ወሎ ዩኒቨርሲቲ የሆዳም ወያኔዎች መጫወቻ የሆነ የትምህርት ሳይሆን የሙስና ተቋም ነው።

Print Friendly, PDF & Email

ወሎ ዩኒቨርሲቲ የሆዳም ወያኔዎች መጫወቻ የሆነ የትምህርት ሳይሆን የሙስና ተቋም ነው። ከዚህ በታች የተዘረዘረውን ሪፖርት አንብቡ እና እንደ እኛ ተገረሙ። በዩኒቨርሲቲ ስም ከሚነግዱ ቢዘጉት ይሻላል!

“የወሎ ዩኒቨርስቲን ብልሹ አሰራር ለማስተካከል የቀረበ ሪፖርት:-

በአሁኑ ጊዜ መንግስት ዩኒቨርስቲዎችን በሰዉ ኃይል ልማት ግንባታ ከፍተኛ ሚና እንዲጫወቱ በየዓመቱ ከፍተኛ መዋለ ንዋይ በመመደብ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ተቀዳሚዉ የትኩረት አቅጣጫዉ በማድርግ እየሰራ ይገኛል። ይሁንና አንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች አመራሮችና አጋሮቻቸዉ ይህንን ዓላማ በመዘንጋት ባገኙት አጋጣሚ ስለራሳቸዉና ስለ ግል ብልጽግናቸዉ ደፋ ቀና ሲሉ ይታያሉ። በዚህም እኩይ ተግባራቸዉ ለአካባቢዉ ማህበረሰብና ለሚያስተምሯቸዉ ተማሪዎቸ የብልሹ አሰራርና የሙስና ተግባራትን በማሳየት ግንባር ቀደሞች ሆነዉ ይገኛሉ።

ለእነዚህም ችግሮች ዋናዎቹ ተጠያቂዎች የበላይ አመራሮቻቸዉና ተከታዮቻቸዉ መሆናቸዉ የማያጠራጥር ጉዳይ ነዉ። በመሆኑም እነዚህ አመራሮች ለመንግስት እጅግ ፈታኝ ሆነዉበታል። የሚያሳዝነዉ አመራሮቹ የሚሾሙት በትምህርትና በመምራት ብቃታቸዉ ሣይሆን

• በመድርክ ላይም ሆነ ባገኙዋቸዉ አጋጣሚዎች የአገር እንዲሁም የአካባቢ ተቆርቋሪ ለለዉጥ የሚተጉ በመምሰል ከፍተኛ ፕሮፓጋንዳዎችን በማስተጋባት፣

• ቁርጠኛ የድረጅት አባልነትን ካባ በመደረብ አንድ ወይንም ጥቂት የክልል ወይንም የፌደራል ባለስልጣናትን በመቅረብ ቲፎዞ በማዘጋጀት፣

• የዚህ አካባቢ ተወላጅነኝ፣ ስለአካባቢዉ የተሻለ ግንዛቤ አለኝ፣ ከባለስልጣንጋር በእኔ /በሚስቴ/፣ ወዘተ ዝምድና አለኝ ስለሆነም የማስፈጸም አቅሜ ከፍተኛ ነዉ በማለት በአካባቢዉ ተፈላጊነትን ማሳደግ ናቸዉ።

መንግስት አመራሮቹን ወደ ስልጣን ሲያመጣ ከባድ እምነትና ሃላፊነት በመስጠት ጭምር ነዉ። ነግር ግን መንበረ- ስልጠናቸዉን ከተቆናጠጡ በኋለ የሚሰሩት ስራ አስፈሪና አሳፋሪ ነዉ። ምን አለበት ይህንን ነገር በአንክሮ ቢመለከተዉ።

• ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ በአሁኑ ጊዜ የዚህ ዓይነት አካሄድ ሰለባ የሆነዉና ወደ ቁልቁል እየተጓዘ የሚገኘዉ ነገር ግን በተለያዩ ሚዲያዎች በሚነገሩ የፕሮፓጋንዳ ወሬዎች ህዝብንና መንግስትን እያወናበዱ ያሉት የወሎ ዩኒቨርስቲ አመራሮች ለዚህ ዓይነተኛ መገለጫ ናቸዉ። በዚህም በአሁኑ ጊዜ በዩኒቨርስቲዉ ልዩ ልዩ የአሰራር ግድፈቶች ሲከሰቱ ይስተዋላሉ። ለእነዚህም መገለጫዎቹ፡- የፕሬዝዳንቱ ገንዘብ ወዳድነትና አስመሣይነት ተጠናዉቷቸዋል።

