በወያኔ ገነት እኛ በህልም እነሱ በእውነት አለማችን እንቀጫለን!

Print Friendly, PDF & Email

ወያኔ በትግሬ ብሄረተኝነት ላይ የተገነባ ጠንካራ አደረጃጀት አለው። ድርጅቱን ህዝቡ ከምክንያት ውጭ በሆነ ደማዊ ስሜት እንዲደግፈውና እንዲንከባከበው ማድረግ ችሏል። ህዝቡን እና ድርጅቱን በማይነጣጠል ገመድ ያቆራኘ ስኬታማ ድርጅት ነው። ትግራይ ወይም ሞት በሚል ጠንካራ ሰንሰለት የተሳሰረ ህዝብ ለማድረግ ችሏል። ይህም የተደረገው ማንኛውንም ነገር ለትግራይ ብሄራዊ ጥቅም በቁጥጥር ስር በማዋል ነው። ወያኔ አዲሲቷ ኢትዮጵያ በሚል የሚጠራት ነባሯን ኢትዮጵያ አፈራርሶ የራሱን ኢትዮጵያ ገንብቷል። ይህች አዲስ ኢትዮጵያ ለትግራይ አፋሽ አጎንባሽ፣ ለትግራይ ጥቅም ተንበርካኪ ናት። ይህች አዲስ ኢትዮጵያ የትግራይን ብሄራዊ ጥቅም በአስተማማኝ ሁኔታ በምታስከብርበት ቅርጽ የተሰራች አፓርታይድ ቅኝ ናት።

ወያኔ ይህችን አዲስ ኢትዮጵያ ራሱ ብቻ በሚጠብቃት መንገድ አይደለም ያዋቀራት። ራሳቸው ተገዥዎች እንዲጠብቋት አድርጎ እንጅ። ሰላማዊ ትግል፣ መድብለ ፓርቲ፣ ብዝሀነት፣ የታሰረ ጥንታዊ ኢትዮጵያዊ ብሄረተኝነት የመሳሰሉትን የወያኔ አዲሲቷ ኢትዮጵያ መጠበቂያ አምዶች በመጠቀም። የታሰረ ጥንታዊ ኢትዮጵያዊ ብሄረተኝነት ማለት የጥንቱን ታላቅ ኢትዮጵያዊነት መመኘት፣ መናፈቅ ባልተጨበጠው በዛ ህልም መዋለል፣ እየዋለሉ በተግባር የሚጨበጥ ስራ አለመስራት ማለት ነው። የሚገለጸውም በመዝሙር፣ በሙዚቃ፣ በተረት ነው። ይሄን ምኞታዊ ኢትዮጵያ ከምኞት አልፎ በተግባር ማምጣት አይቻልም። ቢያንስ አሁን ባለው የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁኔታ። በእውነት ለውጥ ካላመጣ ደግሞ ከምኞትነት የዘለለ ሚና አይኖረውም። ምኞትን ደግሞ ወያኔ ለራሱ አጃቢ ማድረጉ የሚጠበቅ ነው።

ወያኔ የራሱን አዲስ ኢትዮጵያ እየገነባ በጎን ኢትዮጵያን እንደሚያፈርስ ያስመስላል። እነዛ የጥንቲቷ ኢትዮጵያ ናፋቂዎችም ወያኔን ኢትዮጵያን እንዳያፈርስባቸው ሲለማመጡ ይኖራሉ። በኢዲሲቷ በወያኔ ኢተዮጵያ ላይ ሆነው የጥንቲቷን ኢትዮጵያ መናፈቅ፣ መሻት ወያኔ በጥብቅ የሚፈልጋቸው ነገሮች ናቸው። በተግባር ተንቀሳቅሰህ አዲሲቷን ኢትዮጵያ አፍርሰህ የምትመኛትን የጥንቲቷን ኢትዮጵያ ለመገንባት እስካልተንቀሳቀስክ ድረስ ለወያኔ ተጨባጭ ስጋት አይደለህም። ይልቅም ህዝቡ በአዲሲቷ የወያኔ ኢትዮጵያ ላይ ተንቀሳቅሶ ወያኔን እንዳያባራር የሚያደነዝዝ አረጋጊ ነህ። አንተ በምኞት ደንዝዘህ የጥንቲቷን ኢትዮጵያ በህልም አለም ስትቀጭ ወያኔ ለራሱ ገነት ለአንተ ሲኦል ባደረጋት አዲሲቷ ኢትዮጵያ ውስጥ አለሙን ይቀጫል። እና አንተ አጃቢ-በህልሙ ነህ። የእውነቱን የሚኖረውን ወያኔ በህልምህ የምታጅብ ህልመኛ። የህልምህ እስረኛ ነህ።

