በትግሬው መንግስት የሚደገፈው የሶማሌ ክልል የኦሮሞ ብሄር ተወላጆችን ከሶማሌ ክልል እያባረረ ነው።

Print Friendly, PDF & Email

ከሶማሌ ክልል በሃይል እየተፈናቀሉ ያሉት የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች

(ምንሊክ ሳልሳዊ) :

የትግሬው መንግስት ከሶማሊያ ክልል እና ከልዮ ሃይ ጋር በመሆን ኦሮሞዎች ከሶማልያ ክልል አስገድዶ አያስወጣ ነው።

በኦሮሚያ ክልል እና በሶማሌ ክልል ድንበር ላይ የተነሳው ግጭት እጄ የለበትም ሲል የነበረው የሶማሌ ክልል መስተዳደር በክልሉ የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ የግድያና የማፈናቀል፣ ሴቶችን የመድፈር ግፎችን እየፈፀመ ይገኛል። በሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች ከጅጅጋ በመውጣት ላይ ናቸው። የወያኔ ፌዴራሊዝም በወለደው ችግር እስከ 12 ሺህ የኦሮሞ ተወላጆች በቀጣይነት ይባረራሉ ተብሎ ይጠበቃል ። ይህ በሕወሓት አይዞህ ባይነት በሱማሌ ልዩ ሐይል እየተፈፀመ የሚገኘው ግፍ እጅግ አስፈሪ መሆኑን የጉዳዩ ተጎጂ አካላት ይናገራሉ ።

በቋንቋ ላይ የተመሠረተ የጎሳ ፌዴራሊዝም ሕወሓት መራሹን አገዛዝ ፈተና ውስጥ የከተተው ሲሆን ኢትዮጵያም እንደ ሐገር እንዳትቀጥል አደጋ የሆነ ሲሆን ባለስልጣናት እንደ ዩጎዝላቪያና ሩዋንዳ በእሳት እየተጫወቱ ነው። ከጅጅጋ የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ጉዳቱን በጥሞና የተመለከተ የጅጅጋ ነዋሪ እንዲህ ተናግሯል፦ በጣም አስከፊ ሁኔታ ላይ ነን! እኛ ያለንበት ሁኔታ ፣ ከ ሩዋንዳ ጭፍጨፋ ጋር ተመሳሳይ ነው፤ መንገድ ላይ ያገኙህ የክልሉ ልዩ ኃይል አባሎች ፣ መታወቂያ ይጠይቁሀል፤ የመስሪያ ቤት እና የመንጃ ፈቃድ መታወቂያ ስታሳያቸው፣ ይስቁብህና፣ የግዴታ የቀበሌ መታወቂያ እንድታሳያቸው ያደርጉሀል፤ መታወቂያ ከሌለህ አለቀልህ! እዛው በሰደፍ ማጅራትህን ቀጥቅጠው ይደፉሀል፤ ሸቤ ትወረወራለህ ።

ከሶማሌ ክልል በሃይል እየተፈናቀሉ ያሉት የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች

መታወቂያ አውጥተህ ስታሳያቸው ፣ጎሳህን አይተው ፣የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ከሆንክ በመኪና ጭነው ግዜአዊ ማጎርያ ወስደው ያሳድሩህና ፣ በቅጥቅጥ መኪና ሞልተው ወደ ሀረር ይልኩሀል! በአሁኑ ሰዓት ራሱ፣ የኔ መኖርያ ቤት ከጣብያው ፊትለፊት ስለሆነ፣ የሚጫኑ ሰዎች ጫጫታ ይሰማኛል፤ በዚህ ወቅት ላይ፣ ጂግጂጋ ከተማ ውስጥም ሆነ፣ ሶማሌ ክልል ውስጥ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ተወላጅ ሆኖ መገኘት ከባድ ጣጣ አለው፤ እዚህ ሰፈር ውስጥ ደግሞ የባሰ ነው ፤ ሶማሌዎች የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪዎችን እየደበደቧቸው ነው።

በዚህ መሀል ፖሊሶች መጥተው የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ከጥቃት ተከላክለው ፣ወደ ማገርያ ጣብያ ይወስዷቸዋል፤ የግጭቱ መንስኤ የሚባለው የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ከሐጅ ስነ-ሥርዓት የተመለሱ የሶማሌኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ የአወዳይ ከተማ ነዋሪዎችን አርደዋቸዋል ተብሎ ነው። በጥቂት ጊዜያት ብቻ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ብዙ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ገድሏል፤ አሰቃይቷል። ለዚያውም ድንበር ጥሶ ገብቶ፤ አሁን ላይ በምድር ምንም ዓይነት የመጓጓዣ አገልግሎት የለም! የኢትዮጵያ ዓየር መንገድም፣ ጂግጂጋ መካነ-አዕምሮ( ዩኒቨርስቲ) እያስተናገደ ላለው ዓለም ዓቀፍ የጥናት እና ምርምር ጉባኤ ሲባል እንጂ፣ በረራ ሳያቆም አልቀረም! አላህ ይሁነን ነው ፤ ነገሮች በጣም ተበላሽተዋል።

The latest batch of Oromos displaced by Weyane Liyu Police who just arrived in Chinaksen, Sept 14 2017