የኃያላኑ የአማራዎች ቀስት እንደምን ተሰበረ?

Print Friendly, PDF & Email

ትንታጉ የአማራ አክቲቪስት (ዴቭ ዳዊት – Dave Dawit) “የኃያላኑ ቀስት እንደምን ተሰበረ?” በሚል ርዕስ የአማራ ሕዝብ በትግራይ ዘረኞች እየደረሰበት ስላለው የዘር ማጥፋትና ወንጀል እና ሰቆቃ እንዲሁም እያደረገ ስላለው የሞት ሽረት ትግል ሰፋ ያለና ሊነበብ የሚገባ ጠቃሚ ጽሁፍ እንድናነብ አቅርቦልናል። ውድ ወንድማችን ዴቭ ዳዊት በጣም እናመሰግናለን።  መልካም ንባብ።
*****
የኃያላኑ ቀስት እንደምን ተሰበረ?

/ክፍል አንድ/    2009 ዓ.ም

(ዴቭ ዳዊት – Dave Dawit)

በአንድ ወቅት አይደለም ጦር ተሰብቆበት በሠላም ጊዜ እንኳን በሠገነቱ ላይ ከሠፈሩት ርግቦች ላባ ፍላፃን የሚያበጅ፥ በጓሮው ከበቀለው የዘንባባ ዝንጣፊ የጦር ሶማያ የሚሰራው አማራ፤ ጥቃትን የሚሸከም ትከሻ የሌለው፥ በራሱ ባይሆንለት ልጁን ”ደም መላሽ” ብሎ በልጁ ጥቃቱን የሚወጣ አማራ ዛሬ ላይ ጥቃትን አሜን ብሎ መሸከም እንደምን ተለማመደ?የእኛ ያልሆነን የተሸናፊነትንና የተንበርካኪነትን የተገዢነትና የተሳዳጅነትን ቀንበር ለጫንቃችን እንዴት አስተማርነው? ይባስ ብሎ ህልውናችን የቁልቁለት ጉዞውን በአስፈሪ ፍጥነት ሲወርድ እያየን የሚገባንን ያህል ለማድረግ እንዴት ይህ በቂ መነሳሻ /adequate stimulus/ ሊሆነን አልተገባም?

መልሱ በውስጥ እና በውጭ የገጠሙን ተግዳሮቶች /Challenges/ ናቸው የሚል እምነት አለኝ። እነዚህን ውስጣዊ እና ውጫዊ ተግዳሮቶች በትክክል ከለየንና መቅረፍ ከቻልን የአማራ ህዝብ ትግል ፍሬ የማያፈራበት፣ አማራነት ወደ ቀደመ ክብሩ የማይመለስበት፣ አማራዊም የአባቱን ሀገር ግዮናዊውን የአማራ ሀገር የማይመሰርትበት እና የሚመኘውን እንደሰው የመኖር መብቱን የማይጎናፀፍበት አንዳችም ምክንያት አይኖርም።

1. ውስጣዊ ተግዳሮቶች /Internal Challenges/፡- ይህ በመወለድ አማራዊ ከሆኑ ከራሳችን ወገኖች የሚመነጩ ተግዳሮቶችን ያካትታል።

ሀ. የባሮክ እንቅልፍ /Change Blindness/፡-

በቅዱስ መጽሐፍ ብቻ ሳይሆን በእስራኤል የታሪክ ድርሳናት ውስጥ ከተፃፉት ታሪካዊ ትርክት መካከል የባሮክ ታሪክ አንዱ ነው። ነብዩ ኤርምያስ በነበረበት ዘመን ባሮክ እና አቤሜሌክ የሚባሉ ደቀ-መዛሙርት ነበሩት። ሁለቱም በየዕለቱ ወደ ፈጣሪ ሲፀልዩ ”አቤቱ የኢየሩሳሌምን ጥፋት አታሳየን” ይሉ ነበር። ኤርምያስም ከዕለታት በአንዱ ቀን ሁለቱንም ወደ ተለያየ ቦታ ላካቸው።ባሮክ ከተላከበት ቦታ ሲመለስ የፀሐዩ ንዳድ ይበረታበት እና በአንዲት ዛፍ ስር እንደተጠለለ ያሸልበዋል።እግዚአብሔርም በዚያ ባሮክን ለስድሳ ስድስት /66/ ዓመታት በፅኑ እንቅልፍ ጣለው። ነገር ግን ባሮክ ባሸለበባት በዚያች ቅፅበት የባቢሎን ወታደሮች የኢየሩሳሌምን ቅጥር አፈራርሰው በመግባት ነብዩ ኤርምያስን ጨምሮ እስራኤላውያንን በሙሉ በግዞት ወደ ባቢሎን ወሰዷቸው።

