የሕወሐት/ብአዴን ጎንደርን በሦስት ዞን መክፈል ምን ማለት ነው? የታሰበለት ምን ይሆን?

Print Friendly, PDF & Email

(መንግስቱ ሙሴ )

የትግራይ ጠባብ ብሄርተኞች በኢትዮጵያ መንበረ ስልጣን በቆዩበት 26 እረጅም አመታት፣ አገር ከመግዛት ባለፈ በአንድ ጀንበር ቢሊየነር የሆኑ በሁሉም ክልሎች የሕወሐት ደጋፊ በብዛት ትግራውያን ቱባ ነጋዴወችን ያፈሩበት። በየትኛውም ክልል ባሻቸው የፏለሉበት እና ሀብት ንብረት የሰበሰቡበት ሁኔታ ነው ያለው። ይህም ሆኖ ከትግራይ ጠባብ ብሄርተኞች አንደበት በየግዜው የምንሰማው የኢትዮጵያ ብሄርተኝነትን የማራገብ ወይንም በኢትዮጵያዊነት የመኩራት የመመካት ሀሳብ ሳይሆን እኛ እና እናንተ ወይንም እኛ እና እነርሱ በሚል አስተሳሰብ ኢትዮጵያ በሀይል የያዟት ባ’እድ ሀገር እና በማንኛውም ግዜ እና ሠአት ለቀዋት የሚሄዱባት፣ ለእነርሱ ምንም ያልሆነች አድርገው እንደሚመለከቷት ባለስልጣናቱ በየግዜው ከሚያወጧቸው መግለጫወች እና ተራ የውይይት ሀሳቦች መረዳት ይቻላል። ለዚህ ደግሞ የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሐት) አባላትን እና ደጋፊወችን መጠየቅ እና ማወቅ ቀላል መልስ ይሰጣል።

ሪፖርተር የተባለው አገር ውስጥ የሚታተም ጋዜጣ እንደውስጥ አዋቂነቱ ዛሬ ኦገስት 12/2017 እ ኤ አ ባወጣው አጭር ዜና ጎንደር በሶስት ዞእኖች እንደሚከፈል ያትታል። ይህ የሕወሐት ስራ ከቂም እና ከበቀል ጋር የታሰበ። አሁንም ጸረ አማራ እና ጸረ ኢትዮጵያ የሆነ አገር የማፍረስ አዲስ ተንኮል መሆኑ ሁሉም ሊያውቅ የሚገባው እጅግ አሳዛኝ እና አደገኛ ጉዳይ ነው። ዞኖቹ እንደሚከተለው ይሆናሉ

1- ሰሜን ጎንደር ዋና ከተማው አድርቃይ
2- መሀል ጎንደር ዋና ከተማው ያው የፋሲል ከተማ
3- ምእራብ ጎንደር ዋና ከተማው ገና ያልተገለጠ በሚል ዜና አካፍሎናል

ይህ ከላይ የሰፈረው የአከላለል መዋቅር መርዝ ያዘለ መሆኑን እና እንደሚታወቀው የማንነት ጥያቄ ተነስቶ ትግሉ የጋመበት አካባቢ የሰሜን እና የምእራብ ጎንደር ሲሆን ሕወሐት በአጀንዳዋ የያዘችው ይህን ከባቢ ወደታላቋ ትግራይ የመቀላቀል እረጅም አላማም የተጨመረበት የማፍረሱ ጅማሮ መሆኑ ነው።
ሌላው እና መርዘኛው ስራዋ የሚያተኩረው አብሮ ተዋልዶ እና ተጋብቶ በኖረ ሕዝብ መሀል ሞክራም ያልተሳካላትን የማጋጨት እና ደም የማፍሰስ ሰይጣናዊ አላማ ዳግም በእቅድ እና በስራ ለማዋል የምእራብ ጎንደር በሚለው የተጠቃለለ ስውር አጀንዳም ይጨመርበታል።

