ግማሽ ልብ ይዞ ቆራጥ ነኝ ማለት እራስን ማታለል ነው!

Print Friendly, PDF & Email

(Ethio Asnesaw)

ምን ግፍ እየተፈጸመ እንዳለ በኢትዮጵያ ሀገር ውስጥ ለማወቅም፤ የረቀቀ ጠፈር ተመራማሪ መሆንም፤ ከአንድ ፈጽሞ አይጠበቅም።

የእጅ አዙር ግኝ ገዢ አማካኛች፤ በመገናኛ ብዙሀናቸው የሐቁን ገጽታ በዝምታ ሊከበክቡት ቢሞክሩም፣ ጎመራው አፈትልኮ ከወጣ ሰንበትበት አለ እኮ ጃል። እራስሺን አታታይ? ወይ ድብን ያልሽ የእግዚብሔር ባሪያ ሁኚ አልያም የነፍስ በሊዎች እና የባንዳዎች አባል ሆነሽ ተገላገይው። ግማሽ ልብ ብሎ ነገር የለም።ቁርጥሺን እወቂው። በሙሉ ልብ አንድ ዓላማ ላይ መዋለል ነው ወዳጄ። ሺ አመት ለማይኖርበት የሰው ተክለ ስውነት ከንቱ ኑሮ፣ ከአጋንንቶች ጋር ተደራድሮ ምድራዊ ገነቴን አሳካለው ብሎ መፍጨርጨር የትም አያደርስም። ቁርጡን ማወቅ ነው ወገኔ! ምክንያቱም የምታልለው እራስህን እንጂ ፤ የታፈነውን ሰፊውን ህዝብ አይደለም። “አይ እኔ የሕዝብ አስደሳች ነኝ እንጂ ፓለቲከኛ አይደለሁም ” ብሎ የፈሪ ህይወትን መምረጥ ፤ ብሎም ልክ እንደከብቶች ሳር ግጦ፤ ከዚያም ስገራ ጥሎ ለማደር ካልሆነ ነገሩ፣ ታድያ ምን ለየን ከነሱ! ከጋማ ከብቶቹ?  ከማለዳ ምሽት   ለመብል ዘመቻ፤  ልክ እንደ እንስሶቹ ። መንፈሳዊ ጥቅሱን እንሆ አንቡ..

ማትዬስ 4:4 ሰው ከእግዚአብሔር፡ አፍ፡በሚወጣ፡ቃል፡ዅሉ፡እንጂ፡በእንጀራ፡ብቻ፡አይኖርም። ይላል ሀቁ።

ስለዚህ የሕዝብን ብሶት በዳሽን ቢራ አማካኝት፣ አዝማሪን ቀጥሮ፣ ማኮላሸት ዘበት ነው። ለሆድ ብሎ፣ ስጋን ፈርቶ፣ ህሊናን ሸጦ፣ እንዳላየ መስሎ፣ ከጨቋኞች ጋር ማበር፣ በሁዋላ። ዋጋ ያስከፍላል። እንደውሻ በሔደበት መጮህ የአዝማሪ ተግባር መሆን የለበትም። ለሐገር የሚያቀነቅኑትን አፍኖ  ከዘራፊው ወንበዴ ጋር የሚተባበሩትን ማስተዋወቅ፣ ዞሮ ዞሮ ውድቅ ነው። በምግባርህ  ባንዳ ከሆንክ ከኤሊ ቀፎህ ውጣ። አታስመስል! ሌባም መሆንክ ይለይህ። ተደብቅህ መኖር አትችልማ። አንተም ሰርቀህ መኖር እንድምትሻው ሁሉ ሌላውም በቅንነት  በራስ ጥረት  ህይወቱን የሚመራ ብዙ የሕብረተሰብ አካል አለ።

ገና ለገና የኔ ጎሳ ተወቀሰ ብሎ በማለቃቀስ የነፍስ ገዳዮችን አረመኔዎችን ግፍ ማስተባል ተቀባይነት የለውም። ያንተ ነገድ/ጎሳ አካል ምንም ቢሆን በጭፍን ጎጠኝነት ተንተርሶ፣ እውነት ላለመንገር አድሎ ማሳየት፤ እራን ማጋለጥ ነው። ዘረኞችም ሁሉን ነገር በዘር መነፅር ስለሚይት፣ ፊታቸው ያለውን እውነታ ለመረዳት በፍጹም አይችሉም። ባጭሩ ታውረዋል ዲዳ የአይምሮ ድኩማን።

በመጀመርያ ሀገር ለማስተዳደር እጩ የሆነ ሰው፣ ከላይ ከተጠቀሱት የስነልቦና  ደዌዎ ነፃ መሆኑን ምዘና ያስፈልገዋል። የጥንቱም  አያቶቻችን በስልጣኔያቸው፤ ህዝብን ወክለው የሚያገለግሉ አካላትን ቅድሚያ የስነልቦና፣ የስነምግባር፣ የስነመነፈሳዊነት፣ ብቃት እንዲያልፉ ይደርጉ ነበር። ማንም ተነስቶ ህዝብን ማሽበር አይችልም ነብር። እድሜ ለባሩድ ጥይት ለጠብ ነጂዎች ነገር ተለውጦ፣ ጨካኝ አረመኔው እራሱ ደንቀሮ ሐገር ሲያዶነቅር እየመሰከርን ነው። ሁለም ስው እንደ ጥቂቶቻቹ፣ ነፍሳችሁን እና ህሊናችሁን ለከንቱ ሆዳቹ እንደሽጣችሁንት እንዳይመስላቹ። የኢትዮጵይ አምላክ አውላላውን ህዝብ ህሊና ለግሶታል።