የፍፃሜው ጦርነት ነው፤ ሁሉም ዐማራ ዘብ ይቁም ለኅልውናው!! – ዐኅኢአድ

Print Friendly, PDF & Email

የፍፃሜው ጦርነት ነው፤ ሁሉም ዐማራ ዘብ ይቁም ለኅልውናው!! (pdf)

 ሀምሌ 2 ቀን 2009 ዓ.ም    ቅጽ 1 ቁጥር 4

         “የምኖርበትን ቤት ለምን ያቃጥሉብኛል?”  ህፃን ዩሓን ዮሐንስ

ረቡዕ ሰኔ 7 ቀን 2009 ዓ.ም የብዙ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው በለንደን ሰዓት አቆጣጠር ከሌሊቱ 1 ሰዓት ላይ በለንደኑ ግሬንፌል ሰማይ ጠቀስ ሕንፃ (Grenfell Towers) ላይ የእሳት ቃጠሎ ተነስቶ በለንደን ታሪክ እጅግ አስቃቂ የተባለ አደጋ አደረሰ። በዚህ የእሣት አደጋ በጣም የደነገጠችውና ግራ የገባት ጨቅላ ህፃን ዩሓን ዮሐንስ “የምኖርበትን ቤት ለምን ያቃጥሉብኛል?” በማለት የእምባ ሳግ እየተናነቃት ፊት ለፊት የከበቧትን የለንደን ነዋሪዎችና ጋዜጠኞች ጠየቀች። ዩሓን ዮሐንስ አከታትላም ከምትኖርበት ሕንፃ መቃጠል ጋር በተየያዘ የደረሰባት ከፍተኛ የአዕምሮ መረበሽና ጭንቀት ሳያግዳት፣ የምትወደውን እርሳስና ወረቀት አንስታ ሁሉንም ባስደመመ መልኩ አሰቃቂውን ቃጠሎ በሥዕላዊ መግልጫ መልክ ለጋዜጠኞች አቀረበችላቸው። ጋዜጠኞችም የጨቅላዋን የአዕምሮ መረበሽና ተሰጥዖ ጭምር የሚያሳየውን ሥዕሏንና ጥያቄዋን በመገረም ተቀብለው የጋዜጣቸው የግርጌ ማሳታዎሻ አደረጉት::

በዚህ አጋጣሚ ለዩሓን ዮሐንስ የአዕምሮ መረጋጋቱንና እንዲሁም በእሳት ቃጠሎው ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ወገኖች ደግሞ መጽናናቱን እግዚአብሔር እንዲሰጥልን እየተመኘን፣ የዚህ ጽሑፍ ዋና ዓላማ ግን በድንገተኛ አደጋ ምክንያት ስለተቃጠለው የግሬንፌል ሕንፃና እርሱን ተከትሎ ስለታየው የጨቅላ ዩሓን አስደማሚ ሁኔታ ለመዘገብ ሳይሆን ከዚህ እጅግ ስለከፋና ሆን ተብሎ ስለተፈፀመ አሰቃቂ እልቂት ለማውሳት ነው። አዎ! ግሬንፌል ሕንፃ ላይ የደረሰው አደጋ የሚያሳዝን ቢሆንም ዘርና ቀለም ሳይለይ በማንም ላይ የደረሰና ሆን ተብሎ ያልተፈፀመ ድንገተኛ አደጋ ነው።

በተቃራኒው ሕፃን ዩሓን ያላወቀችዉ ጉድ በኢትዮጵያ ተፈፅሟል፤ እስከ አሁኗ ሰዓትና ደቂቃም በመፈፀምም ላይ ነው። በኅዳር ወር 1993 ዓ.ም. ምሥራቅ ወለጋ ውስጥ የዩሓን የዕድሜ እኩያ ወይም ከእርሷ ያነሱ ሕፃናት ከዐማራ ቤተሰብ በመወለዳቸው ብቻ በወያኔ ትዕዛዝ በኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ካድሬዎችና ወታደሮች ከቤተሰቦቻቸው ጋር ቤት ተዘግቶባቸው መቃጠላቸውን ብንነግራት ዩሓን ምን ያህል ታምነን ይሆን? ይህ ብቻ አይደልም፤ ከዚህም የበለጠ ዘግናኝና አረመኔያዊ ድርጊት ተፈፅሟል እንጅ።

