ባህር ዳር እና ደብረታቦር በአጋዚ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ወድቀዋል፣ ወጣቶችም እየታፈሱ ነው፣ የንግድ ተቋማትም እየታሸጉ ነው። በጎንደር፣ በወልደያ፣ በምስራቅ ጎጃም ደምበጫ እና አማኑኢል የሥራ ማቆም አድማ እየተደረገ ነው።

Print Friendly, PDF & Email

በባህር ዳር እና በደብረ ታቦር ከተሞች በአጋዚ ወታደሮች የተፈጸመውን የንጹሃን ዜጎች የነሐሴ 1ን ጭፍጨፋ ለማስታወስ በተደረገው የስራ ማቆም የንግድ ተቋማት ተዘግተው ውለዋል።

የወያኔ መንግስት አድማ ባደረጉት የባህርዳር ነዋሪዎች እና የደብረታቦር ተኖች ነዋሪዎች ላይ የበቀል እርምጃዎችን እየወሰደ ነው። የባህር ዳር ከተማ ሙሉ በሙሉ የአጋዚ ወታደሮች የተወረርች ሲሆን የከተማ ነዋሪው ከቦታ ቦታ በመንቀሳቅስ የእለት ተለት ተክግባሩን ለማከናውን በጣም አስቸጋሪ አድርገውበታል።

በተመሳሳይ መልኩ ነሐሴ 1 2008 ዓ.ም በአጋዚ ወታደሮች በባህር ዳር ከተማ የተፈጸመውን የንጹሃን ዜጎች ጭፍጨፋ ለማሰብ ለ3 ቀናት በአድማ ውስጥ በቆየችው ደብረ ታቦር ከተማ ውስጥ ምሽቱን የቤት ለቤት አፈሳ እየተደረገ መሆኑ ለማውቅ ተችሏል።

የብራና ራድዮው አያሌው መንበር እንደዘገበው ከትላንት ጀምሮ ደብረ ታቦር ዩንቨርስቲ አጠገብ የሚገኘው የሳባ ኢንጅነሪንግ የኤሌክትሪክ ኮንክሪት ፖሎችን የሚያመርተው ድርጅትን በስራ አስኪያጅነት የሚመራው የትግራይ ተወላጅ የሆነው ኮረኔል ሰይፈ በደብረ ታቦር ዙሪያ የሚገኘውን የአማራ ልዩ ሀይል ፖሊስንም በበላይነት እንደሚመራው ተወስኗል::

አመድ በር አካባቢ ሰፍሮ የነበረው የአማራ ልዩ ሀይል ፖሊስ ዛሬ ከሰአት በውሀላ ደብረ ታቦር ቴክኒክና ሙያ ፊትለፊት ወደሚገኘው ካምፕ በተጨማሪነት እንዲቀላቀል አድርጓል:: ይህ በ እንዲህ እንዳለም ማምሻውን ሮንድ እንዲደረግባቸውና ወጣቶች እንዲያዙ የታዘዙ ቦታዎች ሰኞ ገበያ ፣ አጅባር እና መናሀሪያ አካባቢ መሆናቸውን አያሌው መንበር ዘግቧል።

በባህር ዳር ከተማ በአድማው ተካፍላችኋል የተባሉ በርካታ የንግድ ተቋማት የታሸጉ ሲሆን ከነዚህም መካክል በርካታ ሆቴሎች ይገኙባቸዋል።

በተመሳሳይ መልኩ በወልደያ ከተማ በባህርዳር ባለፈው ዓመት ነሐሴ 1 የተገደሉትን ንጹሃን ዜጎች ለማሰብ የተጠራው የሥራ ማቆም አድማ ሶስት ቀን ሲሞላው በደብረታቦር ጎንደርም እንዲሁ በተመሳሳይ 3ኛ ቀኑን የያዘ የሥራ ማቆም አድማ እየተደረገ ነው።

በምስራቅ ጎጃም ህዝባዊ አድማው ወደ ለየለት ደረጃ አምርቷል። በደንበጫ ግርግር ተፈጥሯል። በአማኑኤል ከተማ ሁሉም መደብር ሱቅ ሆቴሎች በሙሉ አገልግሎት አንሰጥም በማለት በአንድ አቋም ዘግተዋል። ደንበጫ ረቡብ ገበያ ወጣቱ መንገድ በመዝጋት የትራንስፖርት አገልግሎት ዋና መንገድ ተቋርጧል። ደብረ ኤልያስ ውጥረት ላይ ይገኛል የጎጃም ህዝብ ወደ ከፍተኛ ቁጣ ማምራቱ የብአዴን አመራር መረበሽ ላይ መሆናቸው ተሰምቷል።

በወያኔ መንግስት የታሸጉ

 

 

በወያኔ መንግስት የታሸጉ