ከትግሬ ወያኔ ከፍተኛ በጀት ተመድቦለት እየተነቀሳቀሰ ያለው አሸባሪ የቅማንት ኮሚቴ ቡድን እቅዶች

Print Friendly, PDF & Email

(ልሣነ ዐማራ- Amhara Press)

ከትግሬ ወያኔ ከፍተኛ በጀት ተመድቦለት ጎንደርን የደም አውድማ ለማድረግ እየሰራ ያለው የቅማንት ኮሚቴ ተብየው አሸባሪ ቡድን እቅዶች ሚስጥራዊ ዶኩመንት ከዚህ ላይ ያንብቡ pdf

የቅማንት ኮሚቴ የሚባለው የህዋሃት ቡድን በሚቀጥሉት ጊዜያት ሊሰራቸው ያሰባቸው ጸረ-አማራ ተግባራት አፈትልከው ወጥተዋል። እኛም ሙሉ ዶክመንቱ እጃችን ላይ ስለገባ እንዲህ አቅርበነዋል። ሁሉም አማራ መረጃውን ለህዝብ በማድረስ አማራ እንዲነቃ ማድረግ ተገቢ ነው። እነሆ ዶክመንታቸው

“ከድል” ማግስት መከናወን ያለባቸዉ ተግባራት

የቅማንት ማንነትና ራስ የማስተዳደር ሃላፊነት እዉን ሊሆን ሳምንታት ቀርተዉታል፡፡ ይህን የተዋደቅንለትን አላማ ግቡ እንዲመታ ከተፈለገ ለህዝባችን ዘላቂ ልማትና ተጠቃሚነቱን ሊያረጋግጡ የሚችሉ ተግባራትን በፍጥነት መተግበር ይኖብናል ብለን እናስባለን፡፡ እስካሁን ያደረግናቸዉን ነገሮች ለስልጣን ብለን አይደለም ይልቁን ቅማንት ያለዉን ሃብት በአግባቡ አልምቶ ሀብት እንዲፈጥር፤ ልጆቹን እንዲያስተምርና ባጠቃላይ ድህነትን በቅማንት ዉስጥ ታሪክ ለማድረግ ነዉ፡፡ በቅማንት ዉስጥ አዲስ መንፈስና አዲስ አሰራር በመመስረት የለዉጥ ፋና ወጊ መሆን ይጠበቅብናል፡፡ ስለዚህም ይህን አጠር ያለ ማብራሪያ ኮሚቴዉ ያቀረበ ሲሆን በተለይም የ12ቱ ቀበሌወች ዉጤት አይተን ተግባራቶችን ልንከልሳቸዉ እንችላለን፡፡

መስከረም 7

1. ምርጫዉን ማስተባበር

ምርጫዉ እንዲሳካ የበኩላችን ማድረግ፡፡ አሁን ባለዉ የህዝብ ስብጥር እነዚህን 12 ቀበሌዎች ማግኘት ከባድ አንደሚሆን ይታወቃል፡፡ ነገር ግን በጎ ፈቃደኛ ወጣት የቅማንት ልጆች ምርጫዉ በሚካሄዱበት ቀበሌወች በተለይም ለወደፊት ለቅማንት ህልዉና አስፈላጊ የሆኑ ቀበሌወች ላይ እንዲሳተፉ ዝግጅት ተደርጓል፡፡ ከላይ አርማጭሆ (ሳታ ምድራሮ፤ ጅንክራ፤ ብር ለበሆ፤ ጫንቂያ፤ ዘራጌ፤ ሮቢት፤ከች፤እንጭናቆና ጋባ ባጠቃላይ 3200 ተመልምለዉ ወጣቶች መታወቂያ ተዘጋጅቶላቸዋል)፡፡ ይሄ ቡድን አብዛኛዉ ሄዶ እንዲሳተፍ የተፈለገዉ አቸራ፤ አኩሸራና መንዶካ ነዉ፡፡ ነገር ግን ምን ያህሉ መጨረሻ ላይ በምርጫ ጣቢያወች ሄደዉ እንደሚካፈሉ አይታወቅም፡፡ መስከረም 4 ሮቢት ላይ ኦረንቴሽን እንሰጣቸዋለን፡፡

