የዓረና ትግራይ ሊ/ር አቶ አብርሃ ደስታ ከአማራ ወደ ትግራይ በተጠቃለሉት ቦታዎች ….

Print Friendly, PDF & Email

የዓረና ትግራይ ልቀመንበር የሆነው አብርሃ ደስታ ሰሞኑን ከአማራ ክልል ወደ ትግራይ ክልል የተጠቃለሉትን ቦታዎች በሚመለከት የዓረና ትግራይ ድርጅት በትግርኛ ቋንቋ ለሰጠው መግለጫ የሰጠውን ማብራሪያ ከዚህ በታች አንብቡ። ዓረና ትግራይ የሰጠውንም መግለጫ ከታች አያይዘነዋል።

**************
የዓረና የክልሎች አወቃቀር ሐሳብ

Abraha Desta

September 9 2017 at 4:34am ·

ዓረና ፓርቲ የትግራይና የአማራ ክልሎች ወሰን ማካለል ጉዳይ አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ ተከትሎ ሦስት ጥያቄዎች ቀርበውልናል።

1, ሁሉም የኢትዮጵያ መሬት ነው ስትሉ አልነበረምንዴ? አሁን ምን ተገኘ?

2, ክልሎች በጂኦግራፊ መካለል አለባቸው አላላችሁምን?

3, የብሄር ሳይሆን የክልል ፓርቲ ነን ትላላቹ። እንዴት ትግራይን ትወክላላቹ ታድያ?

መልስ

1, አዎ! ሁሉም የኢትዮጵያ መሬት ነው። ሁሉም ክልሎችም የኢትዮጵያ ናቸው። የኢትዮጵያ መሬት ለክልሎች ይሰጣል። የክልል መሬት ደግሞ ለግለሰቦች ይታደላል። የኢትዮጵያ መሬት ነው ማለት ግን ከአንድ ግለሰብ ወይ ክልል ወደሌላ በዘፈቀደ ይዛወራል፣ ይሰጣል ማለት አይደለም። ሁሉም መሬት የኢትዮጵያ ቢሆንም ባለቤትነቱ የጋራ ሳይሆን የግል ነው (ወይ መሆን አለበት)። መሬት ለክልል ወይ ግለሰብ መሰጠቱ ኢትዮጵያዊነቱ አይለቅም።

ለምሳሌ፡ የእንደርታ መሬት አለ። መሬቱ ለአርሶአደሮች ታድሏል እንበል። የእንደርታን መሬት ከታደሉ አርሶአደሮች ሓጎስ እና ገብረመድህን ይገኙባቸዋል። አሁን የእንደርታ መሬት ለሓጎስና ገብረመድህን ተሰጥቷል። መሬቱ ስለተሰጠ የእንደርታ የሚባል መሬት የለም ማለት አይቻልም። የሐጎስና የገብረመድህን መሬት ሆኖ ሳለም የእንደርታ መሬት ነው። የሐጎስና የገብረመድህን መሬት የእንደርታ ስለሆነ የሓጎስን መሬት ቀምተን ለገብረመድህን ወይ ሌላ አካል አሳልፈን መስጠት እንችላለን ማለት ግን አይደለም። የኢትዮጵያ መሬት ነው። የኢትዮጵያ መሬት እንደመጣልን ከአንድ ክልል ወይ ግለሰብ እየቆረስን ለሌላ ማደል እንችላለን ማለት ግን አይደለም።

2, ዓረና ክልሎች በጂኦግራፊ መሰረት መካለል አለባቸው ብሎ አያምንም። ከአንድነት ፓርቲ ጋር ያልተግባባንበት አንዱ ነጥብም ይሄ ነው። ባሁኑ ሰዓት በጂኦግራፊ የምንካለልበት ዕድል የለም። ዕድሉ የሞተው ድሮ ነው በአፄዎቹ ግዜ። ያኔ ጭቆና ባይኖር፣ ብሄር መሰረት ያደረገ አድልዎ ባይፈፀምና በእኩልነት የምንኖርባት ሀገር ብትኖረን ኖረ በ”ብሄር ጭቆና” ተወልደው በብሄር የተደራጁ ሓይሎች ባልኖሩ ነበር። በአድሏዊ አገዛዝ ምክንያት የትግራዋይነት እና የኦሮሞነት ስሜት ከዳበረ ቆይቷል። እንደ ውጤቱም አሁን በ”ብሄር” ተካለናል። በብሄር የመካለሉ ጉዳይ መፍትሔ ከመሆን ይልቅ ራሱ የባሰ ችግር ፈጥሮ አማራነት፣ ዓፋርነት፣ ሶማልነት፣ ቤኑሻንጉልነት፣ ጋምቤላነት ወዘተ ስሜት ወልዷል።