ተዝግቶ ከሚቃጠለው ቤት ያመለጡ የዩሓን የዕድሜ እኩዮች ወይም የበታቾች፣ በተአምር ከሚቃጠለው ቤት አምልጠው ሲሮጡ፣ ዙሪያውን ከብበው የነበሩት ካድሬዎች እያነቁ ከሚነደው እሣት መልሰው በመጨመር አንድደዋቸዋል። ይህ ልብወልድ ሳይሆን በዛሬይቱ ኢትዮጵያ በዐማራው ቤተሰብና ሕጻናት ላይ ዐማራ ሆነው በመወለዳቸው ብቻ የተፈፀመና እየተፈፀመ ያለ እጅግ ዝግናኝ ዕውነታ ነው። የምሥራቅ ወለጋውን እንደምሳሌ አነሳነው እንጅ ይህ በዐማራው ላይ በወያኔዎችና በጀሌዎቻቸው እየተፈፀመ ያለው ኢ-ሰብአዊና እጅግ ሰቅጣጭ ድርጊት በየትኛውም ቦታ እስከአሁኗ ሰዓት ድረስ በዐማራው ነገድ ላይ እየተፈፀመብት ነው። በንፁህ ኅሊናው ለሚፈርድ ሰው ይህ በዩሓን እና በመሰሎቿ በግሬንፊል ሕንፃ ላይ የደረሰው ድንገተኛ የእሣት ቃጠሎ ኢትዮጵያ ውስጥ ዐማራ በመሆናቸው ብቻ እየተዘጋባቸው ከሚቃጠሉት ጋር በማንኛውም መሥፈርት ፍፁም ሊወዳደር አይችልም።

ይህን መሰሉ ዘግናኝ የዘር ማጥፋት ድርጊት ወያኔዎች መፈፀም የጀመሩት ገና በ1972 ተከዜን ተሻግረው ወልቃይትና አካባቢው እግራቸው ከረገጠ ጊዜ ጀምሮ ነው። ጉዳዩ የመከረኛውና የወዳጅ – አልባው የዐማራ ሕዝብ ጉዳይ በመሆኑ አስታዋሽ አጣ እንጅ፣ ወያኔዎች በዐማራውና በተልይም በወልቃይት ሕዝብ የፈፀሙት የዘር ፍጅት ሂትለር አውሮፓ ውስጥ ይኖሩ በነበሩ የአይሁድ ተዋሎጆች ላይ እ.አ.አ. ከ1933-1945 ድረስ ከፈፀመው የዘር ፍጅት የማይተናነስ ነው። ሂትለር አይሁዶቸን በመርዝ ጭስ ፈጅቶ ሳሙና እንደሠራባቸው ሁሉ ወያኔዎችም የወልቃይትን ዐማራዎች ጉድጓድ ውስጥ ቀብረው እየተሉ እንዲሞቱ፣ አለበለዚያም እዚያው ጉድጓድ ውስጥ በጭስ አፍነው ከገደሏቸው ብኋላ አቃጥለዋቸዋል። የተከመረውንም አጥንትና አመድ “የትግራይን መሬት የምናለማበት ማደባሪያ ነው” እያሉ ግፍን ሳይፈሩ ተመፃድቀዋል። ሂትለር ከአይሁዶች ሰውነት ሣሙና ሲሠራ፣ ወያኔ ደግሞ ዐማራን አቃጥሎ ለትግራይ ምድር ማደበሪያ አደርገዋልሁ አለ።

