የቅድመ አያቴ አጽም ማረፊያ ሲያጣ እንዴት አይቆጨኝ!

Print Friendly, PDF & Email

(ልያ ፋንታ)

አንዳንዴ ሰው በአካል ከትውልድ ሀገሩ ተሰድዶ ገንዘብ፣ ገንዘብ ብቻ እያለ ሲንገበገብ ይገርመኛል። ከገንዘብ በላይ ስለሀገሩ መሬት እንደ ተራ የመገልገያ እቃ ሲሼጥ እና ሲለወጥ ዝምም ማለት የሚያስችል ልብ ያለው በዚህ ወቅት የሚገኝ ኢትዮጵያዊ በተለይም በሰሜን አሜሪካ እና አውሮፖ የሚኖር ሰው ነኝ ባይል ለስራ እና ለሆድ የተፈጠርኩ አጋሰስ ፈረስ ነኝ ቢል ይቀለለዋል።

ወደ ተነሳሁበት ርእስ በቀጥታ ላምራ፣ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት ሁመራን ድቅቅ፣ ቁርጥምጥም አድርጎ የበላ ህወሃት ትግሬ አሁን ደግሞ የሰሜን ፖርክ ጎበኝዎች ጉዞ በመቀሌ በኩል እንዲሆን ከመቀሌ ሰሜን ፖርክ የአስፖልት መንገድ ከማዘጋጀቱም በላይ ጎንደርን ፣ መተማን ሙሉ በመሉ ለመጉረስ በቁጥር በአማካኝ ግምት 170,000 ለሚደርሱ ይልቁንም ከአማራው ጋር በደም እና ስጋ የተሳሰሩትን ወገኖች ለማለያየት፣ በተለይም ምሁራን የተባሉ የቅማንት ማህበረሰብ አባላትን በተለያዮ ጥቅማ ጥቅም በመግዛት በጎንደር ዩኒቨርስቲ እና በጎንደር የግብርና መስሪያ ቤቶች ትልቅ ምሽግ በመፍጠር አማራውን ከቅማንት ጋር በሌላ አባባል ሁለት የአንዲት የጎንደር ልጆች ሊገዳደሉ የሰውነት ማሟመዛቅ ላይ ናቸው።

ይህን ጉዳይ የሚያስፈጽሙ ሁለት ልዩ የትግራይ ልዑካን በጎንደር ሁለት ትልልቅ ሆቴሎች ከትዋል። መላ የጎንደርን ህዝብ በጥላቻ እና በክፉ አይን እየገላመጡት። ትግርኛ የማያደምጥ መስሏቸው ምግብ የሚያቀርቡትን የሆቴል ሰራተኞች ሳይቀር በሚያሳዝን የውርጋጥ ስድብ እየተሳደቡ መሆኑን መስማት አሳዛኝ ነው።

ጎንደር ሪፍረንደም ይሰጥባቸዋል የተባሉ 12 ቀበሌዎች ድምጽ ሊሰጥ ሶስት ቀናት ቀርተውታል። ከዚህ በተጨማሪ ጎንደር ከከተማው ሁለት ቀበሌዎችም ድምፀ ውሳኔ ይሰጣል የሚል መረጃ አለ። የሚገርመው ለዚህ የተመረጠው አንዱ ቁስቋም አካባቢ ነው። የቅድመ አያቴ አለቃ ኃይሉ የደብረታቦር መንበረ ንግስት እናቲቱ ማሪያም የመጀመሪያው አለቀሰ የነበሩ ሲሆን ባላቸው ትጋት በተመሳሳይ ስልጣብ እና ሙሉ ክብር የመጄመሪያው የቁስቋም አለቃ በመሆን አገልግለው አጽማቼው እዚያው እንዲያርፍ በኑዛዜ ቃላቼው መሰረት ተደርጓል።

ይታያችሁ የዚህ አካባቢ ነዋሪ ጎንደሬ ቅማንት ነህ ወይስ አማራ እየተባለ ቤት ለቤት ምዝገባ ህወሃት ባሰማራቸው የቅማንት ወጣቶች ሲከናወን ሰንብቷል። ከጥቂት ቀናት በኋላ ቁስቋም የቅማንት ነች፣ እዚያ አካባቢ ያላችሁ አማራዎች በሙሉ ልቀቁ ሊቀጥልነው ማለት ነው።

ወይ ነዶ!

ጎንደር ከተማ ገብቶ የወያኔ ትግሬ በወገን እና በተወለድንበት ቀዮ ሲንፈላሰስ እኛ በሀገር ጉዳይ አስችሎን ተኝተን ማደራችን?
እግዚኦ! ጎንደር የእነ እራስ ውብነህ የእነ ቢትወደድ አዳን ፣የእነ ግራዝማች አድማሱ፣ የእን ጄኔራል ነጋ ተገኝ፣ የእነ አየለ አባጓዴ፣ ወዘተ ሀገር የትግራይ ወንበዴ መፈንጫ ትሁን?
በህግ አምላክ ! ቁስቋም ያረፉት ቅድመ አያቴን በመለያየት የከበሮ ጩኽት ገንጣዮች አትረብሿቼው!
ወይ ነዶ እሳት አመድ ወልዶ!

ልያ ፋንታ