ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያን በሙሉ፦ እንኩዋን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ!

Print Friendly, PDF & Email

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት
እሑድ ሚያዚያ ፰ ቀን ፪ሺህ ፱ ዓ.ም.              ቅፅ ፭፣ ቁጥር ፲፬

 ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያን በሙሉ፦ እንኩዋን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ!

ውድ የመላው ኢትዮጵያ የክርስትና ዕምነት ተከታዮች ሆይ፦

ከሁሉ አስቀድሞ እንኳን ለ፪ሺ፱ ዓ.ም የትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ! የሰውን ልጅ ከሞት ፍርድና ከመከራ ሊታደግ ሰው የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለመዳናችን በዕለተ ዐርብ ታመመ፤ ተስቀለ፤ ሞተ። ሞቱም እኛን ከሞተ ነፍስ ለማዳን ነው። በመስቀል ከሞተም በኋላ ከመስቀል ወርዶ ተገንዞ ተቀብሯል። በዕለተ ዐርብ ክፉ መካሪዎችና አድራጊዎች እውነትን ያሸነፉ መስሏቸው ነበር፤ በመድሃኒታችን ላይ የደረሰውም መከራ መልካም ነገርን የሚያስብ ኅሊና ያለው ሰው ሁሉ በዚህ ዓለም እንዳይኖር የተከለከለ አስመስሎት ነበር። ይሁን እንጅ የመቃብርን ኃይል ሽሮ፤ ሦስት ቀናትና ሌሊት በከርሰ መቃብር አድሮ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ፤ ሞትን ድል ነሥቶ «መቃብር ክፈቱልኝ፣ መግነዝ ፍቱልኝ» ሳይል በኃይል በሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ። አሜን!

የታላቁ ዐማራ ሕዝብ ጉዳይም እንዲሁ ነው። ዐማራው የኢትዮጵያዊነት ዋልታና ማገር፣ ወራጅና ጭምጭም፣ ሲሚንቶና አሸዋ መሆኑ ይታወቃል። ይህን ማንነቱን ጠንቅቀው የሚያውቁ፤ የአገርና የትውልድ ከሃዲዎች፣ ዐማራውን የሌሎች ነገድና ጎሣዎች ጠላት አድርገው በመሳል፣ ላለፉት ፳፮(ሃያ ስድስት) ዓመታት የዘረኛው የትግሬ ወያኔ አገዛዝ፣ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል እንዲፈጸምበት አድርገዋል። በመሆኑም በቁጥር ከአምስት ሚሊዮን የማያንሱ ዐማሮችን በልዩ ልዩ መንገዶች ከምድረ-ገጽ እንዲጠፉ አድርገዋል። አንዳንድ አወቅን የሚሉ፣ የማንነት ቀውስ ውስጥ የገቡ ሰዎችም «ዐማራ የሚባል ነገድ የለም» እስከ ማለት የደረሱ መኖራቸውን፣ ዐማራው በትዕግሥትና በትዝብት ሲያያቸው እንደኖረ ይታወቃል። ወያኔም በትዕቢት ተወጥሮ፣ ዐማራን «ፈሪ፣ ሽንታም፣ ወራሪ፣ ትምክህተኛ፣ ነፍጠኛ»፣ ወዘተርፈ እያለ የዐማራን ዘር ከመግደልና ከማንገላታት አልፎ፣ መልካም ስምና ታሪኩን ጥላሸት ሊቀባ መሞከሩ በግልጽ ይታወቃል። ሆኖም፣ ሁሉም ነገር ገደብና ወሰን አለውና፣ የዐማራው ድምፅ ከፍ ብሎ እንዲሰማ በቆራጥነት የቆሙት ልጆቹ ባሰሙት ጩኸት፣ ይኸውና የጉዳዩ ባለቤት የሆነው የዐማራው ሕዝብ ከሐምሌ ፭ ቀን ፪ሺ፰ ዓ.ም. ጀምሮ፣ በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ፋና ወጊነት የተቀጣጠለው የዳግማዊ የዐማራ ትንሣኤ ሕዝባዊ አመጽ  ተጠናቅሮ በከፍተኛ ታክትክና ስትራቴጂክ በአጥቂነት ረድፍ ይገኛል።