ታዲያ በዚህ ዓይነት ሂትለርና ውያኔ ልዩነት አላቸው? በፍፁም የላቸውም። ይሁንና በጨካኝ ዘረኞች የዘር ፍጅት የተፈፀመባቸው አይሁድና ዐማራ ግን ልዩነት አላቸው። በዘራቸው ላይ ሂትለር የዘር ፍጅት በመፈፀሙ ውስጣቸው የተነካው በዐልም ዙሪያ ያሉ አይሁዶች ሁሉ እንደ አንድ ሰው በአንድነት በመነሳትና በመተባበር እንዲህ ኢሰብአዊ በሆነ መልኩ ዘራቸውን ያጠፋውን የናዚ አባል የሆነውን ሁሉ እየተከታተሉ ለፍርድ አቅርበው ተበቅለውታል።  የእኛ ዐማራ ግን እንደ አይሁዶቹ አንድ ሆኖ በመቆም ጠላቱን ሊበቀልና ለፍርድ ሊያቀርብ ቀርቶ፣ ችግሩ ቀድሞ ገብቷቸው በዐማራነት ለመደራጀት የሚሞክሩትን “ዐማራ መደራጀት የለበትም” በማለት ከማንም ቀድሞ እንቅፋት ይሆንበቸዋል።

የዐማራው እልቂት የጀመረው ወያኔ ደርግን ጥሎ ምኒልክ ቤተመንግሥት ከገባ ከ1983 ጀምሮ ሳይሆን ከላይ እንደተጠቀሰው ወልቃይትን ከረገጠበት ከ1972 ዓ.ም. ጅምሮ ሲሆን በአሶሣ በኩል ደግሞ ከ1982 ጀምሮ ነው። በኦነግ መሪነት፣ በወያኔና ሻቢያ ተባባሪነት (ሱዳንን ባሳተፈ መልኩ) አሶሣ ወስጥ በጥር ወር 1982 ዓ.ም. ከ300 በላይ የሚሆኑ ዐማራዎች ተልይተው ሕፃናት፣ ሴቶች፣ እመጫቶች፣ ወጣቶች፣ ወንዶችና አረጋውያን በአንድ ላይ ተረሽነዋል፤ ትምህርት ቤት ወስጥ ተቆልፎባቸው በእሣት ጋይተዋል። ይህ ዐማራን የማጥፋቱ ሥራ ወያኔ ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላም በመላ ሀገሪቱ እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ በስፋትና በተጠናከረ ሁኔታ ቀጥሏል። በወገኖቻችን ላይ ይህ አሰቃቂ የግፍ ጨፍጨፋ የተደረገባቸውና እየተደርገባቸው ያለው ምንም ወንጀል ሠርተው ሳይሆን ዐማራ ሆነው በመወለዳቸው ብቻ ነው። በለየላቸው ዘረኞች ዐማራን ነጥሎ የሚደረገው የዚህ ዓይነቱ አረመኔያዊ ጭፍጨፋና የእሣት ቃጠሎ እኛን የግፉ ሰለባ የሆነውን የዐማራ ተወላጆች ዛሬም ድረስ እሣቱ ትኩስ ሆኖ እየፈጀን መሆኑን ዓለም እንዲያውቅልን እንሻለን!  ይህንን አረመኒያዊ የዘር ፍጅት የፈፀሙት ግለሰቦችም ሆኑ ቡድኖች ለፍርድ ቀርበው ተገቢ ቅጣታቸውን እስኪያገኙ ድረስም ፈፅሞ እርፈት አይኖረንም።

ወደ ተነሳንበት ርዕስ እንምጣና እንሆ ባለፈው ዓመት፣ ሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ከወሰደው የኅልውናና ሕጋዊ ራስን የመከላከል እርምጃ ጋር በተየያዘ በጎንደርና በጎጃም በሚገኙ የዐማራ ነገድ ተወላጅ ወገኖቻችን ላይ የማያባራ እሣት እየነደደ ነው። በዚህ ኢሰብአዊ  ጭፍጨፋ ያልረካው ናዚው የትግሬ የወያኔ ቡድን አሁን ደግሞ የኅልውናና የማንነት ጥያቄን ላነሳው ሕዝብ እየሰጠ ያለው ምላሽ ፍትሃዊ ምላሽ ሳይሆን፣ ልክ ጠላት የሆነ ሌላ ሀገርን እንደሚወር ሁሉ በከባድ መሣሪያ ሳይቀር ሙሉ የሀገር መከላከያ ኃይሉን እስከአፍንጫው አስታጥቆ መላ ጎንደርን በማንደድ ነው። አዎ፣ ለጊዜው የጎንደርን ያክል አይሁን እንጅ የጎጃም ወገናችንም የዚሁ እልቂት ገፈት ቀማሽ ነው። መሠሪው ወያኔ የጎንደርን ዐማራ ለዘር እንዳይተርፍ ካደረገ በኋላ የቋጠረውን ቂም እንደያዘ ወደ ጎጃም ሕዝብ በሙሉ ኃይሉ እንደሚመለሰ ሳይታለም የተፈታ ነው።

