አንዳንድ የተቃዋሚ የዜና ማሰራጫዎችና የብረዛ ዘመቻቸው

Print Friendly, PDF & Email

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ) Ethiopian Semay

ሰላም አቶ አብርሃ በላይ! ድህረ-ገፅህን ከሚከታተሉት በርካታ ኢትዮጵያውያን አንዱ በመሆኔ ብዙ ጠቃሚ እና የሚታመኑ መረጃዎችን ማግኘቴን ሳልገልፅ አላልፍም። በቅርብ ድህረ-ገፁ እንደማትመራዉ ስሰማ አዘንኩኝ። አንድ ግን ሁልጊዜ ከእኔ ጋር አብሮ የሚኖር ቅሬታ ኢትዮ ሜድያ ትቶ ያልፋል። ያም የተወደደዉ እዉነትን ፍርጥርጥ እያደረገ ለብዙዎች የሚያቀርበዉን አንበሳዉን የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያዊዉን የኢትዮጵያን ሰማይ ድህረ ገፅ አዘጋጅ አቶ ጌታቸዉ ረዳን መጣጥፎች በኢትዮ ሜድያ አለማዉጣቱ ነው። እኛ ግን ማግኘታችን አልቀረም። እኔ የትግራይ ተወላጅ አይደለሁም። አቶ ጌታቸዉን ፅሁፉን ከማንበብ በስተቀር በአካልም በድምፅም ሰምቼዉ አላውቅም። አቶ አብርሃ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምንም ኢትዮጵያን ሰማይ ልክ እንደ ኢትዮ ሜድያ የህዝብ ነዉ ብለን ካመንን ለምን እንደዚህ የሰፋ ልዩነት እንደሚታይ እኔና ጓደኞቼ አይገባንም። ከምስጋና ኮፒ ለአቶ ጌታቸዉ ረዳ

የዘሐበሻ ዋና አዘጋጅ እና …

በነገዱ ኦሮሞ የሆነው፤ የዘሐበሻ ዋና አዘጋጅ ከቀኝ በኩል ኦኖጎቹን ለማብሰር ጣቶቹን የድል ምልክት የቀሰረው፤ ሔኖክ ዓለማየሁ ነው። እመሃል ያለው ወጣት ደግሞ የታወቀው ጸረ ኢትዮጵያ፤ ጸረ ምኒለክና ጸረ ቴዲ አፍሮ ዘመቻ የሚያካድ ኦነጋዊው “አብዲ ፊጤ” ነው።

ወደ ዘሐበሻው ሚዲያና ኢሳት ልመልሳችሁ እና ባጭሩ ነካክቼ ልደምድም።

ባለፈው ሰሞን ስለ ሁለት ዕውቅ ‘አትሌቶች’ ቅድመ አያቶቻችን የሞቱላት የኢትዮጵያ ሰንደቃላማችን ላይ ያሳዩት ጋጠወጣዊ ወንጀል በሰፊው መተቸቴ ይታወሳል። ከዚያም ጉዱ ካሳ በተባሉት እውቅ ጸሓፊ ስለ እኔ የዘመናት ትግል ጽናት በሚመለከት የኢትዮጵያ ሕዝብ እና ታሪክ አንዲመዘግበው የላኩትን ጽሑፍ ደብረገጾቻቻው አንዳይታተም አግደውታል። አትሌቶቹ የተቸሁበትም ሆነ ስለ በኤርትራ ውስጥ ሰንደቃላማችን መረገጥ የጻፍኩትን (የመጀመሪያ ተቺ ስለ በዓሉ እና ዝርዝር ንግግሮችን በሰፊው የገለጽኩት እኔ ብሆንም ሌሎቹ የኔን ትችት ከተመለከቱ በሗላ ሳምንት ቆይተው በየሬድዮናቸውም ሆነ በየድረገጾቻቸው ያመለከትኳቸውን ቪዲዮ እየተመለከቱ ቆይተው መተቸት ጀምረው ነበር) እነዚያ እና የመሳሰሉ ጽሁፎቼን በጥቂት ድረገፆች ሲታተሙ በኢትዮ-ሚዲያ እና በኦነግ ባንዴራ ጨፋሪው በዘሓበሻ ድረገጽ ላይ እንዳይወጣ ታግዷል። እያንዳንዶቹ ድረገፆች ምክንያቶች አሉዋቸው። ካሁን በፊት በሰፊው ገልጫለሁ አልመለስበትም። ይህ የሚዲደያዎች ባሕሪ ትግሉን ወደ አንድ አቅጣጫ እንዳይሄድና የተቃዋሚ መሪዎች እንዲስተካከሉ የሚያስተምሩ ትችቶች በ “ፓርቲዛን /ቡዱናዊነት/ ምክንያት ጠቀሜታ ላይ እንዳይውሉ ካገዱት አንዱ የነዚህ ሚዲያዎች በሽታ ነው።

