ህወሓት በብአዴን ጉዳይ አስፈጻሚነት ጥቃቱን በአማራ ህዝብ ላይ አጠናክሮ ቀጥሏል!

Print Friendly, PDF & Email

(ዳግማዊ ቴዎድሮስ – ከአዲስ አበባ)

ኢህዴን/ብአዴን ማን ነው?

የመጀመሪያ ስያሜው ኢህዴን /የኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ በሚል ከኢህ አፓ /የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ/  በተገነጠሉ ጥቂት የያኔው 1988 ዓ/ም የተማሪዎች አመጽ ተሳታፊ በነበሩ ወጣቶች ህዳር 11 ቀን 1973 ዓ/ም ትግራይ በረሃ ውስጥ ተመሰረት።

ከመጀመሪያ ለዴሞክራሲያዊ አሳቤ ለፍትህና ለእኩልነት ተብሎ መጀመሩ በወቅቱ ከነበረው የአገራችን ችግር አኳያ ሁሉንም የሚያስማማ እበጀህ ኢህዴን የሚያስብል ስለነበር በወቅቱ በጥቂት ተማሪዎች ቁንጮ አመራርነትና በበርካታ የአማራ አርሶ አደር ጋሻነት በተወሰነም ከኤርትራ/በሻቢያ/ በየግዜው የሚማረኩና ስጦታ በሚሰጡ ምርከኞች ከሰዓት-ሰዓት ከእለታት እለታት ከአመታት አመታት እንደ ህጻን ልጅ በዳዴ ጉዞ የጀመረው የወያኔው ኢህዴን / የአሁኑ ብአዴን / ብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅንቄ / ወደ ወታደራዊ ንቅናቄ የተሸጋገረው በ1976 ዓ/ም አካባቢ እንደነበር በወቅቱ የነበሩት ነባር ታጋዮች አጫውተውኛል።

ከዚያ በመቀጠል የፓርቲ ሊቀመንበር እና ም/ሊቀመንበር የወታደራዊ አመራር በመምረጥ ግስጋሴውን እስከ 1978 ዓ/ም ድረስ በተወሰነ መልኩ ነጻ ድርጅታዊ መዋቅር ያላቸው አስመስሎት እንደነበር ቀደምቶቻችን ዛሬ በቁጭት ይናገራሉ። አሁን በኢህዴን/ብአዴን ውስጥ ያለው ችግር የተከሰተው ከ1978 ዓ/ም በኋላ ባሉ አመታቶች ላይ እንደሆነ እነኝሁ ነባር አባላቶች ይናገራሉ።

የችግሮቹ መገለጫዎችም፡-

1. ፓርቲው /ኢህዴን/ የሚወስናቸው ውሳኔዎች በህወሃት አመራር ተቀባይነት ካጡ ተግባራዊ አለመሆናቸው፣

2. አንደ አንድ ፓርቲ ማሰቡ ቀርቶ እንደ ሕወሃት ቅርንጫፍ መታየትና ሁሉም ድርጅታዊ ተግባሮች ከህወሃት መመንጨት መጀመሩ፣

3. በተለይ ወታደራዊ ጉዳዮች እንደ ኦፓርቲ ማቀዱ ቀርቶ ለማጠናከር ተብለው በሚላኩ ጥቂት የመቶዎች (ጋንታዎች) ጋር ከፈተኛ የህወሃት አመራር አብሮ በመምጣት ውጊያዎችን ይመሩ ስለነበር የሚገኘውን ውጤት በህወሃት እንጅ በኢህዴን ስም አይነገሩም ነበር። በወቅቱ ኢህዴን አብዛኛው ሃይሉ አማራ ቢሆንም በአገሪቱ ካሉ ህዝቦች /ብሄር ብሄረሰቦች/ ቁጥሩ እምብዛም አይሁን እንጅ የለለበት አልነበረም። እናም የኢትዮጵያ ህዝቦች በሰሩት ታሪክ ገድለ ታሪኩ ግን የአንበሳውን ድርሻ በያዘው በህወሃት ስም መነገር በመጀመሩ የወቅቱ  የኢህዴን ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ያሬድ ጥበቡ (ጌታቸው ጀቤሳ) እና በአቶ መለስ ዜናዊ መካከል ጥርስ መናከስ ተጀመረ ይላሉ ይህን ቀደምት የድርጅቱን ታሪክ ያጫወቱኝ እውቁ የጦር መሪ የነበረው አሁን በህይወት የሌለው ታጋይ ጥጋቡ አዳነ።  …….  (ኢህዴን/ብአዴን ማን ነው? Read more, pdf)