ከዚያ ወሎና ሸዋ ተራ በተራ የናዚውን የዕልቂት ፅዋ ይጎነጫሉ። በአራቱ ከፈለ ሀገራትም ሆነ በየትም ያለው ዐማራ ሁሉ የወያኔውን እኩይ ዓላማ በመረዳት ሁሉም በያለበት መነሳትና ራሱን ከጥፋት መከላከል ለነገ የማይለው የኅልውና ግዴታው ነው። ወያኔ ገና ከጥዋቱ ዓልሞ የተንሳው የዐማራን ዘር ለማጥፋት እንጅ ጎንድርን ወይም ጎጃምን ብቻ ለይቶ ለማጥፋት አይደለም።  አሁን ጎንደር ተነጥሎ ሲመታ ሌላው ዐማራ “እኔ ልተርፍ እችል ይሆናል” ብሎ እጁን አጣጥፎና አፉን ለጉሞ ከተቀመጠ ልክ “የገናው በሬ ሲታረድ፣ የፋሲካው በሬ ሣር ይግጣል” እንደሚሉት መሆኑን በእርግጠኝነት ልንነግረው እንወዳለን። ልክ እንደገናውና የፋሲካው በሬዎች የጊዜ ቅደም – ተከተል ጉዳይ እንጅ ሁሉም አይቀርለትም። ስለዚህ ናዚው ወያኔ አንድ በአንድ ነጣጥሎ ሳያጠፋን በፊት ዛሬውኑ በያለንበት ሆ ብለን እንነሳ።

ሌላው ደግሞ ይህን በወገን ላይ የሚፈፀምን የዘር እልቂት እያዩ ያሉ የአገር ውስጥ ታማኝ ተቃዋሚ ተብዬዎችም ሆኑ በውጭ ሀገር ያለው ተቆርቋሪ ኢትዮጵያውያን ወገኖች በጎንደር ወገኖቻችን ላይ የናዚው ትግሬ ወያኔ ጦር የገበሬውን ቤት በከባድ መሣሪያ እያቃጠለና ሕዝቡንም ሕፃን፣ ሽማግሌ፣ ሴትና ወንድ ሳይል በመደዳ ሲጨፈጭፍ እንደወገን ተቃውሟቸውን በማሰማት ፋንታ ዝምታን መርጠዋል። አንዳንዶቹማ እንዲያውም “ላም ባልዋለበት፣ ኩበት ለቀማ” እንደሚባለው አንድ እንኳን ወታደር ባላሰለፉት የጦር አውድማ ላይ ጥይት በጮኸ ቁጥር “የእኛ ጦር ነው” እያሉ በዐማራው ገበሬ ደም እየነገዱበት ነው። እንዲህ ያለውን ለከት የለሽ ድርጊት የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (ዐኅኢአድ) ከምር ያወግዘዋል! ምክንያቱም ባልዋሉበት የጦር ሜዳ የዐማራውን ድል መቀማት አሳፋሪ ከመሆኑም በላይ፣ ዐማራውን ሆን ብሎ ለማስጨረስ የተሸረበ ሤራ እንደሆነ አድርጎም ስለሚቆጥረው ነው።
ግንቦት 7 በጎንደርና በጎጃም ወታደር ሳይሆን ያለው፣ ከሕዝብ በሚሰበሰብ ገንዘብ ደመወዝ ተከፋይ የሆኑ ወሬ አቀባዮች ብቻ ነው። እነዚህ የኢሣት የመሥመር ወሬ አቀባዮች የሚያቀበሉትን ዜና ደግሞ ናዚው የትግሬ ወያኔ ቡድን በሁለት ዐበይት ምክንያቶች እጅግ በጣም ይፈልገዋል::

