የባህር ዳር ከነማ የጣና ሞገድ የአግር ኳስ ክለብ በመቀሌ ከነማ በደጋፊዎቹና በተጫዋቾቹ ላይ የደረሰበት የበደል ዝርዝር

Print Friendly, PDF & Email

የባህር ዳር ከነማ የጣና ሞገድ የአግር ኳስ ከለብ በመቀሌ ከነማ ደጋፊዎች የደረሰበት የበደል ዝርዝር እንደሚከተለው ዘርዝሮ አቅርቧል።
*************

ለባህር ዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች

በ05/09/2009 ዓ/ም ከመቀሌ ከነማ ጋር በምንጫወትበት ሰአት የደርሱብንን ችግሮች ስለማሳውቅ።

ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት በስቴዲየሙ ትራክ ላይ በሁለት ሚኒባስ፣ በባለ ሦስት እግር ባጃጅ እና በሁለት እግር ሞተር ባይስክል በመጫን ሜዳውን በመዞር የቡድናችንና የደጋፊዎቻችን ስሜት የሚጎዳ የእጅ ምልክና እጅግ አሳፋሪ ተግባር ተመልክተናል።

ሙሉ ስቴዲየም በማይክ [በድምጽ ማጉያ] ለሰው ህሌና የሚሰቀጥጡ፣ እኛ ለመጻፍ የተቸገርነውን የማንነታችን መለያ የሆነውን የብሄራችንን ስም በመጥራት አፀያፊ ስድቦችን ተሰድበናል።

ጨዋታው ከመጀመሩ ጥቂት ደቂቃዎች ጀምሮ ደጋፊዎች ከተቀመጡበት ማለትም ከዩኒቨርስቲው ስቴዲየም ፊት ለፊት በተወሰ መልኩ የዲንጋይ ውርዋሮሽና ደጋፊዎቻችንን የማዋከብ ድርጊቶች ሲከናወኑ በቦታው የነበሩ ጥቂት የፀጥታ ሀይሎች ምንም አይነት እኛን የማትረፍ እርምጃ አለወሰዱም።

እነዚህን ሁሉ ችግሮች ተቋቁመን ጨዋታው ከተጀመረ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ቡድናችን ጎል ያስቆጠረ ሲሆን ይህ ጎል ከተቆጠረ በኋላ በእለቱ የተመደበው ዳኛ በ5 ደቂቃዎች ውስጥ 4 ቢጫ ካርዶችን በማሳየት የተጫዋቾቻችን ስነ ልቦና ለመጉዳት ተሞክሮብናል። የእረፍት ጊዜ ጨርሰን ወደ ሜዳ ስንገባ የዳኛው ማስፈራራት ቀጥሎ ጨዋታው ውጥረት የነግሰበት ሆነ። ዳኛው በቡድናችን ላይ ጫና በማሳደር ያለአግባብ ወይም ተጫዋቹ ምንም አይነት ንክኪ ሳይኖረው የፍጹም ቅጣት ምት ተሰጠበን። ይህንንም በተወሰነ ደረጃ ትክክል አለምሆኑን ለመግለጽ ሞክረን መጠነኛ ቅሬታ አቅርበን ህጉን አስታውሰን ለህጉ ተገዝተን ፍፁም ቅጣቱ እንዲመታ ተስማምተን ፍፁም ቅጣት ምቱ ከተመታ በኋላ በ1 አቻ ጨዋታውን ቀጠልን። በመሃል የተጎዳብንን ተጫዋቻችንን በስትሬቸር አውጥተው ከሜዳ ውጭ በመወርወር ጉዳት አድርሰውብናል።

እነዚህን ችግሮች ለማስቆም አለመቻሉ በራሱ ውድድሩን ወደ ፀብ እና ወደ አላስፈላጊ ብጥብጥ አምርቶ ይበልጥ አስጨናቂ አደረገው። የተጎዳውን ተጫዋች መርዳት ሳይቻል ስነ ስረዓት አስከባሪ ሳይበግራቸው የመቀሌ ከነማ ደጋፊዎች ጥቂት የፀጥታ ሃይሎችን ጥሰው ወደ ሜዳ በመግባት በተጫዋቾቻችን እና በደጋፊዎቻችን እንዲሁም የቡድናችንን አባላት ጨምሮ በሙሉ ከፍተኛ ጉዳት ሲያደርሱብን በቦታው የነበሩት የፀትታ ሃይሎች ሊከላከሉልን እና ሊያድኑን አልቻሉም።

በሰአቱ ከፍተኛ ጉዳት ለደርሰባቸው ተጫዋቾቻችንና ደጋፊዎቻችን ወደ ህክምና ቦታ የሚያደርስ አምቡላን ባለመኖሩ በተገቢው ሰአት ወደ ሆስፒታል ሂደን ህክምና ለማግኘትና ህይወታችንን ለማዳን ብንጥርም የውድድሩ አመራሮችና የክልሉ ፌደሬሽን ሊተባበሩን ባለመቻላቸው ክፍተኛ ቅሬታ ጭሮብናል። በዚህ መሀል ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አመራሮች ያለብንን ሁኔታ ባንገልጽና ባይተባበሩን ኖሮ በህይወት የሚመለስ ተጫዋችና ደጋፊ አይኖርም ነበር።

በመጨረጫም የአባይ ባስ መኪናችን ሙሉ በሙሉ መስታውቶቹ በመመታታቸው 4 መኪኖች ቀያይረን ባህርብ ዳር ገብብተናል።

በግዜው የነበረው ሁኔታ ከሞላ ጎደል ይህን ይመስላል። ቀሪ ሙሉ ማስረጃዎችን የክለባችን ስራ አስፈጻሚዎች ለፌደሬሽኑ ያቀረብን መሆኑን ለመግለጽ እነወዳለን።

ይሁንና የመቀሌ ከነማ ሁሌ በህግ የማይዳኝበት ምክንያት አይገባንም!

ለአብነት፡- ከውልዋሎ፣ ከለገጣፎ፣ ከአክሱም፣ ከባህር ዳር የእግር ኳስ ቡድኖች ጋር የተደረጉ ጨዋታዎች በሙሉ ስፖርታዊ ጨዋነት በጎደለው መልኩ ነው የተጠናቀቁት።

በመጨረሻም ያለውን ችግር ተቋቁማችሁ የተጎዱ ልጆቻችን በመኪና እና በባጃጅ ወደ ህክምና ቦታ ላደርሳችሁልን አንዳንድ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች በደጋፊ ማህበራችን ስም ከልብ እናመሰግናለን።

ድልና ስኬ ዛሬም፣ ነገም ሁሌም ለጣናው ሞገድ ባህር ዳር ከነማ!