ጎጃም የሚኖሩ ወላጆቿን ወይም ዘመዶቿን በማፈላለግ ህጻን መቅደስ ሽታዬ ከተደቀነባት አደጋ እንታደጋት

Print Friendly, PDF & Email

ይህች ህጻን ልጅ ስሟ መቅደስ ሽታየ ይባላል። ዕድሜዋ ደግሞ ከ11-13 ዓመት ሲሆን ተወልዳ ያደገችው ጎጃም ክፍለሃገር ነው። በምን እና በማን ምክንያት ወደ ደቡብ ክልል እንደተወሰደች አይታወቅም። እዚያ ከደረሰች በኋላ የገጠማት ነገር ግን ልብ የሚሰብር ነው። ቡርጂ ሶያማ በሚባል አካባቢ ህሊና ቢስ የሆኑ ሰዎች አንድ አይኗን አጥፍተው የገንዘብ መለመኛ አድርገዋታል። ሁለተኛዋ አይኗን አጥፍተው ሙሉ በሙሉ አይነስውር ለማድረግ በሚሞክሩበት ሰአት ግን የፍትህ አካላት ደርሰው አንድ አይኗን ያጠፋውን ሰው በህግ ቁጥጥር ስር አውለውታል።

መቅደስ በአሁኑ ሰአት ሰዎች ቤት ለጊዜው ተጠግታ የምትኖር ሲሆን በአካባቢው የምታውቀው አንድም ሰው ስለሌለ የነገ ህይወቷ አደጋ ላይ ወድቋል። እናም የአስገድዶ መድፈር እጣፈንታ ሊገጥማት አልያም ሌላኛዋ አይኗ ሊጎዳ ይችላል እና በአስቸኳይ ልንታደጋት ይገባል። ይህንን መልዕክት ሼር በማድረግ ለቤተሰቦቿ እና ለምታውቃቸው ሰዎች መልእክቱ ይደርስ ዘንድ ሁላችንም እንተባበር።

ገና በህጻንነቷ ዓንድ አይኗን ማጣቷ ሳያንስ ሙሉ በሙሉ አይነስውር እንዳትሆን ሁላችንም በምንችለው ሁሉ ልንረባረብ ይገባል!

ከምስጋና ጋር
ልሳነ_አማራ

የበለጠ መረጃ ለማግኘት ፌስ ቡክ በመሄድ ልሣነ ዐማራ- Amhara Press  https://www.facebook.com/AmharaPress/  ማነጋገር ይቻላል