ስለ እነዚህ ቡድንተኛ ሚዲያዎች ወደ ጎን ልተውና፤ የተቃዋሚው ትግል ለምን በአንድ መስመር መትመም አልቻለም? እየተባለ ብዙ ጥያቄ ሲቀርብ አመታት አልፎታል። እንደዚህ ዓይነት ጥያቄ ለሚያቀርቡ መልስ የሰጠሁበት ‘አሲምባ’ ከተባለ ፓልቶክ የሰጠሁትን ማብራርያ በኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አሁንም ተለጥፎ ስለሚገኝ ያንኑ ብታደምጡ መልሱን ታገኙታላች ። ደጋግመው የሚጠይቁ ጠያቂዎች ፤ያልተማሩትን ይቅርታ እየሰጠሁዋቸው፤ አትኩሮቴ ግን በተማሩ ‘ደደብ ሙሁራን” ብየ የምጠራቸውን ነው። እነኚህ በየፓልቶኩም ሆነ በየሕዝብ ስብሰባ አዳራሽ እየተገኙ አስተናጋጅም፤ እንግዳም በመሆን ‘ድምፅ ማጉያ ይዘው” ለምን አንድ አልሆንም? እያሉ የሚጠይቁትም ሆነ የሚደሰኩሩት በሙሉ “በግንዛቤ ጉድለት” በሽታ የሚሰቃዩ ክፍሎች ሰለሆኑ ነው። ችግሩን ካልፈተሹት መልስ ማግኘት አይቻልም።

ለ26 አመት የተከሄደበት የተግንጣይና አስገንጣይ፤ የአስመሳይ፤ አጭበርባሪና ሴረኛ፤ የደላላ፤ የወንጀለኛ እና የዋሾ ፖለቲካ ሊሂቃን የቀየስዋቸው ድርጅቶች፤ በአንድ አዝማች እና ባንድ የተቀየሰ ትግል መስመር ለመታገል አስቸጋሪ ነው። ‘የጋራ ራዕይ” “ቢያስማሙን መስመማት፤መቻቸል”” ወዘተ ወዘተ.. እያሉ አገርን በሚያፈርስ የፖለቲካ ገመድ ከሚጎትቱን አደገኛ ሊሂቃን ካልተጠነቀቅን፤ በምንመም መልኩ ከተረገረግንበት ጭቃ መውጣት አንችልም። ያንን የትም ያላደረሰ የፖለቲካ መስመር መደጋግም ትርፉ “ኪሳራ እና ለሕብ አደጋ ነው”።

