“ውሃን ምን ያስጮኸዋል…..”

Print Friendly, PDF & Email

(ዴቭ ዳዊት – Dave Dawit)

“ውሃን ምን ያስጮኸዋል ቢሉ፥ በውስጡ ያለው ድንጋይ” የሚል በሳል አማራዊ ብሂል አለን።

ከፊት ለፊታችን በታሪካችን አይተነው የማናውቅ የጥፋት ድግስ በትግሬው ቡድን ተዘጋጅቶልን ቀናት እየተቆጠሩ ባሉበት በዚህ ፈታኝ ወቅት በዋናነት በትግሬ ዲቃላዎች፥ ሲቀጥልም የአማራዊነት ብኩርናቸውን “በምስር ወጥ” በለወጡ ሆድ አደሮች የሚዘወረው ተላላኪው እና ራሱን ብ.አ.ዴ.ን. እያለ የሚጠራው ቡድን “ተደራድሬ ሰፋፊ የእርሻና የኢንቨስትመንት መሬት ለአማራ አመጣሁ” በሚል ስላቅ ጆሯችንን ማደንቆሩን ስራዬ ብሎ ተያይዞታል። እኛም ይህን ጩኸት አስመልክተን በዚህች አጭር ጽሑፍ ሁለት ነገሮች ላይ አጽንኦት ልንሰጥ ወደድን።መልካም ንባብ!

1. ከተባለው የድንበር ማካለል የአማራ ህዝብ ምን አገኘ?

መልሱ “ጩኸት” /Echo Chamber/ የሚል ነው።

በሁለት ተመጣጣኝ ባልሆኑ ቡድኖች መካከል በሚደረግ የይስሙላ ድርድር ወቅት የድርድሩን አንኳር ውጤት የሚወስደው ቡድን ድርድሩ ጤናማ እና በተደላደለ ሜዳ ላይ የተካሄደ ለማስመሰል ለደካማው ቡድን የጩኸቱን ድል /Echo Chamber Trophy/ ይተውለታል። እናም ደካማው ቡድን ከራሱ አብዛኛው ተወስዶበት ግን ለእርሱ የተተወችለትን ቅንጥብጣቢ እንደ ትልቅ ድል በማግዘፍ በእልፍ እያባዛ የሆዱን በሆዱ ይዞ ይጮኻል። ይህች የጩኸት ፖለቲካውም ደጋፊዎቹን የሚሸነግልባት ብቸኛ መፅናኛው ነች።

በነገራችን ላይ ይህች “የጩኸት ድል” /Echo Chamber Trophy/ የምትለውን አባባል በአንድ ወቅት የሶቭየት መሪ የነበሩት ክሩስቾቭ አሜሪካውያን አቻዎቻቸውን ለመሸንቆጥ በግል ማስታወሻቸው ላይ ያሰፈሯት አባባል ስትሆን ከረጅም ዓመታት በኋላ የግል ማስታወሻቸው መፅሐፍ ሆኖ ወጥቷል። እኛም ለተነሳንበት ነጥብ ጥሩ ማሳያ ይሆናል ብለን ስላሰብን አባባሏ የተፈጠረችበትን ክስተት በምሳሌነት ከተመለከትን በኋላ ወደ ጥንተ-ነገራችን እንመለሳለን።

እንዲህም ሆነ። እ.አ.አ. ኦክቶበር 22, 1962 ዓ.ም. ከምሽቱ 7 P.M. ላይ 35ኛው የዩ.ኤስ. አሜሪካ ፕሬዝደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ለአሜሪካ ህዝብ ሀገራቸው ከሶቭየት መንግስት ጋር የኑክሌር ፍጥጫ ውስጥ እንደገባች፣ የሀገሪቱ ጦርም በመጀመሪያ ደረጃ ተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኝ፣ኪዩባ /Cuba/ ላይ የሚተከሉ የኑክሌር ሚሳኤሎችን የጫኑ የሶቭየት መርከቦችም ከፍሎሪዳ 90 ማይል ርቀት ወደ ምትገኘው የፊደል ካስትሮዋ ኪዩባ እየመጡ መሆኑን በዚህም የአሜሪካ የጦር መርከቦች ኪዩባን በመክበብ የሶቭየት ኑክሌር ተሸካሚ መርከቦች ጋር ፍጥጫ ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ ብሎም በማንኛውም ሰዓት የኑክሌር ጦርነት ሊጀመር እንደሚችል ገለፁ።