ይህ የተበታተነ ስሜት ቀላል ፈተና አይደለም፡ የኢትዮጵያን አንድነት ለሚመኝ ሁሉ። የኢትዮጵያን አንድነት ታሳቢ በማድረግ “ብሄር” መሰረት ያደረገ የክልሎች አወቃቀር ችግር ነው። ችግር ስለሆነ ተብሎ አሁን ያለውን አወቃቀር በጂኦግራፊ ለመተካት ማሰብ በራሱ ግን የባሰ ጥፋት ነው።

ምሳሌ ልስጥ፡ መንገድ ላይ ፈንጂ ተጠምዷል እንበል። መንገድ ላይ ፈንጂ መጠመዱ ስህተት (ችግር) ነው። ስህተቱን በመቃወም ፈንጁን ከረገጥከው ግን የባሰ ጥፋት ነው። ማድረግ ያለብህ ፈንጁን መርገጥ ሳይሆን ፈንጂ መቀበሩ አምነህ ተቀብለህ፣ ሳትረግጠው (እንዳለ ትተህ ወይ መኪናህ አቁመህ) በጥንቃቄ ማምከን መቻል አለብህ።

ዓረና አሁን ያለው የክልሎች አወቃቀር ከነ ችግሩ እንዳለ ተቀብሎ በክልል ህዝቦች መካከል ፍቅርንና አብሮነትን በመስበክ የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በአብሮነት የሚኖርበትና የኢትዮጵያን አንድነት የሚጠበቅበት አግባብ ያመቻቻል። ለዚህ ሲባል በክልል ህዝቦች መካከል ግጭት የሚቀሰቅስ ማንኛውም ተግባር አይደግፍም። በዚህ መሠረት ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል የሚወሰድ (የሚቆረስ) መሬት (አንድ ሜትርም ይሁን) ከቶ መኖር የለበትም። ወደፊትም አይኖርም። በክልል መሬት ላይ ድርድር የለም። ስለዚህ መግለጫ ማውጣታችን ተገቢ ነው።

3, የብሄር ሳንሆን የክልል ፓርቲ ነን። በትግራይ ክልል ሦስት ብሄሮች አሉ፤ ኩናምኛ፣ ኢሮብኛ እና ትግርኛ ተናጋሪዎች። የሁሉም ነን። ከሁሉም አባላት አሉን። ለሁሉም የቆምን ነን። “የብሄር ፓርቲ ነን” ብንል የየትኛው ብሄር ልንሆን ነው? ትግራይ ውስጥ የሚገኙ ሁሉ የኛ ናቸው። በብሄር አንለያቸውም። አንድ ትግራይ! ለዚህ ነው በዓረና ደረጃ የትግራይ ክልል ፓርቲ ነን የምንለው። በመድረክ ደረጃ ደግሞ የኢትዮጵያ ፓርቲ ነን።

ስለዚህ ተጋሩ ኢትዮጵያውያን ነን። ጥቅማችንና ክብራችንን አሳልፈን አንሰጥም። በኢትዮጵያዊነታችን እንጠቀማለን እንጂ አንጎዳም።

ትግራዋይነት ኢትዮጵያዊነት!

It is so!!!

