ከመቃብር በላይ የዋለን ስም፣ ሃውልት በማፍረስ ማጥፋት አይቻልም!! – ዳግማዊ መዐሕድ መግለጫ

Print Friendly, PDF & Email

ከመቃብር በላይ የዋለን ስም፣ ሃውልት በማፍረስ ማጥፋት አይቻልም!! – ዳግማዊ መዐሕድ መግለጫ

ግንቦት ፩፱ ቀን ፪፲፻፱ ዓ.ም (May 28 2017)
 ዳመዐሕድ 008/2009/2017

የሰምዓቱ መሪያችን የክቡር ፕሮፌሰር ዓሥራት ወልደየስን የመቃብር ሃውልት በማፍረስ ተግባር ላይ የተሰማራው ኃይል ማንም ይሁን ማን ከትግሬ ፋሽስታዊ አገዛዝ አቀናባሪነት ውጭ እንደማይሆን የመላው ዐማራ ሕዝብ ያውቃል። የትግሬ ፋሽስታዊ አገዛዝ ያልተረዳውና ሊረዳው አቅም የሌለው ዋና ጉዳይ፣ ዝነኛውና ዕውቁ የህክምና ሳይንስ አንጋፋ ሊቅ ክቡር ፕሮፈሰር ዓሥራት ወልደየስ ከሕዝብ መካከል ተገኝተውና ተማክረው ያከናወኑት ተግባርና የከፈሉት መስዋትነት በሚሊዮኖች ልብ ውስጥ ዘላለማዊ ሆኖ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገር ገድል መሆኑን ነው። ከመቃብር በላይ የዋለን ስም፣ ሃውልት በማፈርስ ማጥፋት አይቻልም።

የአስራ ስምንተኛውን ዓመት ዝክር አስበን በዋልንበት ማግስት፣ በሃውልታቸው ላይ የተፈጸመው የብልግና ተግባር፣ በፕሮፌሰር ዓሥራት ቤተሰቦችና ተከታዮቻቸው እንዲሁም በመላው ዐማራ ላይ የተከፈተ ጥቃት አድርገን እንወስደዋለን። ከዚህ ባለፈም ይህ ጥቃት በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸመ እና የፈጻሚዎቹን አውሬነት እና ትንሽነት ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ተግባር ነው።

የፕሮፌሰር አስራትን የመቃብር ሃውልት በማፍረስ በሚልዮኖች ውስጥ የተዋሃደውን ሃሳባቸውን እና ፍሬ እያፈራ ያለውን የህልውና ትግል ማጨናገፍ አይቻልም። ስለዚህ ይህን እርኩስ ምግባር ማንኛውም ሰብዓዊ ፍጡር ሊያወግዘው ይገባል። በተለይም የአዲስ አበባ ሕዝብና ባጠቃላይ የዐማራውን የትግስት መጠን የሚፈትን ነውና ዐማራው ይህንና መሰል በህልውናው ላይ የሚቃጡ ግፎችን በአንድ ላይ በመቆም እንዲታገል እና ራሱን ከዚህ አይነት ሰቅጣጭ ግፍ እንዲያላቅቅ እንጠይቃለን።

ዳግማዊ መዐሕድ የተደራጀን እብሪት፣ በተደራጀ የሕዝብ አመጽ እልባት መስጠት ለነገ የምናስተላልፈው ጉዳይ አለመሆኑን እየጠቆመ፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ባሉ መዋቅሮቹ ስር በመደራጀት እየገፋን ያለውን ስርዓት በማስወገድ ራሳችንን ከማንኛውም ኢሰብዓዊ ጭቆና ነጻ እናወጣ ዘንድ ጥሪውን ያስተላልፋል።
በተጨማሪም የመላው አዲስ አበባ ዐማራ የክቡር ፕሮፌሰር አስራትን የመቃብር ሃውልት በንቃት እንዲጠብቅ እና በቦታው ላይ በማፈርስ ተግባር ላይ በተሰማሩ ቡድኖች ላይ እርምጃ እንዲወስድ በጥብቅ እናሳስባለን።

የተገፋህ ግፋ እኮ አታንቀላፋ፣
ህይወት የለምና ገፊ ሰው ካልጠፋ!!!

ድል ለዐማራ ሕዝብ!!
ዳግማዊ መዐሕድ