የመጀመሪያውና ዋናው ምክንያት በጎንደርና በጎጃም እየተካሄደ ያለውን የዐማራ ኅልውናን የማዳን ሕዝባዊ ትግል ወያኔ “የሻዕቢያ ተላላኪ” ብሎ በፈረጀው ግንቦት 7 እየተካሄደ ያለ የሽብር ድርጊት እንጅ የዐማራን ኅልውና ለመታደግ እየተደረገ ያለ ሕዝባዊ ትግል መሆኑን ለማዳፈን ይጠቅምበታል። ይህም የጥያቄውን አቅጣጫ በማስቀየሩና ጭራሹንም ግንቦት 7 በሚያቀርበው “የኔ ትግል ነው” ጥያቄ ምክንያት ሁሉም የዐማራው ነገድ ተወላጆች “የእኛ ትግል ነው” በማለት በአንድ ጊዜ ሆ! ብለው እንዳይነሱበት  ረድቶታል። ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ወያኔ የዐማራ ነገድ ተወላጆችን እንደፈለገ ለመግደልና ለማስር በአሸባሪነት የፈረጀውን የግንቦት 7ን “ትግሉ የኔ ነው” ጥያቄ በደንብ ተጠቅሞበታል። ለዚህም ነው ግንቦት 7 “ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ” እየሄደ ለወያኔ ጥይት እያቀበለ “ለኅልውና” እየተደረገ ያለውን ትግልና ወገናችንን በጅምላ ደርቦ እያስመታ ነው ብሎ ዐኅኢአድ በጽኑ የሚያወግዘው!! ግንቦት 7 ይህን መሰሉን ደባ በዐማራው ሕዝብ ላይ ከመፈፀሙም በላይ በአባላቱ አማክኝነት በግልፅም ሆነ በሥውር “ዐማራው መደራጀት የለበትም” እያለ ደጋግሞ መዝመቱንም አኅኢአድ ያወግዛል።

በመሠረቱ በመርህ ደረጃ የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ከግንቦት 7 ጋር ምንም ዓይነት ጠብ የለውም። ግንቦት 7 ዕውን ተዋጊ ሠራዊት “አለኝ” በሚላቸው ቦታዎች ሁሉ ሠራዊት ኖሮት ቢዋጋና ሕዝባችን ላይ የሚወርደውን ፍላፃ ለመመከት ሙከራ ቢያደርግ “እሰየው” ብለን ከጎኑ በቆምን ነበር። ባለመታደል ግን ባልተገኘበት የጦር አውድማ ሁሉ በአፈጮሌነት የዐማራውን ድል እየነጠቀ በእርሱ ስም የዐማራው ገበሬ በፋሺስቱ ወያኔ ያለምንም ርህራሄ እንዲጨፈጨፍ ማድረጉ በጣም እያሳዘነን ነው። ይበልጥ የሚያሳዝነው ደግሞ ወያኔ ወገናችንን መጨፍጨፉ ብቻ ሳይሆን ነገ ከነገ ወዲያ እንኳን ለፍርድ እንዳይቀርብ ግንቦት 7 የሕግ ከለላ እየሰጠው መሆኑ ነው። ምክንያቱም ምንም እንኳን የወያኔን አሻንጉሊት ፓርላማ እኛ ተቃዋሚዎች ባንቀበለውም፣ ግንቦት 7ን “አሸባሪ ድርጅት” ብሎ ፈርጆታል። ይህ “አሸባሪ” የተባለ ድርጅት ደግሞ ባልዋለበት የጦር ሜዳ ዋልኩ እያለ ወያኔ “አሸባሪውን ድርጅት መታሁ” እያለ ምስኪኑን የዐማራ ገበሬ ያለምንም ረህራሄ እንዲጨፈጭፍ መንገድ ከፍቶለታል። ይህ ደርጊት ደግሞ ባለማወቅ ተደርጓል ብለን አናምንም። ስለዚህ ግንቦት 7 ከእንዲህ ዓይነቱ እኩይ ድርጊት እንዲቆጠብ እንጠይቃለን።

