ክቡር ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ከዚህ ዓለም የተለዩበትን 18ኛ ዓመት አሥመልክቶ የወጣ መግለጫ

Print Friendly, PDF & Email

ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ

ሰማዕቱ ክቡር ፕሮፌሰር አሥራት ወልደዬስ የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (የመዐሕድ) ፕሬዝዳንት የዛሬ 18 ዓመት ግንቦት 6 ቀን 1991 ዓ.ም. (እ.አ.አ. ሜይ 14ቀን 1999 ዓ.ም.) በፔንሲልቫንያ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ፊላደልፊያ አሜሪካ አገር በህክምና ላይ እንዳሉ ከዚህ ዓለም እንደተለዩ ይታወቃል። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ በተለይ ደግሞ የአማራው ሕዝብ ይህን ዕለት አስቦት የሚውለው በታላቅ ሀዘንና ቁጭት ነው።

ክቡርነታቸው ለኢትዮጵያ ሀገራዊና ሕዝባዊ አንድነት እንዲሁም እኩልነትና ዲሞክራሲያዊ ሕይወት ግኝት የከፈሉት አቻ የለሽ መሥዋዕትነት፣ በታሪክ ዓምድ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ ከመያዙም ባሻገር፣ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የሚኖር ነው።

ፕሮፌሰር! ከትግሬ ዘረኞች ሥልጣን መያዝ ጋር ተያይዞ የመጣው የጎሳ ፖለቲካ ገና ከመነሻው ችግር ሊያሥከትል እንደሚችል በግልፅ ከመናገር አንሥቶ የመከራ እሳቱም ሲቀጣጠል ያንን ለማጥፋት በቀዳሚነት የተሰለፉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነበሩ። ለምሳሌ በ1983ዓም የትግሬ ዘረኞችና ዕድምተኞች ያካሄዱትን የኢትዮጵያን ሀገራዊና ሕዝባዊ አንድነት የመናድ ተግባር፣ የኮንፈረንሱን ምንነትና ተልዕኮ በጀግንነት በመዋጋት ድምፃቸውን አጉልተው ያሠሙ ጀግና ነበሩ።

በ1984 ዓ.ም. ዐማራው በአርባጉጉ፣ በበደኖ፣ በአረካ፣ በአሰቦት ገዳም፣ በአሩሲ ነገሌና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል ህይወቱ እያለ ዓይኑ ሲጎለጎል፣ ሕይወቱ እያለ ቆዳው ሲገፈፍ፣ ሕይወቱ እያለ ሥጋውን ቆርጠው “ብላው እያሉ” ሲያሰቃዩት፣ ሕይወቱ እያለ ቤት ዘግተው ሲያቃጥሉት፣ሕይወቱ እያለ ወደገደል ሲወረውሩት፣ ሕፃናት ከእነቤተሰቦቻቸው ሲታረዱ፣ የዕርጉዞች ሆድ ሲቀደድና ሽሉ ሲጣል፣ የዐማራው ልጃገረዶች ሲደፈሩ፣ ሲዋረዱና ተማርከው በባርነት ሲያገለግሉ፣ አብያተ ክርስቲያናት ሲቃጠሉና ሌሎችም ተዘርዝረው የማያልቁ የዘር ማጥፋት ሰቆቃዎች ሲፈፀሙበት፣ ፕሮፌሰር አሥራት አይተው እንዳላዩ፣ ሰምተው እንዳልሰሙ ሆነው ማለፍ አልቻሉም። ….. (Read more, pdf)