የባህር ዳሩ የአማራ ጭፍጨፋ ትውስታና ያስተላለፈው መልዕክት

Print Friendly, PDF & Email

(አያሌው መንበር)

ልክ የዛሬ አመት ነሀሴ 1,2008 ዓ.ም ህዝቡ በምን ቋንቋ እንደሚግባባ የሚያውቀው ከህዝቡ ጋር ያለ ብቻ ነበር። እርስ በርሱ በምልክትና በመልዕክት የክተት አዋጅ አውጆ ከተለያየ አቅጣጫ በመትመም የባህር ዳር ከተማን የህዝብ ጓርፍ ተመታች። ከወደ ቀበሌ አስራ አራት፣ ቀበሌ አስራ ሶስት፣ ቀበሌ አስራ ሰባት እና ቀበሌ አስራ አንድ ወደባህርዳር የሚየስገቡ መንገዶች ሁሉ ልክ እንደቅዳሜ ገበያ ተጓዥ ተጨናንቀዋል። በእጀቸው መሳሪያ አልያዙም። አማራዊ ወኔን ብቻ ታጥቀው ወመኔ አጋዚን ለመግጠም ወደመሃል እየተመሙ አብዛኛዎቹ መሃል ከተማ የገናኙ።የመጀመሪያው ዙር ከርዕሰ መስተዳደር አካባቢ ያለውን ሰንደቅ አላማ በማውረድ ከዚያም የህወሃት ትግሬዎቹን እነ ኢትዮስትርን በግልምጫ በማየትና ትንሽ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ከዚያም የእነ ዳሸን ባንክን ሰንደቅ በማውረድና በታሪካዊ ባንዲራ በመተካት የእነ አርበኛ በላይ ዘለቀን ሀውልት በመሳለም የእነ መለስን ታፔላ በመቅደድ ሰላማዊ ጥያቄውን ብቻ እያስተጋባ አሁንም ይጓዛል።

በመፈክሩ የነጠሩ የአማራ ጥያቄዎች ተሰምተዋል። ወልቃይት ሆይ ብረሳሽ ቀኘ ትርሳኝ የሚለው የህዝቡ ኩላሊት በሁሉም ዘንድ ስሜት ቀስቃሽና ካልተመለሰ ለዘላለም ሊበርድ የማይችል ጥያቄ ጎልቶ ተተውሏል። ወልቃይት ላይ ጋዝ ያርከፈከፉት እነ ካሳ ተ/ብርሃን፣ በመላላክ የአማራን ህዝብ ጥያቄ እያፈኑ ነው የተባሉት እነ ብናልፍ አንዷለም ህዝባዊ ማስጠንቀቂያ ብቻ ሳይሆን ዳግም በአማራ ስም መድረክ ላይ እንዳይቀመጡ ግልፅ ማብራሪያ ደርሷቸዋል። ህወሃት በ1968 ይዞት የተነሳው የአማራን ህዝብ በጠላትነት የፈረጀ አጀንዳ እና በስልት ለአመታት ሲጠቀምበት የቆየ ሁለገብ ዘር ማጥፋትና ማፅዳት እንዲሁም የአማራን ህዝብ ሁለገብ በሆነ ስልት ማግለል እንደተባነነበት ግልፅ መልዕክት በህዝብ ተላለፈ።

ባህር ዳር ሰኔ 1 2008 ዓ.ም የዘረኛ የትግራይ ወያኔዎች አገዛዝን በመቃወም የተደረገ ሰላሚ ሰልፍ

የህወሃት የበላይነትን አንቀበልም አለ ይህ በሺህ የሚቆጠር የባህር ዳር እና አካባቢው አማራ። የአማራን ህዝብ ለመጉዳት ታስቦ የሚደረግ ሴራ ነገ ኢትዮጵያ የማትወጣው አረንቋ ውስጥ እየከተታት መሆኑን ከቀጠናዊ ሰላምና መረጋጋትና ከሀገር ውስጥ ደህንነት ጋር በማቀናጀት የሱዳን ድንበር እና የህወሃት የእጅ መንሻ ጉዳይ እንዲቆምም ህዝቡ አስጠነቀቀ።