ግንቦት 7 እንደሚለው ዕውን ከልቡ ለኢትዮጵያ አንድነት የቆመ ቢሆን ኖሮ በአንድነቱ የማያወላውለውን የዐማራ ነገድ አግልሎ “ኢትዮጵያ ቅኝ ገዣችን ናት” ከሚሉት ጋር ጥምረት እየፈጠረ ሽር-ጉድ ባላለ ነበር። ነገሩ “ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን እነግርሃለሁ” እንደሚባለው ሁሉ እኛም ግንቦት 7 ጥምረት ከነማን ጋር እየፈጠረ እንደሆነ አየንና ማንነቱን አወቅን። በመሆኑም ለግንቦት 7 ተገንጣይ ጓደኞችህን ጠበቅ፣ ዐማራውን ለቀቅ አድርግ ልንለው ተገደድን።
ይህንን ካልን በኋላ በዐማራ ስም ለተደራጁ ድርጅቶችና ለመላው የዐማራ ሕዝብ ጥሪ ማስተላለፍ ፈለግን።

1/ በዐማራ ስምም ሆነ በክፍላተ – ሀገራት ለተደራጃችሁ በሙሉ!

ፋሺስቱ ወያኔ የዛሬ 42 ዓመት ሲቋቋም ምንም ያላደረገውን የዐማራ ሕዝብ “ዐማራ ጠላቴ ነውና ማጥፋት አለብኝ” ብሎ ነው የትግል ፕሮግራም ነድፎ ጫካ የገባው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ልክ የዛሬ ዓመት እነኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ለኅልውናቸው ሲሉ ባልሞት ባያ ተጋዳይነት እስከተኮሷት ራስን የመከላከል ጥይት ድረስ ዐማራው ዝም ብሎ ሲታረድ ነበር የኖረው። ከሃምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ግን ዐማራው በሙሉ ኃይሉም ባይሆን በአንዳንድ ቦታዎች (በተለይ በጎንደርና በጎጃም) ራሱን መከላከል በመጀመሩ ወያኔው ዐማራው ተደራጅቶ ቢነሳ ምን ዓይነት ኃይል ሊሆን እንደሚችል ትምህርት አግኝቶበታል። በመሆኑም ይህንን መሰሉን ኃይል “ሳይቃጠል በቅጠል” እንዲሉ ሳይደራጅ ነጣጥሎ እያጠፋው ነው።

እያንዳንዱ በዐማራና በክፍለሀገር ደረጃ የተደራጀ የዐማራ ስብስብ ከተደራጀንበት ርዕዮተ ዓልም በፊት ኅልውና ይቀድማልና ኅልውናው ፍፁም አደጋ ላይ ያለው ወገናችን በፋሺስቱ ወያኔ ጨርሶ ከመጥፋቱ በፊት በማንኛውም መልኩ ተባብረን እንድንታደግው (ዐኅኢአድ) ክልብ ጥሪ ያቀርባል። ይህንን ጊዜ የማይሰጠው የኅልውና ትግል ለማስተባበር አንድ የጋራ ግበር – ኃይል በአስቸኳይ አቋቁመን የወገናችንን ኅልውና እንድንታደግ በፋሺስቱ ወያኔ በግፍ በሚጨፈጨፈው የዐማራ ወገናችን ስም እንጠይቃለን።  ኅልውናችን በአስተማማኝ ሁኔታ ካስጠብቅን በኋላ ብንስማማ የጋራ ግብረ – ኃይሉን ይበልጥ አጠናክረን አብረን እንቀጥላለን፤ ካልተስማማን ደግሞ የየራሳችን የትግል መሥመር ተከትለንና ከጎንዮሽ ትግል ታቅበን በየመረጥነው መሥመር መጓዝ እንችላለን።

2/ በጎንደር፣ በጎጃም፣ በወሎ፣ በሸዋ፣ በአዲስ አበባ፣ እንዲሁም በተለያዩ ክፍላተሀገራትና በውጭ ሀገራት ላለው መላው የዐማራ ሕዝብ!