በእርግጥ ኬኔዲ ለህዝብ ይፋ ከማድረጋቸው አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ነበር ይህ በተለምዶ “የኪዩባ የሚሳኤል ቀውስ” በመባል የሚታወቀው ውጥረት በሁለቱ ሀገራት መካከል የተጀመረው።ለዚህም መነሻ የሆነው ዩ-2 በመባል የሚታወቀው የአሜሪካ የስለላ አውሮፕላን በኮሚኒስት ኪዩባ ሰማይ ላይ ሲበር በኪዩባ የተለያዩ ስፍራዎች የሚሳኤል ጣቢያ እየተገነባ መሆኑን በምስል መቅረፅ በመቻሉ እና ደብል ኤጀንት የሲ.አይ.ኤ. ሰላዮች ቀደም ብለው “ቀዩ ጦር” /የሶቭየት መከላከያ ኃይል/ በኪዩባ የኑክሌር አረር /Nuclear War-head/ የሚሸከሙ ሚሳኤሎችን የማስወንጨፊያ ጣቢያዎች እየገነባ ነው የሚል መረጃ በመስጠታቸው ነበር።

ይህንንም ተከትሎ በአሜሪካ መንግስት በኩል የአስቸኳይ ጊዜ የግንኙነት መስመር /Hot line Channel/ በሁለቱ መንግስታት መካከል በመክፈት ወደ ድርድር ለመግባት ሲዘጋጁ ከዲ.አይ.ኤ. /Defence Intelligence Agency/ እና ከሲ.አይ.ኤ. ተጨማሪ መረጃዎች ተገኙ። ይኸውም የሶቭየት ጦር የሚሳኤል ጣቢያዎችን ገና እየገነባ ሳይሆን በኪዩባ ውስጥ በተለያዩ ስፍራዎች ተገንብተው ያለቁ ጣቢያዎች ከመኖራቸው ባሻገር ከመቶ በላይ የትኛውንም የአሜሪካ ግዛቶች መምታት የሚችሉ ስትራቴጂክ የኑክሌር ሚሳኤሎች እንዲሁም በርካታ ታክቲካል የኑክሌር መሣሪያዎች በኪዩባ ምድር የመገኘታቸው ምስጢራዊ መረጃ ነበር። ይህም ኬኔዲን ጥርስ የሌለው አንበሳ አደረጋቸው። ስለሆነም ከዚህ በኋላ በድርድሩ የበላይነት የሚኖራቸው የሶቭየቱ ንኪታ ክሩስቾቭ እንጂ ኬኔዲ አልነበሩም።

ትግሬዎች ብአዴን እና የአማራ የመገናኛ ብዙሃን ያልተሰጠውን መሬት ተሰጠኝ እያለ እየዋሸነው አሉ። በትክልል!! እኛ ብአዴኖች እየዋሹ ነው እንላለን!!