ችግሩ ምንድ ነው? 100 በመባል በሚያስችል የድርጅት መሪዎችና ተከታዮች “የዲሞክራሲ እጦት ስለሆነ ዲሞክራሲ ካሰፈንን አገራችን ሰላም ይመጣል ፤አንድነታችን ይረጋገጣል ሲሉ ይደመሉ። ያ እሚንት እንጂ ዋናው መልህቁ ‘ዲሞክራሲ እጦት’ ሳይሆን ‘አገር በውስ እና በውጭ ጠላቶች ተወጥራ በመያዝዋ፤ ትግሉ ማተኮር ያለበት ለዚህ ሁሉ መከራ የዳረገን “የኢትዮጵያ ሉአላዊ መለክአምድር እና ሰንደቃላማዋ” ላይ ያለን የማያወላዳ መስመር በመልቀቃችን ነው። እነኚህ የትግላችን መፎር እና ቀምበር ናቸው። ገበሬ፤ በሬ እና ዘር፤ እነዚህ ሦስት ነገሮች ቢቀናጁም ‘ማሳ’ (መሬት) ከሌለ አርሰው ለማፍራት ያለሙትን ፍሬ ማፍራት አይችሉም። ተቃዋሚውም እንዲሁ ዲሞክራሲ የሚባለው ‘አገር ከሌለ’ ዲሞክራሲ ትርጉም የለውም። አገራችን በሃይለኛ የውስጥም የውጭም ጠላቶች ተይዛለች።ስለሆነም በሬውና ገበሬውን በምሳሌ እንመለከት።

እላይ እንደገለጽኩት ሞገደኛው በሬው በእርሻ ተጠምዶ፤ ሞፈሩን እየጎተተ ከተተለመበት መስምር ግራ ቀኝ እየወጣ/እያፈረገጠ ለቁጥጥር ሊያስቸግር ይችላል። ዋናው ነገር፤ ገበሬው ሞፈሩን አጥብቆ ካያዘ “ወዶ ሳይወድ” በሬው ወደ መሰሩ መግባቱ አይቀሬ ነው። በሬው ወዲያ ወዲህ ቢልም ሞፈረን ያለመልቀቅ የገበሬዎች ዓየነትኛ የያንዳንዱዋ ደቂቃ አትኩሮት መመሪያ ነው።

ሊሂቃኑም እንደዚሁ ናቸው። በሬዎች ናቸው። ለሕዝቡ በመራኸኝ በቃልህ በመስምርህ እጓዛለሁ ሲሉ ‘በመደስኮር’ ይምላሉ፤ ይገዘታሉ፤ በመሃላ ይመረጣሉ። ሕዝብን በመስመራቸው ይጎትታሉ። ከመስመር ውጭ ያለቁጥጥር ያሻቸውን ለማድረግ የማይመለሱ ተጠማጅ ሞገደኛ የሰው እንሰሳዎች ናቸው። እንዲህ ሲሆን ሕዝቡ ሞፈራቸውን አጥብቆ ይዞ እንዳይፎልሉ ማስቆም እና መስመር እንዲገቡ ማድረግ ነው። ከመስምር ሲወጡ ወያኔን ብቻ እናስወግድ በሚል ‘ቸል” እየተባሉ “በአንድነት” ጠላትን መታገል የሚባል የትግል መስምር ማራመድ ‘በአሸዋ ላይ ቤት መስራት ነው” ።

