ከብአዴን ጽ/ቤት የተገኘ – የ2010 በጀት ዓመት የፖለቲካና ድርጅት ሥራ እቅድ ሰነድ

Print Friendly, PDF & Email

የብአዴን ብልግና በዚህ ዶክመንት ቁልጭ ብሎ ወቷል (አማራ ነኝ እሚል ኧረ የሰዉ ዘር ነኝ የሚል ቢያነበዉ ያስገርማል)

ይሄ ከብአዴን ገና ኢዲት አድርጎ ሳይጨርሰዉ አፈትልኮ የወጣዉ የ2010 እቅድና አቅጣጫን የሚያሳየዉ ዶክመንት የአማራን ህዝብ ከትንሽ እስከ ትልቅ በአጸያፊ የስድብ ዉርጅብኝ አጭቆ አዉጥቶታል። ጹሁፉን ያዘጋጀዉ የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ አለምነዉ መኮነን ነዉ። ይህ ሰዉየ ከዚህ በፊትም አማራን የተሳደበ ሰዉ ነዉ።

….. ከብዙዉ በጥቂቱ …….

1. በክልሉ ዉስጥ የብአዴን አባል የሆኑ መምህራንን ብቃት የሌላቸዉ፤ ወሬ ማዉራት እንጅ ለሃገር የማይጠቅሙ የድርጅት መዋጮ ብር በዛብኝ እያሉ ከማለቃቀስ ዉጪ በሙያቸዉ አንዳችም ነገር ማበርከት የማይችሉ ትህምክተኞች ይላል። በየወሩ ከደሞዛቸዉ ለብአዴን በመቶወች የሚቆጠር ገንዘብ እየሰጡ ከዘለፋ ካልዳንክ። አባልነቱ ምን ያደርግልሃል። እግዚዎ።

2. በብአዴን ዉስጥ ያሉ አንዳንድ አመራሮችና ከድርጅቱ ዉጪ ያሉ ሙሁራን በሽተኞች እንደሆኑ ያትታል። እግዚዎ

3. በሴቶች አደረጃጀት የታቀፉት ሴቶች ደካማና አቅም እንደሌላቸዉ ያወራል። ይሄም የአቅም ግንባታ እንደሚያስፈልገዉ። እግዜዎ

4. የክልሉ ወጣቶች ስራ የማይወዱ በሱስ የተጠመዱና በአስተሳሰብ ያልበሰሉ እንደሆኑ ይተነትናል። እግዚዎ

5. 1.6 ሚሊየን በላይ የብአዴን አባላት ቢኖሩም ይላል አድር ባይ፤ በጸረ ህዝብ አስተሳሰብ የተለከፈ፤ በራሱ መተማመን የሌለዉ ብሎ ይጨፈጭፋቸዋል።

እንዴት ክልሉን የሚያስተዳድር ፓርቲ ንጹህ ዜጎችን ኑሮን ለማሸነፍ የሚታትሩ አስተማሪዎችንና የመንግስት ሰራተኞችን እንዲህ ያንቋሽሻል?

(ከብአዴን ጽ/ቤት የተገኘውን የ2010 በጀት ዓመት የፖለቲካና ድርጅት ሥራ እቅድ ሰነድ ሙሉን ከዚህ ላይ ያንብቡ, PDF)

ምንጭ፡ ልሣነ ዐማራ- Amhara Press Facebook page