እንቁጣጣሽ! – እንኳን ከዘመነ ማቲዎስ ወደ ዘመን ማርቆስ አሸጋገራችሁ – ሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት

Print Friendly, PDF & Email

የተከበራችሁ የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች በሙሉ፤ እንኳን ከዘመነ ማቲዎስ ወደ ዘመን ማርቆስ አሸጋገራችሁ።

(መሰከረም ፩ ቀን ፪ሺ፲ ዓ.ም)

እንቁጣጣሽ!

ውድ ወገኖቼ በዘረኛው የትግሬ ወያኔ የግፍ አገዛዝ የዘር ማጽዳትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ለተፈጸመበት ወገናችን ድምፅ ለመሆንና ዘራችን ከፈጽሞ ጥፋት ለመታደግ ከዛሬ 5 ዓመት በፊት በጥቂት የቆረጡ የዐማራው ልጆች የጀመርነው ትግል በርካታ ተከታዮችን በማፍራት ዛሬ የዐማራው ድምፅ በዓለም ዙሪያ ከፍ ብሎ እየተሰማ ነው። ይህ ድምፅ ወድ ድርጅታዊ ኃይል በመለወጥ ዐማራው ኅልውናውን አስጠብቆ የኢትዮጵያን የአንድነት ትንሣዔ ዕውን የሚያደርግበት ጊዜ እሩቅ እንደማይሆን ሕዝባችን የሚያደርገው ትግልና ትግሉ የሚገኝበት የዕድገት ፍጥነት በግልጽ ያሳያል። ነፃነት እና ከፈለጉት ለመድረስ መስዋዕትነት ይጠይቃልና የሕዝባችን የመከራ ጊዜ ለማሳጠር አስፈላጊውን ሁሉ ለትግሉ ለማዋል በአዲሱ ዓመት ቃላችንን በማደስ የድሉን ፍሬ ለማየት የበኩላችን መወጣት እንድንችል አምላክ ብርታቱን፣የማድረግ ጥበቡን፣ ትዕግሥቱን፣ ቁርጠኝነቱን ከሀብትና ከጤና ጋር እንዲያድለን ፈቃዱ እንዲሆንልን የዘወትር ጸሎቴ ነው። ለሞላ ቤተሰባችሁ መልካሙን ሁሉ እመኛለሁ።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

ተክሌ የሻው
የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ሊቀመንበር