ወደ ድርድር ሲገቡም ክሩስቾቭ ሁለት ወሳኝ ጉዳዮችን ይዘው ብቅ አሉ። የመጀመሪያው አሜሪካ በማንኛውም ጊዜ ኮሚኒስት ኪዩባን በጦር ኃይሏ እንደማትወር ዋስትና መስጠትና ይህንንም በይፋ ለዓለም ህዝብ በሚዲያ ማሳወቅ የሚለው ሲሆን ሁለተኛው የመደራደሪያ ነጥብ ግን የአሜሪካንን እጅ የሚጠመዝዝ ነበር። ይኸውም ከጥቂት ዓመታት በፊት አሜሪካ በቱርክ እና በደቡባዊ ጣልያን የተከለቻቸውን ሶቭየትን መምታት የሚችሉ “ጁፒተር” የተሰኙ ሚሳኤሎቿን በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ነቅላ እንድታነሳ የሚያስገድድ ነበር። ይህ ሁለተኛው የመደራደሪያ ነጥብ አሜሪካንን በኔቶ /NATO/ አጋሮቿ ዘንድ “የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም” የሚያስብል ትልቅ ፖለቲካዊ ኪሣራ የነበረው ቢሆንም የኬኔዲ አስተዳደር ግን አሜን ብሎ ከመቀበል ውጪ አማራጭ አልነበረውም። በመሆኑም የኬኔዲ አስተዳደር በምላሹ ከክሩስቾቭ የፈለገው አንድ ነገር ብቻ ነበር። ይኸውም ሁለተኛው የስምምነት ነጥብ ይፋ እንዳይወጣ እና በምስጢር እንዲያዝለት የሚጠይቅ ነበር። ይህም ማለት አጠቃላይ እውነቱ በሶቭየት መንግስት እስካልተገለፀ ድረስ የአሜሪካ መንግስት “በድርድሩ ጥቅሜን አስከብሬ በአሸናፊነት ተወጣሁ” እያለ እንደፈለገ የመዋሸት ዕድል ይኖረዋል።በተግባርም የሆነው ይኸው ነበር። ቀውሱ በተከሰተ በ13ኛው ቀን ድርድሩ ሲጠናቀቅ ኬኔዲ “ክሩስቾቭ ኪዩባን ታደጓት፥ እኛ ግን አለምን ታደግናት” ብለው የሞራል ልዕልና ያላቸው መስለው ለመታየት ሲሞክሩ፤ የአሜሪካ ሚዲያዎች፣ፀሐፊያን እና የፊልም ኢንደስትሪው እውነቱ ተደብቆ የተነገረውን እየያዘ ክሩስቾቭ እጃቸው ተጠምዝዞ መርከቦቻቸውን ከመሀል መንገድ እንደመለሱ፣በኪዩባ የነበረውን የሚሳኤል ጣቢያንም እንደዘጉ ክፍ አድርገው ለዘመናት አስጮኹት።እርግጥ ነው በድርድሩ ያገኙት ውጤት በአብዛኛው “የጩኸቱን ድል” ነበር። ክሩስቾቭም ያንን የአሜሪካውያንን “ድል” ነበር “የጩኸት ድል” /Echo-Chamber Trophy/ ሲሉ በማስታወሻቸው ላይ የከተቡት።

ወደ ቀደመ ነገራችን ስንመለስ በተመሳሳይ ትግሬ ተፈጥሯዊ ድንበሩን የተከዜን ወንዝ ተሻግሮ በአማራ ታሪካዊ መሬቶች ላይ በመስፈር “ባለ ሀገር ነኝ” ባለበት ሁኔታ እንዲሁም የትግሬው ቡድን /ወያኔ ትግሬ/ የአድራጊ ፈጣሪነቱን ሚና በተቆጣጠረበት ሁኔታ ሊደረግ የሚችል ድርድር ሊኖር አይችልም። የሆነው ከጌታ ወደ ሎሌ የተሰጠ የውሳኔ ትዕዛዝ /Imposition/ ነው። የተላላኪው ብ.አ.ዴን. ም “ሰፋፊ የኢንቨስትመንት እና የእርሻ መሬት ለአማራ ተከለለ” የሚለው ተረት ተረት ባዶ “የጩኸት ድል” ነው!!!