ተቃዋሚ መሪዎችም ሆኑ ተከታዮቻቸው አብዛኛዎቹ አገርም እውጭ አገርም ያሉት እንደ አልታረመ ሙጃ እግራቸው ስር ተጠናንጎ መረማመጃ እየከለከላቸው ያለው መሰናክል ምን እንደሆነ ሊያውቁት አልቻሉም። ከስር ሆኖ ወያኔዎችም ሆኑ ተቃዋሚዎች የሚያሰናክላቸው፤ “መሰናክላዊ ሐረግ” ዲሞክራሲ ስለታጣ ሳይሆን ከዘመነ አክሱም ጀምሮ እስከ ቀዳመዊ ሃይለስላሴ ዘመነ መንግሥት ድረስ ከቅኝ ግዛት (”ሲስተማቲክ የሆነ የቅኝ ገዢዎችን”) አለንጋ እየተጋፈጠም ሆነ እያፈገፈገ ያመለጠ ኢትዮጵያዊ ‘እሴት’ ሲረገጥ፤ እያዩ ወደ “ዲሞክራሲ” ብቻ ማትኮር ሕዝቡን በአንድ መስመር እንዲተም ማድረግ ያስችግራል። ምክንያቱም ሉዓላዊ ክብራችን መሬታችን ሰንደቃላማችን ተረግጧል የሚሉ በርካታ ወገኖች “’የዲሞክራሲ መፈክር” ቀዳሚ ጥያቄ/አጀንዳ አድርገው ስለማይመለከቱት፤ አነሱን ‘ከዲሞክራሲ ፈካሪዎች’ ሊረግጉ/አንድ ሊሆኑ አይችሉም። ለዚህ ነው ትግሉ የተወላገደው። ካሀበቃለ መጠይቅ አንደገለጽኩ ዲሞክራሲ “የሚለወጥ፤ የሚገሰስ፤ ባልተጠበቀ ውቅት በጠምንጃ ያዥ ወረበላ የሚነጠቅ፤ ፋሺስቶች፤ ናዚዎች፤ ሳይቀሩ በዲሞክራሲ መንገድ መሰላል ወጥተው ሕዝብን የሚጨፈጭፉበት “ማንም ሊነጠቀው የሚችል፤ ብዙሃን በድምጻቸው አነስተኞችን የሚጨቁኑበት አገርን ማስገንጠልና ለማፍረስ የሚያስችል የሚያመች መሳርያ ነው። ስለሆነም አስተማማኝ ያልሆነ ስርዐተ ስልት በመሆኑ፤ አገርን ሰንደቃላማን ከማትኮር/ከማክበር አኳያ እርባና ስለሌለው፤ ትግሉ ተጎትቷል።

የተቃዋሚ መሪዎች እየረገጡት ያለው የጉዞ መስምር ይህንኑ ነው። ከመስመራቸው እየወጡ መስመራቸው ከመስመራችን ጋር ከማይሄድ ቡድኖች ጋር የጋራ ትግል ለማቀናጀት እየጣሩ ነው። እነኚህም ልክ እንደወያኔ መስመራቸው ተመሳሳይነት ያለውጊዜ-እየጠበቁ ያሉ ጠላቶች ናቸው። ስለሆነም ተቃዋሚው ‘ውጭም፤ ውስጥም” የተጓዘው የትግል መስምር እየደጋገመው ከመጣ ድሉ አድብተው ላሉ ጠላቶች እንጂ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት አይሆንም። በዚህ ላይ በተቃዋሚ ድርጅቶች ውስጥም “የውጭ ጠላቶች” ተጨማሪ እጅ አስገቢነቱን ሴራ አትርሱ። አንዳንዱ በዓይናችሁ የምታየት ይመስለኛል።

ተቃዋሚው ማወቅ ያለበት ከቅድመ አያቶቻችን ተያይዞ የመጣው የተረከብነው ሰንደቃላማም ሆነ መልክአምድር ክቡርነት ሳይቀበሉ፤ አሁን ስለ ዲሞክራሲ ግንባታ እንነጋገር ስለ ሉዓላነትና ሰንደቃላማ ‘ነፃ’ ስንጣ በሕዝብ ድምፅ የሚወሰን ነው” ነፃ ስንወጣ እንነጋገርበታለን፤ ስለ ሉዓላዊነት ለመነጋገር ማንዴቱ የለንም፤ ሕዝብ ኣልወከለንም፤ የምንመራበት ሐገራዊ መመሪያ/ፖሊሲ/ የለንም፤ የጋራ ጠላት አለን ወደ እሱ እናትኩር፤ እያሉ እያሞኙዋችሁ ናቸው። ከተገንጣይ እና አስገንጣይ፤ ከሰይጣንም ጭምር ሆነን ጠላታችንን እንጥላለን ብሎ መስመር፤ አይሰራም። ስሜት እና እውነታ ለየቅል ናቸው። ለዚህ ነው 26 አመት ወያኔን ‘ባንድ ቅልጥም” መምታት ያልተቻለው። በወያኔ መስመር እና መልክዓምድር በቀየሰው ሰንደቃላማ መትመም የመሳሰሉት “የክልል፤ የነገድ ፌደራሊዝም (ፋሺስታዊ) የመገንጠል” መስመሮች ከሚከተሉት ጋር ግምባር ፈጥሮ “ወያኔን እንጥላለን” የሚለው የተቃዋሚው የትግል መስመር ተሎ ካልተወው፤ በየስብሰባው የሚጮኸው “የአንድነት” “የጥምረት” የሚባሉ ፕሮፓጋንዳዎች ከድምፅ ማጉያ ጩኸት አያልፉም።