• እኒህ ፕሬዝዳንት የዓመቱን አብላጫ የስራ ጊዜያቸዉን (ከ90% በላይ) ወይ በአገር ዉስጥ ስብሰባዎች አለበለዚያ በዉጭ ሀገር በመሄድ በዩኒቨርስቲዉ ዉስጥ አይገኙም በተገኙበትም ጥቂት ጊዜያት ዩኒቨርስቲዉ ያሉበትን ዉስብስብና ስር የሰደዱ ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ ምን በማድረግ ገንዘብ አገኛለሁ በሚል ለልዩ ዓላማ የሾሟቸዉን የኢንተርፕራይዝ፣ የግዥ፣ የተማሪዎች አገልግሎት፣ የፋይናንስ እና የህንጻ ቁጥጥር ሀላፊዎችን በመያዝ በዝግ ስብሰባ ተቀምጠዉ አጭር ግባቸዉን ያሳካሉ ፣

– በቅርቡ ወደ አሜሪካን አገር ግንኙነት ለመፍጠር ብለዉ አስበዉ ኦኮላህማ ዩኒቨርስቲ ከ4 የስራ ባልደረቦቻቸዉ ጋር ይሄዳሉ ከዚያም ከ10 ያላነሰ ቆይታ በኋላ ተመለሡ።

የሚገርመዉ በተመለሱ በ4ኛ ቀናቸዉ ተመልሰዉ በሌላ ጉዳይ ሰበብ ወደ አሜሪካ ይሂዱና ከብዙ ቆይታ በኋላ መጥተዉ ወዲያዉኑ የተማሪ ዎች ምረቃት ላይ ታደሙ።

የሚያስቀዉ ደግሞ በምርቃት ማግስት በብርሀን ፍጥነት የህንድ ቪዛ አግኝተዉ ወደ ህንድ አገር መምህር ለመቅጠር ሄዱ።

– ህንድ ሂደዉ ለ1 ወር ያክል ከትመዉ በመሃል እያንዳንዱን ዲን እየደወሉ እባካችሁ የሚቀጠር መምህር ፍላጎት ላኩ ቁጥሩ ይብዛልኝ ሲሉ ተሰምተዋል። ታዲያማ ወደነዚህ ሀገራት ሲሄዱ የሚወስዱት ገንዘብ መጠን ብቻ ሳይሆን ገንዘብና ኢኮኖሚክ ትብብር ሚ/ር የማያዉቀዉ ጉድ እንዳለ ፀሀይ የሞቀዉ ሀቅ ነዉ። ታዲያ የህንድ ተቀጣሪ መምህራን መብዛት ለዚህ ሰዉ ምን ፋይዳ ይኖረዉ ይሆን አብዙልኝ እያሉ የሚደዉሉት?)

– ከህንድ በተመለሱ ማግስት የሴኔት አባላትን ስብሰባ ጠርተዉ ስለ እኔ፣ ስለ ዩኒቨርስቲዉ፣ እና ስለ ወሎ ተርሸሪ ኬር ማስተማሪያ ሆስፒታል በፌስቡክ ምን ተወራ በማለት ዉይይት አካሄዱ። አንዳንድ ደካማ ጎናቸዉን የተረዱ ሴኔት አባላት አጀንዳዉ ከሴኔት አጀንዳ ዉጭ መሆኑን ቢያስረዷቸዉም አሻፈረኝ ብለዉ ስብስባዉን በተለያዩ ማስመሰያዎች አጅበዉ ቋጩት።

– ይህን ባደረጉ ማግስት ወደ ጀርምን አገር እንደ በረሩ አልተመለሱም ምን አልባትም ከጀርመን ወደ አሜሪካ አምርተዉ ይሆን? ምነዉ ዘገዩ?

– ታዲያ ይህ ሁሉ ሲሆን የወከሉዋቸዉ ምክትሎቻቸዉና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁ በአገር ዉሥጥ በሚገኙ ስብሰባዎች ሰበብ ለከፍተኛ አመራር የተፈቀደ የዉሎ አበል ሁለት ቦታ ለመሰብሰብ ደፋ ቀና በማለት ቢሮ እንደማይቀመጡ ተስተዉሏል። ታዲያ ፕሬዝዳንቱ ሲመለሱ ያልተሰሩ ስራዎችን በሪፖርት አሳምረዉ ስለሚሸፍኗቸዉ (ያቋቋምነዉ ኢንተርፕራይዝ ከሌሎች ዩኒቨርስቲዎች በተለዬ መልኩ…ወዘተ በማለት)።

አይ ኢንተርፕራይዝ !!!!!!!!!!! ድንቄም ኢንተርፕራይዝ !