ሲጀመር፡- በዋናነት የኤርትራና የትግሬ ደም ባላቸው ግለሰቦች የሚዘወር የወንጀለኞች ስብስብ የሆነ ድርጅት /ብ.አ.ዴ.ን/ የአማራን ህዝብ ሊወክልም ሆነ በአማራ ህዝብ መሬት ላይ ሊደራደር የሚያስችለው ተፈጥሯዊ መሠረት የለውም።

ሲቀጥል፡- ትናንት “ወልቃይት የብ.አ.ዴ.ን አጀንዳ አይደለም” ያለ ድርጅት፣ ትናንት አማራዊው ከያቅጣጫው በጠራራ ፀሐይ እየተዘረፈ ሲሳደድ “ያሳደዱህ የትምክህት…….ስላልጠረግህ ነው” እያለ በቁስላችን ላይ ጥዝጣዜን ሲጨምር የነበረ ድርጅት፣ ትናንት ለትግሬ የእግር ኳስ ስቴዲየም ማሰሪያ ከንግድ ድርጅቱ ዳሽን ቢራ ካዝና አርባ ሁለት ሚሊየን ብር አውጥቶ የለገሰ ነገር ግን መንፈሳዊ እና አለማዊ ሀብቶቻችንን በውስጡ የያዘው ታሪካዊው የጣና ሐይቃችን በአረም ሲወረር ጀርባውን የሰጠ ድርጅት፣ ትናንት በአማራ ህዝብ መሬት እና ወንዝ የተመረተ የኤሌክትሪክ ኃይል ለህዝባችን ተነፍጎ ድንበራችንን ተሻግሮ ትግሬን በመብራት ሲያሽቆጠቁጥ የነበረ ድርጅት፣ የአማራ ሀገር በመሠረተ ልማት /Infrastructure/ እጅግ ኋላ ቀር እንዲሆን ያደረገ ድርጅት፣ ኢንቨስትመንት ወደ አማራ ሀገር እንዳይመጣ፥ ቢመጣም በቢሮክራሲ እና በመሠረተ ልማት አለመሟላት ተማርሮ እንዲወጣ ያደረገ ድርጅት፣ ብርቱው አማራዊ ገበሬ በትግሬው ቡድን /ወያኔ-ትግሬ/ የማዳበሪያ ዕዳ እጅ ተወርች እንዲጠረነፍ ያደረገ ድርጅት፣ ትናንት ወሰናችን በየአቅጣጫው ከውጪም ከውስጥም ሲገፋ አሜን ብሎ ሲቀበል የኖረ ድርጅት ዛሬ በአንዳች የደማስቆ መንገድ ላይ በተፈፀመ አይነት ጳውሎሳዊ ተዓምር ተቀይሮ ለአማራ ህዝብ ጥቅም መከበር ሊቆም አይችልም!! ይልቁን ከጥንትም ዋነኛ ተልዕኮው በጉዳይ አስፈፃሚነት በህዝባችን ጫንቃ ላይ ተቀምጦ የትግሬን ጥቅም ማስጠበቅ ብቻ ነው!!!

እንዲያውም የወሰን ማካለል ተደረገ ከተባለባቸው ሥፍራዎች እየመጡ ያሉ ዘገባዎች የሚያመለክቱት ብ.አ.ዴ.ን የተባለው የትግሬ ተላላኪ ቡድን በሚዲያ እያስተጋባ ካለው ፍፁም ተቃራኒ ነው።

2. ይህ ወቅት ለምን ተመረጠ?