ሰሞኑ ‘ዳዊት ወ/ዮርጊስ’ የተባለ የደርግ ባለሥልጣን እና አፍቃሬ “ሻዕቢያ” ሰሞኑን ተቃዋሚውን ሲተች “መደመጥ ያለበት ንግግር” እየተባለ በየድረገጹ ተለጥፎ አንባበችኋል። ዳዊት ስለ ዓሰብ፤ ስለ ኤርትራ ጉዳይ ያበቃለት ነው፤ ( የተባበሩት መንግሥታት ፈርመውበታል)፤ ‘ኤርትራ፤ ኤርትራ እያለ የሸተተው ጠረናችሁ ነፋሱን አትበኩሉብን” እያለ ምጽዋ፤ አልጌና ኤርትራ በረሃዎች ላይ የተሰውትን የጓዶቹን መስዋዕት እና “የአደራ ቃል” የከዳ ግለሰብ፤ የወያኔና የሻዕቢያን መስመር የሚያናፍስ፤ ለጠላት ጥብቅና የቆመ፤ ኢትዮጵያዊ ትውልድ ትጥቁን እንዲፈታ ብዙ የደከመ መሰሪ ሰው ያናፈሰው የዳዊት ሰሞኑን የስያትሉን ንግግር ‘የተጃጃለውን ማሕበረሰብ” እንደገና በአዲስ ዘዴ ለማደንዘዝ አዲስ “ድምፅ” ይዞ ብቅ ስላለ “አድምጡት” ተብለናል።

ዳዊት ተቃዋሚዎቹ “ምላሰኞች፤ ጉረኞች፤ ባዶሽ” ብቻ ከማለት፤ ተቃዋሚዎች እዛ ድረስ ሊያደርሳቸው የቻለው “ድክመት” ምክንያቱን ሊገልጽልን አልቻለም። የዳዊትም ሆነ የጓዶቹ መፍትሔ ፤ያው ኦነግን ውደዱ፤ ሻዕቢያን ውደዱ፤ የብዙ ጀግኖች ደም የገበርንበትን፤ በውስጥ ጠላቶች “በሕገ ወጥ” የተነጠቅነውን ዓሰብን ኤርትራን አትጠይቁ፤ የኤርትራና የኢትዮጵያ ሕዝብ በእነ ብርሃኑ ነጋ፤በእነ ኤፍሬም ማዴቦ፤ በነ ሌንጮና በ…. በኩል “ዲፕሎማሲያዊ ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት” ጀምሯል እና ‘አንድነት ሃይሎች’ የምትባሉ አፋችሁን ዝጉ ነው ዳዊት እንደመፈትሄ የሚያቀርበው። ይህ ደግሞ ኢሳት ላይ ካንደበቱ ያደመጥነው ነው።

ዳዊት ከጥቂት ወራት በፊት ‘የተቃዋሚው ጥንካሬ/አብሮ መቀናጀት” መጥቷል እያለ ሲያዳምቅ እንዳልነበረ ዛሬ “አዲስ ደምፅ እየተቃኘ ነው” (ያም ባልከፋ)። ‘ሆኖም፤ ዳዊት እና ጋሻ ጃግሬዎቹ እነ ጌታቸው በጋሻው፤ ካሳ ከበደ” የመሳሰሉ “ ትውልድን፤ አንድነትን የሸረሸረ ታሪክ ያስረከቡ፤ “ርሳይክልድ/ውራጅ” የሆኑ ከትግሉ መድረክ መገለል የሚገባቸው አደንቋሪዎች፤ዋሾችና አሳሳቾች ናቸው። ከኦነግ እንቁላሎች የተፈለፈሉ እባቦችን እየጎተቱልን የሚመጡ ግለሰቦች ናቸው።

