ትግራይ በቅማንት በመታገዝ ጎንደርን በመዋጥ የመስፋፋት እቅዷን እውን ለማድረግ እየተጣደፈች ትገኛለች

Print Friendly, PDF & Email

ትግራይ ክልል ጎንደርን በመዋጥ የመስፋፋት እቅዷን እውን ለማድረግ እየተጣደፈች ትገኛለች ፦አሁን ባለኝ መረጃ መሰረት የሪፈረንደም አስፈፃሚ አባላት የተባሉ ልዩ ልዑካን!

ጎንደር ከተማ ውስጥ ” ሳንቃ በር ሆቴል ” (ቀበሌ 13) እና ሮማን ሆቴል (ፒያሳ) ማረፋቼውን እና የመኝታ አልጋ መያዛቸው ታውቋል፡፡

እነኝህ የምርጫ አስፈፃሚ አባላት በትግርኛ ቋንቋ ብቻ እንደሚያወሩ እና ማታ፣ ማታ ደግሞ ከቅማንት ኮሚቴዎች ጋር ለሚስጥራዊ ስብሰባ በተከታታይ እንደሚገናኙ ታውቋል፡፡

በተያያዘ ዜና ፣

ጭልጋ ጮንጮቅ አካባቢ መሳሪያ የታጠቀ የቅማንት ማህበረሰብ ተወላጂ የሆነ ብቻ እና የትግራይ ክልል ልዩ ሐይል ከታች ከዳዋና ከአርማጭሆ ወደ ጮንጮቅና አይከል ለገብያ እና ለሌላ ጉዳይ የሚመጡትን አማራዎች በማስቆምና፣ በመፈተሽ በማንገላታት የዘረፏቸው ሲሆን አንድ እቃየን አልሰጥም ብሎ ለማምለጥ የሞከረ ስሙ አዳነ ሽመካች የተባለ ወጣት ትከሻውን በጥይት መተው በማቁሰላቸው ጎንደር ሆስፒታል ለህክምና ገብቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በዛሬው እለት በጎንደር ከተማ ቁስቋም በተባለው ሰፈር ግቢ እያንኳኩ ቅማንት አለ? ወይስ የለም እያሉ በመጠየቃቸው ምን አገባቹህ በማለት የሠፈሩ ወጣት እያራወጠ ደብድቧቸዋል፡፡ ጎንደር ወደ ተባባሰ ጦርነት እንድትገባ የትግራይ ክልል ልዮ መልእክተኛ እና የክልል አንድ ልዩ ጦር መላኩ ሁኔታው አስከፊ ውጤት እንደሚያሳይ ከወዲሁ ተገምቷል።

 

 

 

ምንጭ፡ ልሣነ ዐማራ- Amhara Press