ዉይ እረስቸ ! ጉድ ነዉ እኮ ! ኢንተርፕራይዝ ሲባል አንድ ነገር ትዝ ያለኝ እስኪ ላካፍላችሁ። በመጀመሪያ ደረጃ ወሎ ዩኒቨርስቲ የማይተገብረዉን እቅድ በማቀድ1ኛ ነዉ። ኮመለዛ የንግድና የማማከር ኢንተርፕራይዝ በማለት ትልቅ እራዕይ ያለዉ ኢንተርፕራይዝን ከ50 000 000 (ሀምሳ ሚሊዮን ብር) በላይ በጀት በመበጀት አቋቋመ፡ ይህ ኢንተርፕራይዝ ከተቋቋመ በኋላ ዋናዉ የሙስናና የብልሹ አሰራር ምንጭ ሆኗል።

የዚህኢንተርፕራይዝ እጅግ በጣም የሚደንቁ መገለጫዎቹ

የሚከተሉትናቸዉ፡-

1. ኢንተርፕራይዙ በተለያዩ የንግድና የማማከር ስራዎች በመሰማራት የመማር ማስተማሩን ስራ እንዲያግዙና ለሌሎች ነጋዴዎች ልማታዊ ንግድን እንዴት በጤናማ ዉድድር ማስኬድ እንደሚቻል ማሳየት ተቀዳሚ አላማዉ አድርጎ ሙህራን ጥናትን መሰረት አድርገዉ ለአካባቢዉ የሚሸጋገሩ የምርምርና የፈጠራ ስራዎችን ወደ ንግድ በመለወጥ መስራት ሲገባ ከዚህ በተቃራኒዉ የአካባቢዉ ነጋዴዎች ሊሰሯቸዉ በሚችሉ ቀላል ንግድ ላይ ተሰማርቶ በኪሳራ ላይ ይገኛል።

ለምሳሌ፡ በሬና በግ በዉድ ገዝቶ ከፍተኛ የመኖ ወጭ ያለ ሙያዊ አሰራር በማዉጣት በኪሳራና በሙስና አሰራር ለሰራተኞችና ነጋዴዎች ይሸጣል፣እጅግ ዉድ በሆነ ዋጋ አዉቶቢስ ገዝቶ ጊቢ ዉስጥ አንዳንዴም ከተማ ገትረዉት ይዉላሉ እንዲሁም በዉድ የተገዛ ፒክ አፕ መኪና ያለምንም አመርቂ ስራ ከተማ ለከተማ በየቀኑ ነዳጅ በመሙላት ሲያዞሩት ይዉላሉ፣ ለ software development work በሚል በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ አዉጥተዉ ከዚህ ሽያጭ ወይም አገልግሎት የተገኘ ገንዘብ ትክክለኛ ሪፖርት ቀርቦ እንደማይታወቅ መረጃወች ይጠቁማሉ።

2. በየወሩ ለሰራተኞች የሚከፈለዉ ደመወዝ ስራዉ ከሚያስገኘዉ ትርፍ አንጻር ሲታይ እጅግ የተጋነነ ሆኗል።

ለምሳሌ፡

•  ስራቸዉን በትክክል የማይተገብሩ ቃናና ፌስቡክ ሲጎረጉሩና ወሬ ሲያመላልሱ የሚዉሉ ጸሀፊዎች፣ ፋይናንስ ሰራተኞች፣ አስተናጋጆች፣ እንዳንድ ባለሙያዎች ከፍተኛ ደመወዝ በየወሩ ይከፍላል።

•  በተጨማሪም ያለ በቂ ስራ ልምድን፣ የስራ ብቃትና እንዲሁም የትምህርት ደረጃ ለኢንተርፕራይዙ ምክትል ፕሬዝዳንት ተብለዉ ለተሾሙት ግለሰብ በየወሩ ለአላፊነት፣ለነዳጅ የሚከፈላቸዉ ገንዘብ ከፍተኛ ኪሳራ ከማምጣቱም በላይ ፕሬዝዳንቷ በዩኒቨርስቲዉ recommendation Circle ከሚባል አለምአቀፍ ተቋም የpostmaster ፕሮግራም በመከታተል ላይ ሲሆኑ ስራዉን በተገቢዉ አልመሩትም

•  ከወሬ የዘለለ ልምድ ሆነ ስልጠና የሌለዉና ከሚሰራዉና ከሚያተርፈዉ ባላይ የሚከፈለዉ ስራ አስኪያጅ ቀጥረዉ ከ15 000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) በላይ ደመወዝ በየወሩ ይከፍላል።