በትግራይ ወያኔ ከተጨፈጨፉ የአማራ ወጣቶች በከፊል

በዚህ ሁሉ ሂደት ግን አማራ ይታገሳል እንጅ አይፈራም፤ የአማራ ህዝብ አሸባሪ አይደለም፣ወልቃይት አማራ ነው፣ ራያ አማራ ነው ወዘተ የሚሉ መፈክሮች በየጣልቃው ያለማቋረህ ልክ እንደኮተኒው ደወል ያስተጋባሉ፤ባህር ዳርን ያነቃንቋታል።ጉዞው አሁንም ቀጥሏል። በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አደባባይ በመታጠፍ ጉዞው ወደ አባይ ማዶ ተጀመረ። ከወደ ወረታና ደራ ሌላ የአማራ ህዝብ በጦር በፈረስ ወደባህር ዳር እየመጣ እንደሆነ ጭምጭምታዎች ነበሩ። (የጎንደርና የጎጃም ኩታገጠምነት ከድንበራዊ ግንኙነት ያለፈ አማራዊ የደም ትስስር ያለው፤ኢትዮጵያዊ አርበኝነትን በጋራ የተላበሰ ህዝብ መሆኑን ልብ ይላሉ)።ጎንደር በአማራ ሳይንት በኩል በእነ ስማዳና ጋይንት፣መቀደላና ተንታ፣ በጎጃም እነ እነብሴ፣ ግንደወይን፣ መካነሰላም ወሎ ጋርም ከኩታገጠም ያለፈ ዝምድና በመኖሩ ሁለቱም ቦታዎች የውስጥ ለውስጥ ግንኙነት ነበር))

እናም ከመሀል ከተማ ወደ አባይማዶ ሰላማዊ ትግሉ ቀጠለ።ቀበሌ አስር እንደደረሱ አስለቃሽ ጭስ ተለቀቀ።በነገራችን የክልሉ ልዩ ሀይልም ይሁን ፖሊስ መሳሪያ እንዲያወርድ ከቀናት በፊት በመወሰኑና በሰላም ማስከበሩ ሂደት ጀሌ ሆኖ (ያለመሳሪያ) እንዲውል በመታዘዙ ፈቃደኛ አልነበረም።ይልቁንም በቅሬታ ውስጥም ሆኖ ጥሩ እድል ፈጠረለትና ሲቨል ሆኖ አብዛኛውም ብሶቱን ከህዝብ ጋር አሰማ።ከክልል ፀጥታ ከአራት ሰዎች ውጭ ትጥቅ የተፈቀደላቸው አልነበሩም።

የሆነው ሆኖ በዚህ የአስለቃሽ ጭስ ያልተገረመው ሰላማዊው የባህር ዳር አማራ ጉዞውን ቀጥሏል።አባይን ተሻግሮ ወደ ገብርኤል አሁንም ይተማል።አንድም የመንግስትም ይሁን የግል ንብረት በዚህ ህዝብ ጥቃት አልተፈፀመም።አቅም ስለሌለው ሳይሆን ታጋሽና አዋቂ ህዝብ ስለሆነ ነው።በዚህ ጉዞው ከጎንደሩ ወገኑ ጋር ፍቅሩን ለመጋራት እያመራ እያለ ግን ዋርካው ላይ (ገብርኤል ሳይደርስ) አንድ አስደንጋጭ ነገር ተከሰተ።ክስተቱ እስካሁንም በደንብ መተንተን እና መረጃውን ማውጣት አልተቻለም።(ምናልባትም ይህ ስርዓት እስኪድወቅ በግልፅ ለማውጣት የሚቸግር ይመስላል።ለጥቂት ሰዎች ደህንነት ሲባል)

