ቅዳሜ እለት 5 August 2017 ጀርመን ፍራንክፈርት ላይ በሚደረገው ስብሰባ ላይ የንግግር ርዕስና ይዘት —› በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ያለው መንግስታዊ ስርዓት ባህርይ ልማታዊ ነው ወይስ ፋሽስታዊ? ያሉብን የግንዛቤ ክፍተቶች ምን ይመስላሉ? የወደፊቱ የትግል አቅጣጫስ ምን ይሁን?

Print Friendly, PDF & Email

ተጋባዥ እንግዳ —–› ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ (ከሆላንድ)

ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ

ባለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት በኢትዮጵያ የተቋቋመው መንግስታዊ ስርዓት በተቃዋሚዎችም ሆኑ በአደባባይ ምሁራኖቻችን የተለያዩ ስያሜዎች ሲሰጡት ቆይቷል። አንዳንዶች የወያኔን መንግስት ጎሰኛ ነው ሲሉት፤ ሌሎች ደግሞ ስታሊናዊ ፤ ሌሎች ደግሞ ኮሚኒስት እንደዚሁም የቀድሞዋ ሶሻሊስት የአልባንያ ቅጂ ነው ብለውታል። አንዳንድ ምሁራን ደግሞ ልማታዊ፤ እንደዚሁም የተቀሩት አምባገነን ስርዓት ነው ወዘተ እያሉ ገልጸውታል። በዚህ ስርዓት የሚሰቃየው ተራው ህዝብ ደግሞ ወያኔዎችን በሰይጣንነትም ጭምር ይመስላቸዋል። የዚህ መንግስት ተፈጥሮና ባህርይ ምንድነው? አነሳሱስ? ፓሊሲዎቹስ ምን ይመስላሉ? እነዚህ ፓሊሲዎች ማንን ተጠቃሚ አደረጉ? ማንንስ ጎዱ?የሚሉትንና ተዛማጅ ጉዳዮች ይነሳሉ። ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ የወያኔን ስርዓት በአክራሪ የትግራይ ብሄረተኛነት የማእዘን ራስ ላይ የቆመ የፋሽስት ስርዓት ነው የሚለው ድምዳሜ ላይ እንዲደርሱ ያደረጓቸውን ምክንያቶች ይገልጹልናል።

ፋሽዝም በአንድ ምርጥ ህዝብ እጅግ የተጋነነ ማንነት የማዕዘን ራስ ላይ የቆመና የዚህን ምርጥ ህዝብ የበላይነት የሚሰብክ የአክራሪ ብሄረተኛነት ፍልስፍና ነው። የፋሽዝም ዓላማ የአንድን ምርጥ ህዝብ ዳግም ልደት (rebirth) በማብስር ምርጡን ህዝብ በአዲስ የሞራል እሴቶች አንፅዖ የአዲስ የሰዎች ማህበረሰብ መፍጠር ነው። እኚህ ተጋባዥ የወያኔ ትግሬዎች ባለፉት አርባ ሶስት ዓመታት አክራሪ-ብሄረኛነትን የሚያቀነቅን፤ የትግራይን ህዝብ ማንነት እንደ ሃይማኖት የሚያመልክና በማናቸውም መለኪያ ከኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ታሪክ፤ ብሄራዊ እሴቶች፤ ስነ ምግባር ወዘተ በተጻራሪነት የቆመ ማህበረሰብ በትግራይ ውስጥ ፈጥረዋል ብለው ይሞግታሉ።በዚህ ነባሩን ማህበረሰብና እሴቶቹን አፍርሶ በአዲስ የመተካት እምነታቸው የትግራይ ፋሽስቶች የኢትዮጵያን ህብረተሰብ ነባር ታሪክ፤ እሴቶች፤ብሄራዊ ተቋሞች፤ ባህል፤ እምነት፤ ወዘተ ስር-ነቀል በሆነ መልክ አጥፍተው ራሳቸው በፈጠሯቸው አክራሪ ብሄረተኛነትን በሚያንጸባርቁ አዳዲስ ተቋማትና እሴቶች ተክተዋቸዋል ብለውም ተጋባዡ እንግዳ ይሞግታሉ።