አንተን እያጠፋህ ራስህን ደግሞ በፈቃድህ የእርሱ ጠባቂ ያደረገህ ወያኔ አያስገርምንም! ወያኔ ግን ዘዴኛ ብቻ አይደለም። እድለኛም ጭምር እንጅ። በጠብመንጃ ብቻ ነው እምወርደው ብሎ እየተናገረ አይ በሰላም ትወርዳለህ ብለው ሲያጅቡት የኖሩ ህልመኞች ሰላማዊ ታጋዮችን ፈጠረለት። ህዝቡ በተለይ አማራው በአማራነቱ እንዳይነሳ የሚያደርጉ ልሂቃንንም አላጣም። እንደ ሳይንቲፊክ ፊክሽን ፊልም የሌለ ነገር በምናብ የሚያስጨብጡ ሰባኪያነ-አንድነት፣ ዘማሪያን-ሀሳዊ ልእልና አላጣም። እና ይሄን ወያኔ እድል እና ዘዴው እንዲህ ይጠብቁታል።

ለማጠቃለልም አዲሲቷ ኢትዮጵያ በሁለት መሰረታዊ ተቃርኖዎች መካከል የቆመች ናት። በቀጥታ ለትግራይ በመንበርከክ እና በቀጥታ አማራን በማጥፋት። የወያኔ ኢትዮጵያ ለአማራ ጥፋት ናት። የወያኔ ኢትዮጵያ አማራውን በማደህየት፣ ቁጥሩን በመቀነስ፣ እንዳይማር በማድረግ፣ በማሸማቀቅ፣ በማሳደድ የተመሰረተች ናት። ይህች የወያኔ ኢትዮጵያ ለወያኔና ለበቀለበት ህዝብ እንዲሁም ለአጋሮቻቸው ገነት ናት። የወያኔ ኢትዮጵያ ስትጎለብት አማራ እየኮሰመነ ነው የሚሄደው። የወያኔ ኢትዮጵያ እድሜዋ በረዘመ ቁጥር የአማራ እድል እየከበደ ነው የሚሄደው። በዛ መልኩ እንድትፈስ ሆና ስለተሰራች። በጣም አሳሳቢ የሚሆነው ደግሞ ራሱ እንዲጠፋ የተፈረደበት ህዝብ ልጆች ይህችን አዲሲቷን ኢትዮጵያ በልዩ ልዩ ሴራ ተጠልፈው ጠባቂዎች በመሆን የወያኔን እድሜ በማራዘም የወገናቸውን ስቃይ ሲያበዙ ማየት ነው። ሰው ሳይገደድ እንዴት ጠንቅቆ ባለማሰብ ብቻ መሰቀያውን ግንድ ተሸክሞ ወደመሰቃያ ተራራ ያጉዛል!

ብቻ ከባድ የሆነ ነገሮችን የመገንዘብ ችግር አለ! መገንዘብ ላይ እንስራ–ለየራሳችን! ለወያኔ እድሜን እያረዘመለት ያለው የእሱ ጥበብ ብቻ ሳይሆን የእኛ የመገንዘብ ችግር ነው! ሰው መጥፊያውን ሲያጅብ ስታይ ከባድ የመገንዘብ ችግር እንዳለ አስተውል!

ምስጋናው አንዱዓለም