ኮሚቴዉ ለመጓጓዣና የምግብ የሚሆን ገንዘብ እስከ መስከረም 4 ቀን በፍጥነት እንዲያፈላልግ፡፡ የገንዘቡ መጠን በኮሚቴዉ የህዝብ ግንኙነት በኩል እየተዘጋጀ ሲሆን ዶክመንቱ አንደደረሰን ለሚመለከተዉ አካል በፍጥነት በማደርስ ገንዘቡ እንዲሰባሰብ ማድረግ፡፡ ጭልጋ አካባቢ የመረጥናቸዉ ወጣቶች ባብዛኛዉ በራሳቸዉ ወጪ የሚንቀሳቀሱ ሲሆን ከኩሻይና፤ ዳንጉራ፤ ዳንጉልቶ፤ ናራ አዉራርዳ፤ ቀርቢያ ቀበሌወች 2142 ወጣቶችን የተመረጡ ሲሆን ይሄ ግሩፕ ባብዛኛዉ ሽንፋ የምርጫ ጣቢያ ሄደዉ አንዲመርጡ ተመድበዋል፡፡ ለነዚህ ኦረንቴሽን መስከረም 5 ቀን ጮንጮቅ ላይ ይሰጣል፡፡

ጥንቃቄ ማድረግ ያለብን ህዝቡ በሚያዉቅበት መንገድ ፈጽሞ መሆን የለበትም፡፡ የተወሰኑ ከፌደራል የመጡ አስመራጭ ኮሚቴወችን ላንድ ማርክ ሆቴል በቀደም ምሽት ላይ ያገኘናቸዉ ሲሆን፡፡ ሊመርጡ የሚሂዱትን ልጆች በደንብ የማሰልጠን ስራ እንድንሰራ አቅጣጫ የሰጡን ሲሆን ዋና ዋና የሚባሉ አስመራጭ ኮሚቴወችን ከመስከረም ሰባት በፊት ለማግኘት ቀጠሮ እንዲሰጡን ጠይቀናቸዋል፡፡ ሰዉ ልኮ አንዲመርጥ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የምርጫ ኮሮጀዉን ሙሉ ለሙሉ ካልቀየርነዉ ሰዉ በመላክ ብቻ የምርጫዉን ዉጤት ለመቀልበስ አዳጋች ይሆናል፡፡

ወደ ኮዘራ ቀበሌ (ቋራ የሚሄዱ ወጣቶች በፍጥነት መመልመልና መታወቂያ ማዘጋጀት ያስፈልገናል)፡፡ አንሰር ወተት አዛዉ አካባቢ በተለይም ጭልጋ ከተማ ያለዉ ወጣት ሄዶ አንዲመርጥ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ የቅማንት ባለሃብት ፈልገን ነጋዴ ባህር አድርሶ የሚመልስ መኪና እንዲሰጡን ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ ሌላዉ ጥንቃቄ የሚያስፈልገዉ ለማኛገኘዉ ቀበሌ ብለን ልጆቻችን እንዳይቀጠፉ ጥንቃቄ ማድረግ ነዉ፡፡ ችግር የሚፈጥር ከሆነ ካካባቢዉ በፍጥነት መራቅ ነዉ፡፡

2. አይከልን መረከብ

ወጣም ወረደም አይከል ለቅማንት ትሆናለች፡፡ ያለ ሪፍረንደም እንዲሰጠን እየጠየቅን ያለበት ሁኔታ እና በቅርቡ ዉሳኔ እንደሚሰጡ ነግረዉናል፡፡ ነገር ግን እዚህ ከተማ ላይ ሪፍረንደም ይካሄድ መባሉ አይቀርም፡፡ ይህ ደግሞ አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ ሁለት አማራጭ መጠቀም ሊያዋጣን ይችላል፡፡ አንደኛዉ መቀመጫዉን አይከል ማድረግ፡፡ ያ ማለት የኣመራም የቅማንትም መቀመጫ ማድረግና ከጊዜ ብዛት ወደ ቅማንት መጠቅለል፡፡ ሌላኛዉ ግን የክልሉ መንግስት ላይ ጫናዉን ማብዛት ያለምንም ማመንታት የቅማንት አስተዳደር ዋና ከተማ እንዲሆን፡፡

በርግጥ ቃል የገቡልን ቢሆንም አሁንም ግን እያመነቱ እንደሆነና የአማራዉን ጫና መቀነስ አንችልም የሚል ስጋት አሳድሮባቸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሚቀጥለዉ ጊዜ እንዲሁ የተለያዩ አካባቢወችን የይገባኛል ጥያቄ እያነሳን የድሮ አርስታችን የማስመለስ ትግሉ ይቀጥላል፡፡ አንደሚታወቀዉ ቋራ፤ደንቢያ፤መተማ፤ታች አርማጭሆ፤ጎንደር ዙሪያ፤ጎንደር፤ አለፋ፤ጣቁሳ ድሮ ቅማንት ይኖርባቸዉ የነበሩ አካባቢዎች ሲሆኑ መጤዉ አማራ በጉልበት እንደያዛቸዉ ታሪክ ይናገራል፡፡ ስለዚህም አኒህ ቦታቸወች የቅማንት እስኪሆኑ ድረስ መታገል ይጠበቅብናል፡፡

ክፍል ሁለት ይቀጥላል!