የወያኔ ሀርነት ትግራይ ዋና አላማ ለሕዝብ በማሰብ ላይ የተመሰረት ሳይሆን አገር በማፍረስ እና ሕዝብን በማባላት ላይ የታቀደ ሰይጣናዊ አላማ ነው። ለዚህ ትግራይ ውስጥ ብዙ አናሳ ብሄረሰቦች እንዳሉ የሚታወቅ ሲሆን ለእነዚህ እራስ ገዝ ክልል መስጠት አይደለም መኖራቸው በዘመነ ሕወሐት አይታወቅም። ለምሳሌ የአዲ ኢሮብ ሕዝብ በዘመነ ሕወሐት ከፍተኛ ተቃውሞ ሲያስነሳ ቆይቷል። የአዲ ኢሮብ ሕዝብ ማህበር መስርቶ እስከ አዲስ አበባ የወያኔ ሸንጎ ድረስ ጉዳዩን እንዳቀረበም ይታወቃል። ከተቃውሞው አንዱ ኢሮብን ለሁለት ከፍሎ አንድ ወደ ኤርትራ ሌላው ወደ ትግራይ መሆኑን ሕዝቡ ለአመታት ምርጫው ኢትዮጵያ መሆኑን ቢያሳውቅም ሰሚ ሳይሆን ግፍ እና በደል ደርሶበታል። ትግራይ ውስጥ ሌሎችም ብሄረሰቦች አሉ ልክ እንደኢሮብ ሕዝብ ሁሉ የእነርሱም እጣ ፈንታ ትግሬ ነህ በሚል ያልሆኑትን እንዲሆኑ ሆነው በግፍ መኖር ነው። የእነርሱን ጥያቄ እና መብት ማክበር በመመስረት ላይ ላለችው ታላቋ ትግራይ አደጋ ነው በሚል እምነት ነው።

ለመሆኑ በአዴን የተባለውስ እና በአለፉት ሁለት ሳምንታት ያየነው ድራማ እውነት ቢሆን ኖሮ የበአዴኖቹ አመራሮች ይህን የማያውቁ በሞግዚት የሚኖሩ እና በጡጦ ላይ ያሉ የሕወሐት ተወካዩች መሆናቸውን እንረዳለን አለያም የትግራይ ነጻነት ግንባር ህግ አስከባሪ፣ ነገር አመላላሽ እና አሳሪና አስገዳይ ለመሆናችው ባለፉት አምስት ቀናት የሰማእታቱን ቀን ለመዘከር በተጠራ የአንድ ቀን የስራ ማቆም ሕዝባዊ እንቢተኝነትን ምክንያት በማድረግ ዛሬ ሕወሐት እና በአዴን ሰፊ የማሰር የማፈን ሕዝብን የማንገላታት፣ ከቤት ቤት በመዞር መፈተሽ እና ብዙ አዛውንቶችን ወደ ወህኒ መወርወሩ አንድ ዋና አስረጅ ሲሆን። በአዴን የተባለ የሕወሐት ስራ ፈጻሚ ለዚህ እየተካሄደ ላለ ግፍ እና በደል አባሪም ተባባሪም በመሆኑ መቀሌ ላይ የተሰራው ሁሉ ድራማ እና ወደ ጎንደር በመስከረም ሊተላለፍ የተባለው የዚያ ተውኔት ቅጣይም እንደ እንቧይ ካብ ተበትኗል።

ይህ በሪፖርተር የሰፈረው ዜና ወደተግባር ሲዞር ዋና አላማው ሕወሐት በመገንባት ላይ ያለችውን ታላቋ ትግራይን ወደነጻነት ጎዳና ለመውሰድ ፍቱን መድሀኒቱ የደቡብ የትግራይን ጎረቤት አፈር ድሜ ማብላት እና ወደ አለመኖር መውሰድ ነው። ይህ ትልቅ የሕወሐት የክፍለ ዘመን ቅዠት እንደሚሆን ደግሞ ጥርጥር የለውም።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!