“አንደነትን እያደናቀፈ ያለው ሊፈትሹት “የማይፈልጉት” ዋናው ነገር “ከ26 አመት በፊት የነበረውን በአንድ ሉአላዊ መልክዓ ምድር ኢትዮጵያና ሰንደቃላማዋ” በማስከበር መስመር (አስታውሱ፤ ቅንጅት በግሩም ሁኔታ በማኒፌስቶው አዋጅ የተቀበለው መስመር ነበር) ተቃዋሚው የነጠረ ስምምነት ካላደረገ “አንደነት/ጥምረት” ወዘተ የሚባለው ባዶ ነው፡ አይሰራም። አሁን በሚጮኹበት ባዶ ጩኸት የሚጓዙ ተቃዋሚዎች ‘ባዶ’ የሆኑ ግንዛቤ የጎደላቸው ኣጨብጫቢ ተከታዮችን በማስጨብጨብ የትም አይደርሱም። ለዚህም ነው በትግርኛው ምሳሌ “ድምፅን ቁንጭን ባዶ ቤት ይፈትው (ድምፅ እና ቁንጫ ‘ባዶ’ ቤት ይወዳሉ) የሚባለው

እውጭ አገር ያሉ ብዙዎቹ የተቃዋሚ ድረገፆች፤ እራሳቸውም ሆነ፤ እንደ እማይተች ‘ታቦት’ የሚያመልኳቸው ”በውሸት እና በወንጀል የተጨማለቁ የፖለቲካ መሪዎቻቸው” ሲተቹ/ሲወቀሱ ፤ እንደ ተቆጣች ድመት ‘ፀጉራቸውን በማቆም” ራሳቸውና መሪዎቻቸውን ለማየት የሚረዳቸውን መስተዋት ለማየት የማይፈልጉ ከወያኔ ባሕሪ ያልተናነሱ እንደሆኑ በማስረጃ በተደጋጋሚ ተጋፍጬአቸዋለሁ። ግን የሚሰሙ አይደሉም።

አግጋይ ድረገጾቻቸውም እንደዚሁ ተመሳይ መስመር የሚከተሉ ናቸው። ስለ እኔ በጎ አስተዋጽኦ ተመስጠው ስለ እኔ በጎ ጽሑፍ እየዘገቡ ለዘሐበሻም ሆነ ለኢትዮሚዲያ ሲልኩ በሕዝብ እንዳይነበብ “ይሸሽጉታል”። እኔ የምጽፋቸውንም ትችቶች ጹሑፌን ለሕዝብ እንዳይደርስ ያግዱታል። እነኚህ እነማን ናቸው? ሌላ ቀን እመለስበታለሁ “በሰፊው”! ምክንያታቸውስ ምንድ ነው? በዚህ ብዙ ተችቻለሁና ያንን መዝገብ መጎልጎል ነው። ብዙዎቹ ኦነግ መነካትን /መተቸትን/ መወንጀልን/ ማጋለጥን የማይወዱ፤ ተገንጣዮችና ጸረ ኢትዮጵያ ሃይላት የሚለቁዋቸው መናፍሖች እና ባንዴራቸውን ተቀባይነት አንዲኖረው በብረዛው ዘመቻ እጃቸው በሰፊው የሚያስገቡ እንደ ዘሐበሻ የመሳሰሉ ድረገፆችን ማሕበረሰቡ በጥሞና በጥንቃቄ ማየት አለበት። በእንዲህ የትም አይደረስም። ኢትዮጵያዊነት መረቅን በዘዴ እያስተናገዱ ኢትዮጵያዊ ያልሆነ መርዛማ ጨውን በላዩ ላይ እየጨመሩ፤ የሕዝቡን ሕሊና በመበከል (ሳብቨርስ በማድረግ) ብከላን የሚያካሂዱ ክፍሎች ናቸው። ከነዚሁ ‘በካዮች’ አንዱ ዘሐበሻ ድረገጽ ዋናው ነው።