*****************************************************
የዓረና ፓርቲ መግለጫ ከዚህ ቀጥሎ ቀርቧል።
****************************************************
Arena Party ዓረና ፓርቲ

September 8 2017 at 11:07am ·

ህዝቢ ትግራይ ኣብ ጉዳይ ምሕንፃፅ ዶብ ፀገዴ ሓበሬታ ናይ ምርካብ ሕገ መንግስታዊ መሰል ኣለዎ !
(ካብ ውድብ ዓረና ትግራይ ንዲሞክራስን ሉኣላውነትን ዝተውሃበ መግለፂ)

ኣብ ኢትዮጵያ ጉዳይ ዋንነት መሬት ጉዳይ ህልውና እዩ። ህዝብና ብቀጥታ ይኹን ብተዘዋዋሪ መንገዲ ናብርኡ ምስ መሬት ኣዝዩ ዝተኣሳሰረ እዩ። ስለ ዝኾነ ድማ መንግስቲ ዘሕልፎ ምስ መሬት ዝተኣሳሰር ዝኾነ ይኹን ዓይነት ውሳነ ህዝቢ ክሳተፈሉን ክፈልጦን ግድን እዩ።

ኣብ ዞባ ምዕራብ ወረዳ ፀገዴ ከባቢ ግጨው ተኻይዱ ዝበሃል ዘሎ ምክላል ብወገን መራኸብቲ ሓፋሽ ክልል ኣምሓራ ይጋዋሕ ዘሎ ሓበሬታ “ትግርኛ ተዛራቢ ህዝቢ ናብ ውሽጢ ምምሕዳር ክልል ኣምሓራ ክካለልን ክመሓደርን ብውድባት ህወሓትን
ብኣዴንን ተወሲኑ” ከም ዘሎ እዩ።

ብሚድያታትን ካድረታትን ህወሓት ዝወሃቡ
ዘለው ሓበሬታታት ድማ ባዕሎም ንባዕሎም ዝዋቕዑን ዘይተጣለሉን ሓበሬታትት እዮም። ህዝብታት ሃገርና ኢትዮጵያ ቋንቋ መሰረት ዝገበረ ዓርሰ ምምሕዳር ተግባራዊ ኣብ ዝግበረሉ እዋንን ህዝቢ ዝመረፆ ምምሕዳር ናይ ምምስራትን
ናይ ምውሳንን ሕገ መንግስታዊ መሰል ዝፈቕደሉ ግዘን እናሃለወ፤
ሰፋሕቲ ናይ ገባራት ሕርሻ መሬትን ናይ ኢንቨስትመንት ቦታት፣ ብማሕበር ልምዓት ትግራይ ዝተሰርሑ ኣብያተ ትምህርትን ጥዕና ጣብያታትን ብዘይፍቓድን ድሌትን ነባራይ ህዝቢ ግጨውን ኸባቢኣን ናብ ክልል ኣምሓራ ክካለል ከም ዝተገበረ ‘ሞ እዚ ድማ ኣብ ውሽጣዊ ንሕንሕ ስልጣን ዝኣተው ውድባት ህወሓትን ብኣዴንን መሰል ህዝቢ ብምዕምጧቕ ንመተዓረቕን መናውሒ ዕድመ ስልጣኖምን ከም መስዋእቲ ዘቕረቡዎ ነውራም ስራሕ ምዃኑ እዩ።

ህዝቢ ትግራይ ከም ብዓልዋና እቲ ጉዳይ፣ ውድብ ዓረና ትግራይ ውን ከም ንረብሓ ህዝቢ ትግራይ ጠጠው ዝበለ ህዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ውድብ ብዛዕባ እቲ ተወሲኑ ዝበሃል ዘሎ ውሳነን እቲ
ኣብ ባይታ ዘሎ ሓቂን መብርሂ ክወሃቦን ዓረና ይሓትት።

ህወሓት ኣብዚ ጉዳይ ንህዝቢ ትግራይን ንውድብ ዓረና ትግራይን ሓበሬታ ክህብ ፍቓደኛ እንተዘይኾይኑ ዓረና ትግራይ ኣብቲ ሕገ መንግስቲ ዝፃረር ውሳነ ኣመልኪቱ ህዝቢ ብምፅዋዕ ኣብ መላእ ትግራይ ብዝተፈላለዩ መንገዲታት ተቓውሞኡን መርገፂኡን ምስ ህዝቢ ክመክር ምዃኑ የፍልጥ።

ክብርን ሞገስን ኣብ እዋን ብረታዊ ቓልስን ኣብ እዋን ሰለማዊ ቓልስን ምእንተ ፅቡቕመፃኢ ትግራይ ክቡር ሂወቶም ዝገበሩ ሰማእታት።

ዓረና ትግራይ ንዲሞክራስን ሉኣላውነትን !
3 ጳጉሜን 2009 ዓ/ም
መቐለ