዋል።

ለምሳሌ ባለፈው 6 ቅማንት ብቻ ተመዝግቦ በተገኘበት የጎንደር ከተማው ብላጅግ ቀበሌ ማጣራት ሲደረግ ከየት እንደመጡ ያልታወቁ ከ500 በላይ ቅማንቶች ተመዝግበው ተገኝተዋል።

ይህ ጉዳይ ትልቅ ጭቅጭቅ የፈጠረ ሲሆን ከምርጫ አስፈፃሚዎች አካባቢ በተሰራ ካርድን ነዋሪ ላልሆነ ሰው በቅማንት ኮሚቴዎች በኩል ተሰጥቶ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ተደርሷል ተብሏል።

እንደዚህም ሁኖ ከ2 ሺህ በላይ አማራ በመመዝገቡ የምርውጫን ውጤት ይቀይረዋል ባይባልም ድርጊቱ ግን የአካባቢውን ነዋሪ አስቆጥቷል፤ ወደ እሰጣገባ ከሰፋም ወደ ግጭት ሊያድግ ይችላል በሚል ውጥረት ነግሷል።