የማንም ተገንጣይ ባንዴራ እና ጸረ ኢትዮጵያ ሃይላት የፕሮፓጋንዳ ቆሻሻ መጣያ እና አጫፋሪ የሆነው ዘሐበሻ ድረገጽ የሚዘጋጀው ከዚህ በታች ወደ ቀኝ በኩል ቆሞ ጣቱን በድል ምልክት ቀስሮ የምታዩት ፎቶግራፍ ወጣት፤ የኦሮሞው ነገድ ነው የሚባልለት “ሄኖክ አለማዮህ” የተባለ ነው።

በነገዱ ኦሮሞ የሆነው፤ የዘሐበሻ ዋና አዘጋጅ ከቀኝ በኩል ኦኖጎቹን ለማብሰር ጣቶቹን የድል ምልክት የቀሰረው፤ ሔኖክ ዓለማየሁ ነው። እመሃል ያለው ወጣት ደግሞ የታወቀው ጸረ ኢትዮጵያ፤ ጸረ ምኒለክና ጸረ ቴዲ አፍሮ ዘመቻ የሚያካድ ኦነጋዊው “አብዲ ፊጤ” ነው።

አብሮት እመሃል ያለው ጸረ ኢትዮጵያ እውቅ የግንጠላ እና የጥላቻ ሰባኪ ፤ቴዲ አፍሮን ከኮካ ኮላ ማስታወቂያና የክብር ማዕረግን በመቃወም’ “ጥቁር ሰው ምንሊክ” የሚለውን የቴዲ አፍሮ “አገራዊ” ሙዚቃን በመቃወም፤ በሺዎች የሚቆጠሩ የኦነጎችን ፌርማ በማሰባሰብ ቴዲ አፍሮን የተቃወመ የኦነጉ ፕሮፓጋንዲሰት “አብዲ ፍጤ” ነው። አብዲ ፍጤ፤ እጅግ ዘግናኝ እና ዘረኛ የሆነ ቴዲን እና አጼ ምኒልክን የሚዘልፍ ትችት እራሱ በሚያዘጋጀው ኦሮሞ ሚዲያ አዘጋጅቶ ለሕዝ ያስተላለፈ የታወቀው ጸረ ኢትዮጵያው በጥላቻ ውሃ የሚታጠብ ‘ኦነጋዊ’ ወጣት ነው። የዘሐበሻው ሄኖክ አለማዮህ ከጸረ ቴዲ አፍሮ፤ ከጸረ ምንሊክ፤ ከጸረ ኢትዮጵያ ከሆኑት ወጣቶች ጋር ማንነቱን እየነገረን ነው። የዘሐበሻ ዋናው ባለቤት ይህ ወጣት፤ የኦነግ ፕሮፓጋንዳ እያሰራጨ እና እየተካፈለ፤ አልፎም በገንጣዮች ባንዴራ እያሸበረቀ፤ ያለ ምንም መጠራጠር፤ ይሉኝታና ሓፍረት፤ ከገንጠይ ሃይላት ጋር እየተቃቀፈ የኔን ዓይነቱ “ማንንም” የማይምር ነጋሪ ብዕርን/ “warchdog/” በማገድ፤ ሕዝባችን ጠላቱ እና ወዳጁ እንዳይለይ ከሚያደርጉ ግምባር ቀደም የተቃዋሚ ሚዲያዎች ዘሓበሻ አንዱ ነው። የዘሐበሻ፤ የግንቦት 7፤ የኦነግና የሻዕቢያ ጻሐፊዎች የማስተናገድን ትስስር የጠበቀው ለምክንያት አይደለም። ዐይናችሁን አብሩ።

ሰላም እንሰንብት
ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ ሰማይ አዘጋጅ) Ethio-Semay
getachre@aol.com