ፀሎቱ ሰምሮለት የኢየሩሳሌምን ጥፋት ያላየው ባሮክ ከረጅም እንቅልፉ እንደተነሳ ለ66 ዓመታት መተኛቱን ስለማያውቅ፤ለውጡንም ስላልተረዳ ያኔ የሚያውቀውን የኢየሩሳሌም መንገድ መፈለግ ጀመረ። ፈልጎም ስላላገኘ ግራ ተጋብቶ እያለ አንድ ሽማግሌ ሰው ያገኝና የኢየሩሳሌም መንገድ በየት ነው? ብሎ ሲጠይቅ ያ አረጋዊ ሰውም ”ኢየሩሳሌም በጠፋች በስድሳ ስድስት አመቷ የኢየሩሳሌምን መንገድ ትጠይቀኛለህን?” አለው።

እኛም ዛሬ እንዲህ እንላለን፡- ከረጅሙ እንቅልፍህ ነቅተህ ”ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊነት፣ አንድነት…” የምትል አማራዊ ለውጡን አስተውል! ኢትዮጵያ ከጠፋች ዘመናት አልፈዋል። የሸዋ መኳንንት የምኒልክን ሞት ምስጢር አድርገውት አመቺ ጊዜ ሲመጣ ይፋ እንዳደረጉት ሁሉ ወያኔም ኢትዮጵያ የምትላትን ሞቷን በአዋጅ ሊነግርህ አመቺ ጊዜ ብቻ ነው የሚጠብቀው። እንደ ኖህ ዘመን ሰው የጥፋት ውሃ መዝነብ ሲጀምር ነው መርከብ መስራት የምጀምር አትበል። መርከብህ የሆነውን ግዮናዊውን የአባትህን የአማራን ሀገር ለመስራት መነሳት ያለብህ ዛሬ ነው። ኖህ ከጥፋት ውሃ የዳነው መዝነብ ከመጀመሩ በፊት መርከቡን ቀድሞ ስላዘጋጀ ብቻ ነው።

አንድ ስሩ ተቆርጦ የሞተንና የደረቀን ዛፍ አርቲፊሻል ቅጠልና አበባ ብታለብሰው ከሩቅ ለሚያየው ሰው ዛፉ በህይወት ያለ ሊመስለው ይችላል። የዛሬዋ ኢትዮጵያም እንዲሁ ወያኔ ጊዜ ለመግዣ ባለበሳት አርቲፊሻል ቅጠልና አበባ በህይወት ያለች ብትመስልም ዳሩ ከሞተች ዘመናት አልፈዋል። ለመሞቷም ያንተ እጅ ስለሌለበት፡-

”ይሆናል ብለን ወፍ አጠመድን፥
ሳይሆን ሲቀር ግን ፈተን ለቀቅን።”

ብለህ ወደ ወገኖችህ ተመልከት። የሞተችውን ኢትዮጵያ በህይወት እንዳለች አስመስሎ በራሱ ምናብ የሚቃዥውን የአማራ ተወላጅም ከሰማህ አንቃው አለበለዚያ ግን ሎጥ ወደ ምትጠፋው ሰዶም እና ገሞራ ዞሮ እንዳላየ ሁሉ አንተም የቅዠቱ ተካፋይ ላለመሆን ዞረህ ሳታይ ሊመጣ ካለው መከራ ለመትረፍ ወደ ተስፋ ምድርህ ወደ ግዮናዊው የአባትህ ሀገር ምስረታ ተሰብሰብ።

ለ. የሹላማይቷ ሴት ምላሽ /Bystander Effect/፡-

ጠቢቡ ሰሎሞን ከፃፋቸው መጽሐፎች መካከል በአንዱ ውስጥ የሹላማይቷ ሴትና የወዳጇ ታሪክ ይገኝበታል።

የሌሊቱ ግርማ በሚያስፈራ፣ ጠል በሚወርድበት በዚያ ምሽት ሹላማይቷ ሴት በአልጋዋ ላይ ነበረች፤ እንቅልፍ ግን አልወሰዳትም። ካስፈሪው ጨለማ፣ከሚወርደውም ጠል ለመጠለል ወዳጅዋ የሆነው ሰው የቤቷን መዝጊያ እያንኳኳ ልብን በሚነካ ቃል ”እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ መደምደሚያዬ ሆይ፥ በራሴ ጠል፥ በፀጉሬም የሌሊት ነጠብጣብ ሞልቶበታልና ክፈችልኝ። ” እያለ ሲማፀናት ከወዳጅ የማይጠበቀውን ምላሽ እንዲህ ስትል ትመልስለታለች፡- ”ቀሚሴን አወለቅሁ፤ እንዴት እለብሰዋለሁ? እግሬን ታጠብሁ፤ እንዴት አሳድፈዋለሁ?”…… (Continue Reading, pdf)