“በቅሎ ገመዷን በጠሰች” ቢሉ “ማሰሪያዋን አሳጠረች” እንደተባለው አማራው ላይ ለሚደርሰው እያንዳንዱ ግፍ የትግራይ ፋሽስቶች ተመጣጣኝ ምላሽ የሚያገኙበት ዘመን ቀርቧል። – ዳግማዊ መዐሕድ

Print Friendly, PDF & Email

ግንቦት 5 ቀን 2009 ዓ ም ስፖርት ለወዳጅነት በሚለው መርህ መሰረት የባህር ዳር ከነማ የእግር ኳስ ቡድንን ለመደገፍ ከባሕር ዳር ከተማ የመኪና ኮንትራት ይዘው በመጡ ደጋፊዎችና በመቀሌ ዩንቨርሲቲ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ የዐማራ ተማሪዎች ላይ በመቀሌ አዲ ሀቂ እስቴዲየም ውስጥ ኢሰብዓዊ ተግባር በትግራይ ፋሽስቶች ተፈጽሞባቸዋል። በጨዋታ መበለጣቸው ያልተዋጠላቸው የመቀሌ ፋሽስቶች የተጨዋቾቹን ሞራል ለመግደልና ተጽእኖ ለማሳደር በሚመስል መልኩ “ትምከተኛ፤ የምኒልክ ርዝራዥ፣ ነፍጠኛ፣ … ወዘተ” በማለት የጀመሩት የእብሪት ስድብ ቀጥሎ ወደ ኃይል ጥቃት ተሸጋግሯል። በዚህም ወደ 7 የሚጠጉ የባህር ዳር ከነማ ተጫዋቾች የተጎዱ ሲሆን ቁጥራቸው ያልታወቁ ደጋፊዎች ጥቃት ደርሶባቸዋል። ከጉዳቱ በላይ የከፋው የትግሬ ጤና ባለሙያዎች በሕዝብና በፈጣሪ ፊት ቃል የገቡትን የHippocratic Oath በመካድ ያሳዩት የስነ ምግባር ግድፈት ታሪክ የማይረሳው አሳፋሪ ድርጊት ሆኖ ተመዝግቧል። በአንጻሩ ይህንን ቃል ኪዳን በማክበር ወገኖቹን በቅንነት ሲረዳ የነበረው ዶ/ር ሃብታሞ ዓለምየ የተባለ የዐማራ ተወላጅ የጤና ባለሞያ የት እንደደረሰ አይታወቅም። ዐማራ የሆኑ የዩንቨርሲቲ ተማሪዎችም ድጋፍ ሰጥታችኋል ተብለው በመታወቂያ እየተለዩ ታስረዋል። ዕብሪተኞቹ የትግራይ ፋሽሽቶች በዚህ ሳያቆሙ የአባይ አውቶቡስና የባህር ዳር ከተማ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶችን በመሰባበራቸው ተጨዋቾቹ እና ደጋፊዎች መመለሻ አጥተው ሲደበደቡና ሲዋከቡ ማደራቸውን ዳግማዊ መዐሕድ ተገንዝቧል። እነዚህን ኢሰብዐዊ ድርጊቶችም ዳግማዊ መዐሕድ በጽኑ ይኮንናል ያወግዛል። እስከ አሁንም የተወሰኑ ዐማራ ወገኖቻችን በቂ የሕክምና እርዳታ እንዳያገኙ መደረጉና ወደመጡበት አካባቢ በሰላም እንዳይወጡ የታገቱ ሲሆን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የዐማራ ወገኖቻችን ይለቀቁ ዘንድ ዳግማዊ መዐሕድ ያሳስባል።

በትግራይ መቀሌ ተደብድበው ጉዳት ከደረሰባቸው አማራሮች በከፊል

በባላንጣ ሜዳ እንደመጫወታቸው በቁጥር አነስተኛ የሆኑት የባሕር ዳይ ከነማ ደጋፊዎችንና ተጫዋቾች ለመከላከል ዝግጅት አለመደረጉ የትግሬ ፋሽስታዊ አገዛዝ ጥቃቱን በተቀነባበረ መንገድ እንዲከናወን እንዳደረገው ዳግማዊ መዐሕድ ያምናል። ይህ ሁሉ እብሪት የተፈጸመው ዐማራው በሞተላትና ከዚህ ሁሉ ግፍ በኋላ አሁንም እንዲ,ሞትላት በሚሰበክለት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። ዳግማዊ መዐሕድ ዐማሮችን በነገዳቸው ነጥሎ የማጥቃቱን ተግባር በጽኑ የሚያወግዘውና እርሱንም እስከ ወዲያኛው ለማስቀረት የሚታገልለት ተግባር ነው። የዐማራ ሕዝብ ልጆቹ ስፖርት ለወዳጅነት ብለው በመጓዝ በስልሳ ደቂቃ የመቀሌ ቆይታቸው ላይ የደረሰባቸው ግፍ ዐማራ በመሆናቸው መሆኑንና ዐማራ ወዳጅ የሌለው መሆኑን በመረዳት ከአሁን ቀደም ከጎንደር ለጨዋታ በሄዱ ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን ተመሳሳይ ጥቃት መለስ ብሎ በማስተዋል ሰብሰብ ማለት ይጠበቅበታል። ራሱን ከፈጽሞ ጥፋት ለመታደግ የሚያስችለውን ሁለንተናዊ አቅም በመገምባት የመታገል አስፈላጊነት ላይ ትኩረት እንዲሰጥ ዳግማዊ መዐሕድ በጽኑ ያስገነዝባል። ዐማራው የገፋውን ሥርዓት የመግፋት፣ የጥቃቱ መንስዔ የሆነውን ሥርዓት የማጥቃት ታሪካዊ ግዳጅ የወደቀበት መሆኑን በመገንዘብ ዳግማዊ መዐሕድን በውስጥም በውጭም በመቀላቀል የዐማራን ነገድ ከፈጽሞ ጥፋት ይታደግ ዘንድ የትግል ጥሪውን ለመላው ዐማራ ሕዝብ በድጋሚ ያቀርባል። ዳግማዊ መዐሕድ በዚህ የግፍ ተግባር የተሳተፉ ፋሽስቶችና የበላይ ጠባቂያቸው የሆነው የትግሬ ፋሽስታዊ አገዛዝ ተጠያቂ መሆኑንና ሰላም ወዳድ የሆነው የሰው ፍጡር ሁሉ ይህን የትግሬ ፋሽስቶች የግፍ ተግባር እንዲያወግዝ ይጠይቃል። የሰብአዊ መብት ጥበቃ አለማቀፋዊ ድርጅቶች የትግሬ ነጻውጭ ፋሽስታዊ አገዛዝ ተጠያቂ በማድረጉ በኩል ትብብራቸውን ይጠይቃል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽንም ጉዳዩን በጥሞናና በገለልተኝነት በመመርመር አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ ዳግማዊ መዐሕድ ያሳስባል።

የተደራጀ የሕዝብ ትግል ለድላችን ወሳኝ ነው !!!
ድል ለዐማራ ሕዝብ !!!

ዳግማዊ የመላው ዐማራ ህዝብ ድርጅት ( ዳግማዊ መዐሕድ)