በትግሬ እና በአማራ መካከል የነበረው የድንበር ውዝግብ “በድርድር ተቋጭቷል” የሚለው ወሬ በዚህ ወቅት እንዲነገር መደረጉ ድንገት አልያም አጋጣሚ አይደለም።በእኔ እይታ ይህ ወቅት የተመረጠው በሁለት ምክንያት ይመስለኛል። አንድም ራሱ የትግሬው ቡድን /ወያኔ-ትግሬ/ ጠፍጥፎ የሰራው “የቅማንት የማንነት ጥያቄ” የሚለው ጉዳይ የአማራን ህዝብ ትኩረት ከፍሎታል ብሎ ስላሰበ በዚህ አጋጣሚ በወረራ የያዘውን መሬት ህጋዊ መሠረት ለማስያዝ አመቺ ጊዜ ነው ብሎ በማመኑ /”Disturb the Water, then Grab the Fish” እንደሚባለው አይነት መሆኑ ነው/ ሲሆን በሌላ በኩል በቀጣይ በአማራ ህዝብ ላይ በቅጥረኛው “የቅማንት የማንነት እና ራስን የማስተዳደር መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ” እያለ በሚጠራው ቡድን በሚመራ አካል ሊያካሂድ ላሰበው የእጅ አዙር ጦርነት /Proxy War/ በአደባባይ ከአማራ ጋር ያለብኝን ውዝግብ “በሰላም” ቋጭቻለው በማለት እጁን ለመታጠብ ነገር ግን በውስጥ የጥፋት ዘመቻውን ከመቼውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ ለማካሄድ ነው /”Conceal a Sword behind a Smile” መሆኑ ነው።/

እንግዲህ አማራዊው ወገናችን ሆይ! ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት እንደ ዕጓለማውታ የእኔ የሚልህ ባለመኖሩ በሄድክበት ሁሉ ስትገደል እና ስትሳደድ ኖረሃል።ወሰንህ ሲገፋ እና የአባቶችህ አፅም ያረፈባት ምድርህ ትግሬ እንደ አንበጣ ሰፍሮባታል። ያንተ እና የልጆችህ ህትብት የተቀበረባት ርስትህም ላንተ አኬልዳማ ሆና ትግሬን የመሰለ እሾህ እና አሜከላ ወሯታል። አንተ አማራዊውን ከትግሬ የሚለይህ ድንበር ተከዜ ነው!!! ይህም የድንበራችን አልፋና ኦሜጋ ነው!!! ዛሬ ትግሬ ተከዜን ተሻግሮ እንደ አንበጣ ኩብኩባ መሬታችንን ቢወር፥ አንተ አማራዊው ደግሞ እንደ ግሪሳ በላዩ ላይ ትሰፍርበታለህ። ይህን ለማድረግ ደግሞ ሌላ እንቶ ፈንቶ ሳያስፈልግህ በአማራዊነትህ ብቻ ተሰባሰብ፣ በፍፁም አማራዊ ወንድማማችነት እጅ ለእጅ ተያያዝ፣ ስትተኛም ስትነሳም አማራዊ በመሆንህ ብቻ በዚያች ሀገር ላይ የግፍ ጽዋን መጋትህ ሳያንስ ትግሬ ሀገር አልባ አድርጎ ሊያጠፋህ ቀን ከሌሊት መልኩን እየቀያየረ ማሴሩን አትዘንጋ። ለልጆችህም በአባቶቻቸው ርስት ላይ እኛን ካላጠፋ ዕረፍት የሌለው ጠላት አፅመ-ርስት መሬታችንን እንደወረረ ንገራቸው። በመጨረሻም ከክንድህ ሌላ ማንም መፍትሔ አያመጣልህምና ነፍጥህን አንሳ!!!

“የማን ቤት ፈርሶ፥ የማን ሊበጅ፣
የአውሬ መፈንጫ ይሆናል እንጂ!!!”

ግዮናዊው የአማራ አባት ሀገር በቁርጠኛ የአማራ ልጆች ትግል እውን ይሆናል!!!

ቸር እንሰንብት!
ዴቭ ዳዊት።


ብራና ራዲዮ ከ2 የወልቃይ ተወላጆች ጋር ያደረገውና ሊደመጥ የሚገባው ቃለ መጠየቅ