የጣናው ሞገድ ተጫዋቾችና የመቀሌው አደጋ

Print Friendly, PDF & Email

ከሙሉቀን ተስፋው | ብራና ሚዲያ

በትግሬ ጉዳት ከደረሰባቸው ዐማሮች በከፊል

ጨዋታው ተጀምሯል፤ በመቀሌ አዲ ሀቂ እስታዲየም ከመቀሌ ዩንቨርሲቲ ያሉ ተማሪዎች እና ከባሕር ዳር መኪና ኮንትራት ይዘው የመጡ ዐማሮች የጣናውን ሞገድ ለመደገፍ እስታዲዮም ገብተዋል። እስከ 60ኛ ደቂቃ የጣናው ሞገድ በባዕድ ምድር 1 ለ0 እየመራ ነበር። 60ኛው ደቂቃ ላይ ዳኛው አላስፈላጊ ቅጣት ምት ለመቀሌዎች ሰጠ።

የጣናው ሞገድ ተጫዋቾች አይሆንም ብለው ተቃወሙ፤ የሚሰማቸው አልነበረም። አገሩም፣ ሥልጣኑም ሁሉም ነገር የአንድ ወገን ነበርና በቅጣት ምት እኩል ውጤት ይዘው ቀጠሉ። በስታዲዮሙ የነበሩ ትግሬዎች በጅምላ ዐማራን መሳደብ ጀመሩ። “ትምከተኛ፤ ነፍጠኛ….” የማይሰማ የማሸማቀቂያ ስድብና የሥነ ልቦናዊ ብዝበዛ አልነበረም። በጠቅላላው የመቀሌ ትግሬ ለስድብ የወጣ እስኪመስል ድረስ።

የመቀሌ ከተማ ተጫዋቾች የባሕር ዳር ከነማዎች ላይ ሆን ብለው መትፋት ጀመሩ፤ ቢሆንም እስካሁን የጣናዎቹ ትዕግስትን አሳይተዋል። ቆይተው 4 ቁጥር ተጫዋችን በእግራቸው ረግጠው ሰበሩት፤ የቀይ መስቀል ሰዎች አልጋ ይዘው ገቡ። የተጎዳውን ዐማራ ተሸክመውት ከወሰዱ በኋላ ሰብአዊነት በሌለው መልኩ በቁማቸው ሲጥሉት የጣናው በረኛ ተመለከተ። ለምን ይህን ታደርጋላችሁ ብሎ ጠየቀ። በዚህም ድብድብ ተፈጠረ።

ሰባት ተጫዋቾች በሰው አገር ላይ ደማቸውን አፈሰሱ። ከደጋፊዎች ቁጥራቸው ያልታወቀ እንዲሁ ተደበደቡ። ከባሕር ዳር ተጫዋቾችንና ደጋፊዎችን ይዘው የሔዱ አውቶቡሶች ሙሉ በሙሉ ወደሙ፤ በጠገቡ ትግሬዎች። ያም ሆኖ የተጎዱ ተጫዋቾች ወደ መቀሌ አይደር ሆስፒታል ተወሰዱ።

የመቀሌ ዩንቨርሲቲ አይደር ሆስፒታል የሥራ ባልደረባ የነበረ ዶክተር ሀብታሙ የተባለ ዐማራ ሕክምና በሚሰጥበት ጊዜ ተጠልፎ ተወስዶ ታሰረ። እስካሁን እንኳ የት እንደታሰረ አልታወቀም። የዩንቨርሲቲ ተማሪ ዐማራዎች ድጋፍ ሰጥታችኋል ተብለው በመታወቂያ እየተለዩ ታሰሩ፤ ሌላም ሌላም።

ሌሊቱን መኪና በማፈላልግ የባሕር ዳር ከነማ ደጋፊዎችና ተጫዋቾች አደሩ፤ የዐማራ ክልል ባለሥልጣናት መኪና እንዲልኩ ቢጠየቁም አፋጣኝ ምላሽ መስጠት አልቻሉም፤ የትግሬ አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች በተደበደቡት ላይ የጥፋተኛነት ክስ ሲሰፉ ዋሉና አደሩ፤ እንዲያውም የመቀሌን ከተማ ሕዝብ ትግስት አደነቁ።

ዛሬ ጠዋት የትግራይ ጋዜጠኞች ወደ ተጎዱት የጣናው ደጋፊዎችና ተጫዋቾች በመሔድ ጥፋቱ የእነርሱ መሆኑን መናገር ካልቻሉ እንደማይወጡ ነገሯቸው። ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ ምንም ላይናገሩ ተስማምተው ወደ ባሕር ዳር መኪና ተከራይተው ጉዞ ጀመሩ።