ይህ የምታዮች የእስረኞች ቅጣትና ስቃይ የተፈጸመው በሊቢያ ወይም በሶሪያ እንዳይመስላችሁ፣ በፋሽስት የትግሬ ወያኔዎች እጅ በወደቀችው በኢትዮጵያ እንጅ! – ፎቶ

Print Friendly, PDF & Email

ከዚህ በታች የምታዩት ፎቶ ሊቢያ ወይም ሶርያ በአይሥ የተፈጸ ከመሰላችሁ ተሳስታችኋል። ይህ እየተፈጸመ ያለው ከትግራይ ምድር በበቀሉ ፋሽሽት ትግሬዎች ላለፉት 26 ዓመታት በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ውስጥ በተለያዮ እስር ቦቶች ታስረው በሚገኙ ኢትዮጵያውያን እየተፈጸመ ያለ ሰቆቃ ነው።

በፋሽሽት ትግሬዎች በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ውስጥ በሚገኙ በእስረኞች ላይ እየተፈጸመ ያለ ሰቆቃ

በኢትዮጵያ እስር ቤትች በህሊና እስረኞች ላይ የሚካሄደው አሰቃቂ ምርመራ ምን እንደሚመስል ይህን ፎቶ ተመልከቱ።

በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ውስጥ በተጠርጣሪነት በታሰሩ የህሊና እስረኞች ላይ እየደረሰ ያለው አሰቃቂ የምርመራ ጥቃት ኢትዮጵያዊያኑን እጅግ በማስቆጣት በማህበራዊ መገናኛዎች ላይ የመወያያና የመነጋገሪያ አጀንዳ ማድረጋቸው ታወቀ።

ሰሞኑን አፈትልኮ በወጣው የእስርኞች በቁም ተዘቅዝቀውና ተሰቅለው ምርመራም ይሁን ቅጣት ሲፈጽምባቸው የሚያሳየው ምስል የኢትዮጵያዊያኑን ቁጣ፣ንዴትና እልህ በመቀስቀስ በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተቀባበሉ ሲወያዩበት ለማየት ተችላል።

ምስሉ በእስር ቤት ያሉና የእስር ቤት ዩኒፎርም ልብስ የለበሱ እስረኞች የመሆኑ እውነታ ማረሚያ ቤቶች እስረኞችን ከመጠበቅ ባሻገር በእስረኞች ላይ አሰቃቂ የቅጣትና የምርመራ እርምጃዎችን እንደሚወስድ የሚያጋልጥ ሆኖ ታይታል።

በፋሽሽት ትግሬዎች በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ውስጥ በሚገኙ በእስረኞች ላይ እየተፈጸመ ያለ ሰቆቃ

በተለምዶ ጉዳዩ በፍርድ ቤት ያልደረሰን ተጠርጣሪን በምርመራ ሂደት የሚያሰቃይ የምርመራ ቴክኒክ በመጠቀም ሲያሰቃዩ እንደነበረ የሚታወቅ ሲሆን አሁን ግን ምርመራቸውን ጨርሰውና አጠናቀው ወደ ማረሚያ ቤት የተላኩ እስረኞች በማረሚያ ቤቱ ውስጥ አስቃቂ የቅጣትና የምርመራ እርምጃ እንደሚካሄድባቸው የተጋለጠ ሲሆን በዚሁ ምክንያትም ህይወታቸው ካለፉ በርካታ እስረኞች መካክል በቅርቡ ለህልፈት የተዳረገው ወጣት በቀለ በያን የሚታወስ ነው።

በየማረሚያ ቤቶቹ በሚካሄድ ማሰቃያ ተግባሮች ለህልፈት የተዳረጉትን አስተዳደሩ በድብቅ እየቀበረ ያፈናቸውን የሚያጋልጥ የቀብር ስፍራ በቅርቡ መጋለጡ የሚታወቅ ሲሆን እነ ፕ/ር መረራ ጉዲና፣አቶ በቀለ ገርባ፣ወጣት ንግስት ይርጋ በእስር ቤቱ ውስጥ የሚደርስባቸውን ማሰቃያ ቅጣት በፎቶና በቃል ማየታችን እና መስማታችን አይዘነጋም።

በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ቅኝ ግዛት ስር የወደቀችው ሐገራችን ኢትዮጲያ ላይ ነው! የምትመለከቷቸው ደግሞ ለእኔ፣ ለአንተ እና ለአንቺ ነፃነት ሲሉ መስዋዕትነት እየከፈሉ ያሉ ወገኖቻችን ናቸው።  ከንፈር መምጠጣችንን አቁመን አምርረን መታገል ካልጀመር የእያንዳንዳችን እጣ ፉንታ ይሄ መሆኑን ለማወቅ ጠቢብ መሆን አይጠበቅብንም።

ምንጭ፡ http://amharic.abbaymedia.com/archives/34212