የትግራይ ክልል የአደር ቃይና ደባርቅ አካባቢን ለመዉሰድ እንደተዘጋጀ ተሰማ

Print Friendly, PDF & Email

(ልሣነ ዐማራ)

ወያኔ ትግሬ ጎንደርን ለ 3 ለምን እንዲከፈል እንደፈለገ ከመቀሌ የደረስን ማስረጃ እንደሚያሳየዉ ለወደፊት አዲአርቃይ፤ ደባርቅና በየዳ አካባቢን ወደ ትግራይ ለመጠቅለል አመች ሁኖ እንዳገኘዉ የተወያዩበት መረጃ ደርሶናል። አሁንም ድረስ በትግራይ ትምህርት ቤቶች የራስ ደጀን ተራራ በትግራይ እንደሚገኝ አድርገዉ በትምህርት ስርአቱ እንደሚያስተምሩ ይታወቃል። ሰሜን ጎንደር በማለት ጠለምት፤ ደባርቅ፤ አደር ቃይ፤ በየዳ፤ ጃናሞራና ጠገዴ ወረዳን አንድ ላይ በማድረግ ወደፊት ወደ ትግራይ ክልል ያለምንም ችግር ለመስገባት መወሰኑ ታዉቋል። ከዚህም በተጨማሪ መተማን፤ ቋራንና ምእራብ አርማጭሆን አንድ ላይ በማድረግ ምእራብ ጎንደር ብሎ በመሰየም በሁመራ በኩል አድርጎ አስከ ቤኒሻንጉል ክልል የትግራይ ክልል ለማድረግ እንደወሰነ ይታወቃል።

ይሄን በማድረግ ታላቋን ትግራይ መስርቶ ለመገንጠል እየሰራ መሆኑ ሁላችንም የምናዉቀዉ ነዉ። ከታች በምስሉ የተያያዘዉ ካርታ የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ያዘጋጀዉ ሲሆን ምእራብ ጎንደር ተብሎ ለመከፈል የተዘጋጀዉ የመተማና ቋራ አካባቢ በትግራይ ክልል ዉስጥ እንደሆነ ያሳያል። ካርታዉን የዛሬ ሁለት አመት በኢትዮጵያ ቴሌቪዠን እንዳስተዋወቀዉ እናስታዉሳለን። እኒህን አካባቢዎች ለመጠቅለል የጎንደር ከተማ ታሪካዉ የአማራ ከተማ ስለሆነች አስቸጋሪ እንደሆነ በማወቅ የጎንደር ከተማን በአማራ ክልል ዉስጥ እንዲቆይ የወሰኑ መሆኑ ይታወቃል። ደባርቅ ሌላኛዋ ወልቃይት ለመሆን ከጫፍ ደርሳለች። ይሄን ሴራ የአካባቢዉ ማህበረሰብ ማክሸፍ አለበት። ከታሪካዊ ቦታህ ከጎንደርና ከታሪካዊ ከተማህ ከጎንደር ከተማ እንዲሁም ከዘርህ አማራ ነጥሎ ትግራይ ዉስጥ ሊያስገባህ እንደሆነ እንዲታወቅ።

ይሄ ካርታ በብአዴን አስተባባሪነት እዉን ሊሆን ወራቶች ቀርተዉታል። መሬታችንና ህዝባችን ላለማስወሰድ የምናደርገዉ የቅዱስ ጦርነት ይጠብቀናል።

ሁላችንም እንዘጋጅ!!