የሆነው ሆኖ ግን ከአንድ ቀን በፊት ከዋርካው በስተግራ በኩል ካለው ኮንዶሚኒየም ውስጥ የሚኖሩ ትግሬዎችና ሌሎችም ቤት የቅደመ ጥናት ተካሂዶ እንደነበር ዘግየት ብሎ ታውቋል።ከዚህ ህንፃ ላይ በፈቃድም ይሁን ያለፈቃድ የአጋዚዎች ጊዚያዊ ምሽግ ተሰርቶ ኖሯል።በጊዜው ከኮበል ኢንዲስትሪ ጥበቃ ጋር አለመግባባ ተስከስቶ ስለነበር የመጀመሪያው የግድያውን መነሻ ወደዚህ ልናስጠጋው እንችላለን።ሆኖም ባህር ዳርን በሙሉ በሰላማዊ መንገድ ሲዞር የዋለ ሰላማዊ ህዝብ ለምን እዛ ጥበቃ ጋር ግጭት ፈጠረ? የሚለው ከቀናት በፊት ወደተሰራው የግድያ እቅድ ያመራናል።ከጥበቃው ጋር ግጭት እንዲፈጠር ያደረጉት ሰልፉ ውስጥ የነበሩ ደህንነቶች ናቸው ወደሚል መደማደሚያ ያመራናል።

በዚህ ቅፅበትም ከኮንዶሚኒየም ነዋሪዎች ቤት በቀጥታ የሚተኮስ ድምፅ አልባ መሳሪያ እንደነበር፤አጋዚዎች ቀድመው ከመሸጉባቸው የህወሃት ሰዎች ኮንዶሚኒየም በተጨማሪ ከሌሎችም ቤት ያለፈቃድ ገብተው እንደተኮሱ አረጋግጠዋል።ነዋሪዎች እንዳሉት ታድያ ቤታቸው ውስጥ ዘለው የገቡት አጋዚዎች ሲተኩሱ የጥይቱን ድምፅ አልሰሙትም። ይልቁንም ከደቂቃዎች በኋላ እነርሱ ወደነበሩበት ሲሄዱ በርካታ ቀለሆዎችን አግኝተው ፎቶ በማንሳት ለታሪክ አስቀምጠዋቸዋል።

ይህ እንግዲህ በደቂቃዎች ቅፅበት የተፈፀመ ከ50 በላይ ወጣቶች በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ሰልፈኞቹ ከየት አቅጣጫ እንደሚተኮስ እንኳን ባላወቁበት የአጋዚ ስናይፐር የተጨፈጨፉበት እለትና ቦታ ነው።ይህ አባይ ማዶ ኮበል ፊትለፊት ከዋርካው አጠገብ የተፈፀመ ግፍ ወቅቱ እነ አበበ ገረመውን ጨምሮ ወልቃይት ሆይ ብረሳሽ ቀኘ ትርሳኝ የሚል መፈክርን ይዘው ታሪካዊ መለያችን ተላብሰው የአማራ ህዝብ መብት ይከበር ስላሉ በህወሃት ሰዎች ቀድሞ በታቀደ እና በተወላጆች ትብብር የተረገ ቅንጅታዊ ወንጀል ነው።

ይህ እለት ለእኛ ለአማራዎች ታሪክ ፀሀፊዎች በታሪክ ሰነዳቸው የአማራ ህዝብ ትግልን የሚስያቀምጡበትን መሰረት የጣለ፤ ፖለቲከኞች የአማራን ህዝብ “አዲስ የክስተት ፖለቲካ” በመገንዘብ ፖለቲካዊ መስመራቸውን አስተካክለው እንዲሰለፉ ግልፅ መስመር ያሰመረ፤ የአማራ ህዝብም በአንድ ላይ መቆም የሚችልና አይበገሬነት ስነልቦናውን በደምም ጭምር ያስመሰከረበት እለት ነው።

የባህር ዳሩ አማራዊ ሰልፍ ሰማዕታት ለዘለላለም ሲከበሩ ይኖራሉ። ታሪክ ታሪክ ነው።

አማራም ታሪኩን ያድሳል፤ የነበረውንም ያስከብራል፤ ያከብራል!!!

ድል ለአማራ ህዝብ!