ፋሺስቱ ወያኔ አንተን አጥፍቶ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ምን ያህል እየሠራ እንደሆነ ከትናንት ዛሬ ይበልጥ ግልፅ የሆነልህ ይመስለናል። እኛም አምርረን የምንነግርህ ናዚው ወያኔ የዐማራን ዘር ከምድረ-ገጽ ሳያጠፋ እንቅልፍ እንደማይተኛ ነው። ይህንን ደግሞ እኛ ሳንሆን የምንነግርህ ፋሺስቱ ወያኔ ራሱ በ1968 ዓ.ም. ባወጣው የድርጅት መመሪያ (ማኒፌስቶ) “ዐማራ ካልጠፋ ትግራይ ማኅበራዊ እረፍት አታገኝም” ብሎ አውጇል። በዚህ መመሪያው መሠረትም እስከአሁን በጥቂቱ ከ6 ሚሊዮን በላይ ዐማራ ከምድረ ገጽ አጥፍቷል። ዐማራ ሴቶች ዘራቸውን እንዳይተኩ እንዲመክኑ ሲደረጉ፣ ወንዶች ደግሞ በሰበብ አስባቡ በታሠሩ ቁጥር ብልታቸው እየተቀጠቀጠ እንዲመክኑ ተደርገዋል። ቤት እየተዘጋባቸው ተቃጥለዋል፤ ከነሕይዎታቸውም ገደል ተጥለዋል። መናኝ መነኮሣት ሳይቀሩ በዐማራነታቸው እየተመረጡ በአፀያፊ ሁኔታ በትግሬ ኮርማዎች ተደፍረዋል፤ ከገዳምም ተባረዋል። በአጠቃልይ ባለፉት 40 ዓመታት ተዘርዝሮ የማያልቅ እጅግ ብዙ አስቃቂ ግፍ በዐማራው ነገድ ላይ ተፈፅሟል። አሁንም እጅገ በተጠናከረ ሁኔታ በጎንደር ሕዝብ ላይ ሠራዊቱን አዝምቶ ንፁሐን ገበሬዎችንና ቤተሰቦቻቸውን ያለምንም ረህራሔ እየጨፈጨፈ ነው።

የጎንደርን ዐማራ ከጨረሰ በኋላ አንድ በአንድ ወደ ሌሎቹ የዐማራ ክፍላተ ሀገራት ሣንጃውን እንደሚያዞር ሳይታለም የተፈታ ነው። ስለዚህ ጀግናው የጎንደር ዐማራ በፋሺስት ከበባ ከመጥፋቱ በፊት ቀኝ ክንዱ የሆነው የጎጃም ሕዝብ ልክ አምና እንዳደረገው አሁንም በየቦታው ተነስቶ ወያኔን መውጫ መግቢያ ሊያሳጣው ይገባል። ወሎም ሆነ ሸዋ እንዲሁ። በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች ያለው ዐማራ ደግሞ በሥውር በመደራጀት በስንቅ ወገኑን ማገዝ ይጠበቅበታል። በውጭ ሀገር የሚኖረው የዐማራ ልጅ ደግሞ ያለ የሌለ አቅሙን በማስተባበር በመዋደቅ ላይ ላለው ዐማራ ወገኑ እንዲደርስለት ዐኅኢአድ ጥሪ ያቀርባል።

አንገት ደፍቶና እጅን አጣምሮ በመቀመጥ ከወያኔ ጭፍጨፋ ሊያመልጥ የሚችል ዐማራ የለም። ምክንያቱም በወያኔ መዝገበ ቃላት ዐማራነት ከወንጀሎች ሁሉ የከፋ ወንጀል ነውና! በመሆኑም የትም ያለ ዐማራ እንደ አንድ ሰው ተባብሮ ይህንን በፋሺስቱ ወያኔ የተከፈተብትን የእልቂት ጦርነት ካልመከተ በቀር፣ የዐማራ ዘር ታሪክ ሆኖ እንደሚቀር መናገር ገሀድ ዕውነታውን ከመመሥከር ውጭ ነቢይነትን አያመለክትም። ሕዝባችን ቃላት ሊገልፀው ከሚችለው በላይ ፍፁም የመጥፋት አደጋ ላይ ነው። ስለሆነም ዐማራው በአንድ ላይ ተባብሮ ራሱን ካላዳነ በስተቀር ማንም እርሱን ለማዳን ከየትም አይመጣም። ዐማራን የሚያድነው ዐማራ ብቻ ነው። ስለሆነም የዐማራ ልጆች ሆይ! የፍፃሜው ጦርነት ነው፤ ሁሉም ዐማራ ዘብ ይቁም ለኅልውናው!!

የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ዋስትና ነው!!

የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (ዐኅኢአድ)
Email-Aseuoipr@gmail.com