አስቸኳይ!! ይድረስ ለጎንደር ሕብረት አብላት በሙሉ

Print Friendly, PDF & Email

(መሸሻ ቢያድግልኝ)

ድርጅቶችን ተብትቦ ይዞ ማፈናና ማፍረስ በአሜሪካ የተሰጠው ተል ዕኮ የሆነው ግንቦት 7 ብርሃኑ ነጋ በጎንደር ሕብረት ላይ አፍራሽ ሴራውን እየፈጸመ ነው። በጎንደር ሕዝብ ስም የተሰበሰበው ገንዘብ ለጎንደር ህዝብ ምንም አልደረሰውም የተባለው አልበቃ ብሎ የወያኔና የሌሎች ድርጅቶች ሰርጎገቦች ሕብረቱን እየጠለፉት መሆን በጊዜ መታውቅ አለበት። ጎንደር ሕብረት በቅርቡ በግንቦት 7 ተውጦ ሊፈርስ እንደሚችል ምልክቶች እየታዩ ናቸው።

አበበ “ጤፉ”–የአዜብ ጎላ ተቀጣሪና ጤፉዋን አጣሪ እንዴትስ የጎንደር ሕብረት ዋና አባል ሊሆን ቻለ? በቺካጎስ የሕብረቱ ተቀጣሪ (ያውም በብዙ ገንዘብ ክፍያ) የሆነው ዳዊት ሙጬ ለዓመታት የሌላ ድርጅት አባልና ደጋፊ ሆኖ የታየ አይደለምን? በስመ ጎንደሬ ሕብረቱ ላይ ጉብ ያሉት ስንቶቹ በእውነት ጎንደሬ ናቸው? የሕብረ ሕዝብ ቡድን አለቃ ነኝ ባዩ ቅማንቱ አለም አንተ ገብረስላሴ የሕብረቱ ከፍተኛ መሪስ ሊሆን እንዴት በቃ? የሸንጎ አባል ነኝ ብሎ እየተናገረ ይህ ለጎንደር ቆመ በተባለ ሕብረት ውስጥስ ስራው ምንድነው ? ይህ ብቻ አይደለም ። ሌሎች ጥያቄዎችንም ማቅረብ እንችላለን።

በቅርቡ ግን ከወደ ቺካጎ እየተናፈሰ ያለው ወሬ ግንቦት 7ና የሕብረቱ መሪዎች ውይይት በምስጢር መጀመራቸውን ያቀርባል ። ሕብረቱ ራሱን ወደ ፖለቲካ ድርጅት ሊቀይር ነው ያለው ይህ ወሬ/ዜና ከግንቦት 7 ጋር በማበር አሜሪካ በምታሴረው የሽግግር ሂደት ለመሰለፍና ከወያኔም ጋር ለመስማማት ዕቅድ ተዟል ይላል። ይህን ክህደት ውስጥ ለውስጥ እያካሄዱ ያሉት የሕብረቱ መሪዎች ከግንቦቴዎቹ ጋር መመሳጠራቸው ግን ሊደበቅ አልቻለም። ሊሞት የሚያጣጥረው የብርሃኑ ነጋ ቡድን በዚህ ዓይነትም ነፍስ ሊዘራና ጸረ አማራ ግቡን ሊያሳካ ቋምጦ እንድሚገኝም ተጠቁሟል።

የጎንደር ሕብረት አባላት ይህን ሴራ ማስቆም፤ማደናቀፍ አለባቸው።

በቅርቡ በዋሺንግተን ይካሄዳል በተባለው ሲምፖዚየም ለምሳሌ በአዲስ በወረቀት በተፈጠረ ተቋም ስም ለኢትዮጵያ በሚል ይደረጋል በሚባለው ውይይት የታወቁ አፍራሾች እነ ዶክተር አክሊሉና አልማዝ ዘውዴ፤ ቅማንቱ አለም አንተና ወሎዬው መቶ አለቃ አያልሰው ደሴ ይገኙበታል ። ሁሉም ራሳቸውን ኢትዮጵያዊ ቢሉም ሰልፋቸውና ሚናቸው ግን አከራካሪ ከሆነ ውሎ ያደረ ነው ። መቶ አለቃ አያልሰው ለምሳሌ የሚያስተናገደው ኮሚሽን አማራውን ሕዝብ በወሎ፤ ጎንደር፤ ጎጃምና ሸዋ የሸነሸነ ነው። ይህ ጠቃሚነቱ ለወያኔ ብቻ መሆኑ ከተነገረ ቆይቷል። አማራው የራሱን ሕብረት ከማጠናከር አልፎ ከኦሮሞውና ሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር አንድነትን ቀይሶ ወያኔን ባስጨነቀበት ጊዜ አማራን በአራት መበለትና ተወያዩ ማለት ምን ይጠቅማል? ለማንስ ይጠቅማል? በዚህስ አሳፋሪ ጥረት ውስጥ ለምንስ የጎንደር ሕብረት ተሰልፎ ይገኛል?

ጠንቀቅ በል አማራ ተብሎ ነበር ከዚህ ቀደም–ጠንቀቅ በል የጎንደር ሕብረት ደጋፊና አባል በጎንደር ስም አማራውንም ኢትዮጵያንም በሚጎዳ ጎዳና እንዳትነጉድ ማለት ያስፈልጋል። የጎንደር ሕብረትን ስብስብ የብርሃኑ ነጋ ሰዎች የሙት ሙታቸውን ሰርገውት እንደገቡ በተለይ በአሜሪካ እየታየ ያለ ነው። የኢትዮጵያ ሕብረት በኢትዮጵያውያን እንዳይደረግ ግንቦት 7 በሚያደርገው መፍጨርጨር የጎንደር ሕብረት መግባት መሳተፍ የለበትም። ወያኔም አልተኛም፤ ቅጥረኞቹን አሰርጓል ማለት እንችላለን። ሁሉም የተነሳበትን ዓላማ ሊያስቱት በመጣር ላይ ናቸው ። ከዚህ በፊት የድንበር ኮሚቴ የተባለው ላይ የደረሰውን ማስታወስ ይበቃል ። ለወያኔም ተንኮል ባዳ አይደለንም ባልንበት አፍ ለቅጥረኛው ብርሃኑ ነጋ ተልካሻ ሴራም ሰለባ አንሆንም ማለት እንችላለን ።

ተጠንቀቅ ጎንደር!!