የዚህን ዓመት የፋሲካ በዓል በምናከብርበት ወቅት ፣ ካሰቡት ግብ ለመድረስ ፤ ያመኑበትን ዓላማ አንግቦ በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ ለድል እንደሚያቃርብ ከልብ የሚያምኑት፣ ይኸውና ዛሬ እንደ ተርብ የሚናደፉ፣ እለፈ አዕላፍ የዐማራ ልጆች ዝምታቸውን ሰብረው፣ በማንነታቸው ኮርተው ወገናቸውን ከፈጽሞ ጥፋት ለመታደግና የኢትዮጵያን አንድነት ዳግም ትንሣዔ ዕውን ለማድረግ ሌት ተቀን ከሳይበር እስከ አካላዊ ጦርነት ገጥመው ወያኔንና አጋሮቹን የተፉትን ምራቅ እንዲልሱ እያስገደዱት ይገኛሉ። ይህ የጽናትና የቁርጠኝነት ውጤት ነው። ያለቁርጠኝነት ለድል መብቃት አይቻልምና፣ ሞረሽ ወገኔ ባለፉት አምሥት ዓመታት በቁርጠኝነት ያካሄደው ዐማራውን የማንቃትና የማደራጀት ትግል ፣ ትግሉን ወደ ትጥቅ ትግል ያሸጋገረው ስለሆነ፣ ይህንም በድል አድራጊነት ለመወጣት ቁርጠኝነቱን በእጥፍ ድርብ ማሳደግ ይጠበቃል። ስለሆነም፣ የዐማራው ልጆች፣ የተፋፋመው የዐማራው  የመደራጀትና ማንነትን የማስከበር ትግል ለድል እንዲበቃ፣ ሁሉም የዐማራ ልጅ፣ በኃሣብ፣ በቁሳቁስ፣ በገንዘብ፣ በምክር፣ በሰው ኃይል ወዘተርፈ ሊተባበር ይገባል። «ድር ቢያብር  አንበሳ ያስር» ነውና ብሂሉ፣ ሊያጠፋን የዘመተውን አጥፊ ቡድን ጨርሶ ሳያጠፋን፣ አጥፊውን ለማጥፋት ድጋፋችሁን ከምንጊዜውም በበለጠ ዛሬ እንሻለን።

ብረትን መቀጥቀጥና ተፈላጊውን ቅርጽ ማስያዝ የሚቻለው ሲግል ሲቀጠቅጡት ነውና፣ የትግሬ-ወያኔም የሚወድቀው ራሱ በፈጠረው ሁለንተናዊ ችግር ተማሮ አደባባይ የወጣው የሕዝብ ቁጣ ሳይበርድ፣ ቁጣውን ማጋጋል ለነገ የሚባል ተግባር ሳይሆን አሁኑኑ ልንያያዘው የሚገባን ነው። በመሆኑም በውስጥና በውጭ ለሚደረገው ሁለገብ ትግል ገንዘብ ወሳኝ ድርሻ ያለው ስለሆነ፣ ጀግኖቻችን እና ቤተሰቦቻቸው ከእኛ ድጋፍ ማነስ የተነሳ ትግሉ እንዳይጓተት የምንችለውን ሁሉ እንድናደርግ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ጥሪውን ያቀርባል። ስለዚህ ሳይውሉ ሳያድሩ በሚችሉት መጠን የወገኖቻችንን ሁለገብ ትግል በገንዘብ ለመርዳት የሞረሽ ወገኔ አማራ ድርጅት ድሕረገጽን (http://www.moreshwegenie.org/) በመጎብኘት፡ የጎፈንድሚ (GoFundMe)፤ የፔይፓል (Paypal)፤ ወይም የባንክ አካውንታችንን  ቁጥር ተጥቅመው የዚህ ታሪካዊ ትግል አካል በመሆን የማያቋርጥ ድጋፍዎን እንዲለግሱ በአንክሮና በትህትና ያሳስባል።

የተወደዳችሁ የክርስቶስ ቤተሰቦች፤ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ያዳነን፤ ጌታችንንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዚህ ታላቅ በዓል ስላበቃን እንዲሁም የመስቀሉ ሥር ስጦታ የሆነችውን ድንግል ማርያምን ስለሰጠን ክብር ምስጋና ይግባው።በክርስቶስ ትንሣኤ ያገኘነው ጸጋ ታላቅ ነው። ከጨለማ ወደ ብርሃን ወጥተናል÷ ከሞት ወደ ሕይወት ተሸጋግረናል፤ በመሆኑም በዚች እለት በኢትዮጵያ ምድር በወራሪውና በጥቁር የአፓርታይድ የግፍ አገዛዝ ቀንበር ወድቀው በቀን ጨለማ ለሚገኙ ዐማራ ወግኖቻችንና በእስር፤ በስደት ና በህመም ለሚሰቃዩ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ፀጋውን ያበዛላቸው ዘንድ ፀሎታችን ይሁን! አሜን

አንድ ዐማራ ለሁሉም ዐማራ፤ ሁሉም ዐማራ ለአንድ ዐማራ!
የዐማራ ኅልውና መጠበቅ ለኢትዮጵያ ኅልውና መከበር አስተማማኝ ዋስትና ነው!