ድንበር :- “ድንበር ሲፈርስ፤ መሐሉ ዳር ይሆናል”

Print Friendly, PDF & Email

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
nigatuasteraye@gmail.com

ጥር ፳፻፰ ዓ.ም.

ማሳሰቢያ

ስለኢትዮጵያ ድንበር መፍረስ፤ መገሰስና መጠገን በተደረጉበት ዘመናት ሁሉ የነበረች አሁንም ታፍና በመታዘብ ላይ ያለች፤ ወደፊትም የምትኖር ይህች ጥንታዊት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፤ አሁን ህዝቧ ስለሚነጋገርበት ስለ ድንበር ምን ትላለች? የሚለውን ለመዳሰስ ይህችን ጦማር ሳዘጋጅ በውስጧ የተሸከመቻቸውን ሀሳቦች በተጻፉባቸው ቋንቋዎች እንዳሉ አቅርቤያቸዋለሁ። ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚሰነዘረውን አፈና ለመከላከል የጠቀስኳቸውን ሀሳቦች በተጻፉባቸው ቋንቋዎች እንዳሉ በማቅረቤ (ግእዙን ግን ትርጉሜዋለሁ) ይቅርታ በመጠየቅ ያጎደልኩትን እየሞላችሁ፤ የተሳሳትኩትን እያረማችሁ ታነቧት ዘንድ በታላቅ ትህትና አቀረብኩላችሁ።

መግቢያ

“ድንበር ሲፈርስ፤ መሐሉ ዳር ይሆናል” በሚል ርእስ ይህች ጦማር የፈለቀችበት ዘመን፤ ኢትዮጵያን ከጎረቤት አገር የሚያዋስኗት ድንበሮችና፤ በውስጥም ዜጎቿ ተከባብረውና ተዋደው የሚኖሩባቸው ወሰኖች የፈረሱበት፤ ረዥም ዘመን የኖሩ ዛፎች የተጨፈጨቡት፤ መልሰው እንዳያቆጠቁጡ፤ (እንዳያንሰራሩ) ግንዶች ከነስራቸው የነገሉበት ዘመን ነው። ለ 25 ዓመት ኢትዮጵያን የገዛው የወያኔ መንግሥት፤ አገሪቱን ከተቆጣጠረበት ቅጽበት ጀምሮ በቅርብ የሚታየው ከሩቅ የሚሰማው መፍረስና መገሰስ ቢሆንም፤ በየዘመኑ ድንበር እየጣሱ ከመጡ ወራሪዎች ጋራ ለዳር ድንበር ስትፋለም የኖረች ጥንታዊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተውህዶ ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ወቅት ምን ትላለች?የሚለው ጥያቄ በኢትዮጵያውያን መካከል ብቻ ሳይወሰን፤ የኢትዮጵያን ታሪክ በሚያውቁ በውጭ አገር ሊቃውንት መካከልም መነጋገሪያ ሆኗል።

በዚህ ወቅት የፈለቀችው ይህች ጦማር፤ ይህች ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ስለ ድንበር የተሸከመችው ሀሳብ የራሴ ፈጠራ አይደለም። በሱባዔ፣ በህልም የተከሰተልኝ አይደለም።አልበቃሁምና መንፈስ ቅዱስ ገለጾልኝም አይደለም። የቅኔ ችሎታቸውን ከመንደር ቧልትና ነገረ ዘርቅ ያላቀቁ ሊቃውንት የህዝቡን አሉታ እየተመለከቱ፤ በሰረዙ ቅኔያቸው ሲዘርፉበት የተማርኩት ነው። የትርጓሜ መምህራንም ባንድምታ ትርጉማቸው የሚያመሠጥሩት፤ ለእለታዊ ጥቅም ተልእኳቸውን ያልሸጡ ቀሳውስትም በጸሎታቸው ሲገልጹት የሰማሁትና “ድንበር ሲፈርስ መሐሉ ዳር ይሆናል፤ የዛፍ ጫፉ ሲጨፈጨፍ ግንዱ ጫፍ ይሆናል”እያሉ የመንደር አዛውንትም ሲናገሩ የሰማሁትን ነው።

ክርስቶስ “እውነት እልሀለሁ የምናውቀውን እንናገራለን፤ ያየነውን እንመሰክራለን” (ዮሐንስ ም 3፡ ቁ 11)። እንዳለው፦ ከአባቶቻችን የተማርንውን፣ የምናውቀውንና ያየነውን ባባቶቻችንም የተጻፈውን ከውጭ ከተሸከምነው ለይተን ብንናገር፤ ወይም ከውጭ በሰማነው ባንሸፍነው፤ በወያኔ ፖለቲካ የተናጋቸውን ኢትዮጵያን፤ በነ ገብረ ኪዳን ደስታ፣ ስብሐት ነጋና አባይ ፀሐዬ የተናወጠችውን ቤተ ክህነታችንን፤ በሰይጣን ውሸት ከመበከሏ በፊት የነበረችውን ገነት ባደረግናቸው ነበር። ነበር ከሚለው ከጸጸት ንግግር ተላቀን ዛሬም አለ! ማለት እንችል ዘንድ ከዚህ በታች በዘረዘርኴቸው፦

፩ኛ ኢትዮጵያዊነት የተመሰረተበት ስርዓተ አምልኮ
፪ኛ የኦሪቱ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ስለ ድንበር ምን ይላሉ?
፫ኛ ድንበር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓተ ጸሎት
፬ኛ ድንበር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክና ባህል

በሚሉ አንቀጾች ያዘጋጀኋትን ይህችን ጦማር በስርዓተ አምልኳችን እጀምራለሁ።  ….. Continue Reading, pdf