3. ኢንተርፕራይዙ ከተቋቋመ በ3 ዓመታት ዉስጥ ለታሪክ አንድም ጊዜ ትርፍና ኪሳራዉ ኦዲት ተደርጎ አያዉቅም ሲቋቋም የተበጀተለትን በጀት ምን ያክሉን በትክክለኛ ስራ ላይ
እንዳዋለዉና ምን ያክሉ በተቀማጭ እንዳለ አይታወቅም

4. በተለያዩ ጊዜያት ለተለያዩ ፕሮጀክቶች በሚል ሰበብ በአባይ ባንክና በሌሎችም ዝግ አካዉንቶች የተቀመጡት ገንዘቦች ማን በምን ጊዜያት እንደሚያንቀሳቅሷቸዉ አይታወቁም።

5. ባይከሽፍ ኖሮ ለከፍተኛ ኪሳራ ሊዳርገዉ የሚችል የግል ሆስፒታል ግዥም ሊፈጽም ነበር

6. በቅርቡ ደሴ ከተማ ቧንቧ ዉሃ አካባቢ ያለምንም ሙያዊ የገበያ ጥናት ሳያካሂዱ በወር 70000(ሰባ ሺህ ብር) አንድ ሆቴል መሳይ ነገር ተከረይተዋል። ከህንጻዉ አለመመቸትና አጠቃላይ ከአካባቢዉ ማህበረሰብ ደንሞ ወሎ ዩንቨርስቲ ሆቴል ከፍቶ ከኛጋር ሊነግድ መጣብን በሚል ግርምት ላለፉት አራት ወራት ምንም ደንበኛ ባለማግ ኘቱ ስራ አልተሰራበትም፤ ወደፊትም የሚሰራበት አይመስልም። ስለሆነም ከ 280 000 (ሁለት መቶ ሰማኒያ ሺህ ብር) በላይ ዩኒቨርስቲዉን ለኪሳራ ዳርጎታል። በተጨማሪም ለስራ አስኪያጅነት የተቀጠሩት የፕሬዝዳንቱ ወዳጅ/ዘመድ በ7 000 (ሰባት ሺህ ብር) ደመወዝ ሲጨመር በ 4 ወር ዉስጥ ብቻ ኢንተርፕራይዙን በዚህ የሆቴል ዘርፍ ብቻ ከ 300 000 (ሶስትመቶ ሺህ ብር) በላይ ኪሳራ ገጥሞታል።

7. የዩኒቨርስቲዉን የ10ኛ የምስራታ ዓመትን ሲያከብር ሙሉ የምሳ ግብዣ አቅርቦት ኢንተርፕራይዙ በማዘጋጀት ከፍተኛ ትርፍ አገኘሁ በማለት ለከፍተኛ አመራሮች ለእያንዳንዳቸዉ 25000(ሃያ አምስት ሺህ ብር) ትርፍ ተከፋፍለዋል።

8. እጅግ በተጋነነ ዋጋ ከ200 000 (ሁለት ሚሊዮን ብር) በላይ በሆነ ዋጋ በጣም ጠባብ የ ፑል ቤት በላሜራ ለማሰራት ወጭ በማዉጣት እያሰራ ሲሆን ያች ፑል ቤት ይህን ያህል ገንዘብ እንደማታወጣ እየታወቀ ይህን ያህል ገንዘብ ማዉጣቱ እንደተለመደዉ ከኮንትራክተሩ ጋር ሊኖቸዉ በሚችል የጥቅም ትስስር እንደሚሆን ግልፅ ነዉ፣

9. ለተማሪና ለመምህራን ተብሎ በዚሁ ኢንተርፕራዝ የሚመሩ ካፌዎች ከተገልጋዮች በላይ ቁጭ ብለዉ የሚዉሉ አስተናጋጆች የሚበዙበት፤ በየቀኑ የሚገዛዉና በተደጋጋሚ በመኪና ተጭኖ ሲወርድ የሚታየዉ ግብኣት ከሚቀርበዉ አነስተኛ የምግብና ትኩስ መጠጥ አንጻር ሲታይ የት እንደሚገባ ግርምት ይፈጥራል፤ ይህም በዩንቨርስቲዉን ዝርክርክ አስተዳደር መስፈኑን አይነተኛና ጥሩ ማሳያ ነዉ።

ብቻ ተዘርዝሮ አያልቅም… የዩንቨርስቲዉ አስተዳደር ይህንን ብልሹ አሰራር የማያስተካክል ከሆነ ከዚህ በላይ በመረጃ አስደግፈን ለሚመለከተዉ የመንግስት አካል /ፀረ ሙስና / የምንወስደዉ መሆኑን እንገልፃለን።

ለዛሬ እዚህ ላይ ይብቃን!”

ይርጋለም አምባቸው!