ወያኔ ትግሬ ሀገራችን በወረራ ከያዘበት ቀን ጀምሮ በተለያየ ግዜ ከአማራ አካባቢ ወደ ትግራይ የወሰዳቸዉ ትልልቅ ጄኔረተሮችና ማሽነሪዎች

Print Friendly, PDF & Email

(አያለው መንበር)

የትግሬ ወያኔ መሬታችን ብቻ አይደለም የወሰደዉ፣ ሁለመናችን ነዉ። ዛሬ የአማራ አካባቢ በጨለማ እንዲኖ የተፈረደበት ገና የገቡ ቀን ነበር።

ወያኔ ትግሬ ሀገራችን በወረራ ከያዘበት ቀን ጀምሮ በተለያየ ግዜ ከአማራ አካባቢ ወደ ትግራይ የወሰዳቸዉ ትልልቅ ጄኔረተሮችና ማሽነሪዎች የታወቁት

1. የጎንደር ጄኔረተር፡

ይህ ጄኔረተር ጎንደር ከተማዉንና የጎንደር ዙሪያ ያሉ ከተሞችን ያለምንም ችግር የ24 ሰአት የመብራት አገልግሎት ይሰጥ የነበረ አሁን ዉቅሮ አካባቢ ያለ። ጄኔረተሩ የነበረበት ሰፊ ቦታ አሁንም ድረስ አዉቶ ፓርኮ የሚባለዉ የከተማዉ እመብርት ላይ ታጥሮ ይገኛል።ጄኔረተሩን አናስወስድም ያሉ ሰወች በጥይት ተደብድበዉ ሞተዋል። እንዲህም ሲል የአማራ ህዝብ ግጥም ገጥሟል

አንድ አንድ ብር አዉጡ ፎቶ እንነሳ፣
እን ደጄኔረተሩ ፋሲል ግንብ ሳይነሳ።

ከላይ ከምስሉ ጋር የምታዩት የጎንደሩ አንደኛዉ የጄኔረተር ክፍል ከ 24 አመት በፊት ዉቆሮ አካባቢ ያለች የወረዳ ከተማ ሲራገፍ

(ይህንን ጀኔሬተር በተመለከተ በክልሉ ም/ቤት ላይ እና በግልም ሀላፊዎችን በመጠየቅ ከፍተኛ ጥያቄ ያነሳ የነበረ ሰው በርካታ መረጃዎችን ይዘረዝራል)

2. የባህርዳር ጄኔረተር፡

ይህ ጄኔረተር የባህርዳር ከተማን ሙሉ ለሙሉ የመብራት ሽፋን ይሰጥ የነበረ ሲሆን በጠመንጃ አፈሙዝ ነቅለዉ ወደ ትግራይ ወስደዉታል

3. ፓዊ ጄኔረተር።

በድሮዉ ጎጃም ክፍለሀገር አሁን በቤንሻንጉል አካባቢ የሚገኝ ተልቅ የንግድ ከተማ ሲሆን የነበረዉን ጄኔረተር እንደዚሁ ህዝብ አስፈራርተዉ በጨለማ ወሰዱት

4. የመርሀ ቤቴ ጄኔረተር (ሰሜን ሸዋ)።

ይህ አንድ ወረዳ ያበራ የነበር ጄኔረተር ሜንሽን ፎር ሜንሽን በተባለ የጀርመን ግብረ ሰናይ ድርጅት ከጀርመን ተገዝቶ ለአካባቢዉ ጥቅም ይሰጥ የነበረ ሲሆን። ህብረተሰቡ ሳያይ በሌሊት ነቃቅለዉ ወስዱት

5. ግምጃ ቤት አካባቢ እንደዚሁ አንድ ወረዳ ያንቀሳቅስ የነበረ ጄኔረተር ተነቅሎ ወደ ትግራይ ተወስደ

6. አዲስ አባባ እጅግ ዘመናዊና ትልቅ የዳቦ መጋገሪያ ማሽን ለአንድ ሚሊየን የአዲስ አባባ ህዝብ አገልግሎት ይሰጥ የነበር ማሽን ተነቅሎ ወመቀሌ ተወሰደ

7. ደብረማርቆስ እንደዚሁ በአይነቱና በመጠኑ እጅግ ዘመናዊ የነበረ የድንጋይ መፍጫ ማሽን ተነቅሎ ወደ አዲግራት ተወሰደ