ፋሽዝም የአንድን ምርጥ ህዝብ ወይም ጎሳ የተጋነነ ማንነት በአምልኮ መልክ በማሳደግ የሚታወቅ የፓለቲካዊ ኃይማኖት እንደ መሆኑ መጠን ይህ ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ገኖ የምናየው የፋሽስት ስርዓት የዛሬ አርባ ሶስት ዓመታት ችግኙ በትግራይ ደደቢት ላይ በጥቂት የትግራይ ተወላጆች የተተከለው የትግራይ ብሄረተኛነት መራራ ተክል ፍሬ መሆኑን ተጋባዡ እንግዳ ያስረዳሉ። ይህ በማናቸውም መለኪያ ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነና በፋሽስታዊ እምነት ላይ ተመስርቶ አዲሲቷንና ታላቋን ትግራይን ከትግራይ በታች በሚኖረው 94% በሚሆነው ትግርኛ-ተናጋሪ ባልሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ አጥንት ደምና እንባ እየገነባ ያለው የወያኔዎች ትግራይ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ የትግራይ ተወላጆችን ብቸኛ ተጠቃሚ ያደረገ የአፓርታይድ ስርዓትን መስርቷል ብለውም ተጋባዡ እንግዳ ይሞግታሉ። እኚህ ተጋባዥ እንግዳ ማህበራዊ ምንድስና (social engineering)፤ ተስፋፊነት (expansionism)፤ ጠበኛነት (violence)፤ ተንኳሽነት፤ እንደ ሰደድ እሳት እየተስፋፋ ያሉት ከልክ ያለፈ በትግራይ ተወላጆች ላይ የሚታዩ የእብሪት (hubris)፤የማንአህሎኝነት (chauvinism) ስሜቶች ወዘተ የፋሽስት ስርዓት መገለጫዎች መሆናቸውንም ያስረዳሉ። የወያኔ ትግሬዎች እንደ ጠላት በሚያዩት ትግርኛ-ተናጋሪ ባልሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየፈጸᎀዋቸው ያሉት ከኢትዮጵያ ባህል የወጡ አጸያፊ ድርጊቶች (በቅርቡ በዋልድባ ገዳም ሴት መነኮሳት ላይ ወያኔዎች የፈጸሙት ወሲባዊ ጥቃት፤ በእስር ላይ በሚገኙ የወንድ እስረኞች ላይ የሚፈጸሙ ግብረ-ሰዶማዊ ጥቃቶች ወዘተ፤ በወልቃይት፤ ጸገዴ፤ ጸለምት፤ ሁመራ የአማራን ዘር ለማጥፋትና የአማራን ህዝብ የወል ማንነት ለማዋረድ በእቅድ ተወጥነው በአማራ ሴቶች ላይ የሚካሄዱ የወሲብ ጥቃቶች፤ እንደዚሁም ሽብርተኞችን እንዋጋለን በሚል ስም በኦጋዴን በሶማሌ ሴቶች ላይ የሚፈጸሙ የወሲብ ጥቃቶች የዚህ በአዲሱ የፓለቲካ ሃይማኖትና ፍልስፍና የሚመራው ፋሽስታዊ ስርዓት እሴቶች አካል ናቸው በማለት ዶክተር አሰፋ መረጃን ተንተርሰውና ነቃሽ አስረጅዎችን በማቅረብ ይሞግታሉ።

በመጨረሻም የተቃዋሚ ኃይሎች የዚህን ስርዓት ፋሽስታዊ ባህርያት በውል ለመገንዘብ አለመቻል በተደጋጋሚ ወቅቶች እንዲዘናጉ እንዳደረጋቸውና፤ በስራቸው ያሰለፉትንም የኢትዮጵያ ህዝብ በበቀለኛው የወያኔ ትግሬዎች መንግስት እጅ ብዙ የህይወት ዋጋ እንዲከፍል እንዳደረገ የቅርቡን የቅንጅትን ውድቀት በምሳሌነት በመጥቀስ ያስረዳሉ። የወያኔን ፋሽስታዊ ስርዓት ነቅሎ ለመጣል ለምን የዚህን ፋሽስት ስርዓት ተፈጥሮና ባህርይ ማወቅ ግድ እንዲሚለንና የወያኔን ዘመን ፍጻሜ ለማምጣት ምን መደረግ እንዳለበት የግል ምልከታችውን ያካፍሉናል። እርስዎ በስብሰባው ላይ ተገኝተው ስብሰባውን ይከታተሉ ዘንድ፤ የእኚህን ተጋባዥ እንግዳ ሃሳብም በአካል ተገኝተው መስማት ብቻ ሳይሆን ፊት ለፊት ይሞግቷቸውና ይከራከሯቸው ዘንድ በትህትና እንጋብዝዎታለን።

ስብሰባው የሚካሄድበት ቀን —› ቅዳሜ እለት 5 August 2017
ስብሰባው የሚጀመርበት ሰዓት —› ከቀኑ 12፡00 ጀምሮ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር
የስብሰባ ቦታና አድራሻ ——-›

SAALBAU Nidda (Bonames)
Harheimer Weg 18 – 22
60437 Frankfurt am Main