የወያኔ ካድሬዎች የሕዳሴው ግድብ ስያቀርቡልን፤ እኛም ይህንን ጉድ እንድያዩልን እንጋብዛቸዋለን!

Print Friendly, PDF & Email

ጌታቸው ረዳ (Getachew Reda – Editor Ethiopian Semay)

ሰሞኑን የወያኔ ፕሮፓጋንዳ አገልጋይ ድረገጾች የሕዳሴ ግድብ ተብሎ የሚጠራው “አማራዎች” በግድቡ ዋና ቀያሺነት/መሃንዲስነት እና በከፍተኛ አስተዳደራዊ መስኮች የተካፈሉበት ግድብ “የብርሃን አብዮት” የሚል ስም ሰይመውለት በዋናነት ባሕር ወደባችን ለእናቱ አገር ለኤርትራ በማዳላት ላስነጠቀን፤ ወደባችን ለዓረቦች መፈንጫ እና ጸረ ኢትዮጵያ መዋያ አጀንዳ እንዲሆን በጥናትና በተንኮል ለሰራው ለሞተው ለፋሺስቱና ለባንዳው መለስ ዜናዊ ማስታወሻ እንዲሆን በመዘገብ እንድንመለከትላቸው ጋብዘውናል። የወያኔ ካድሬዎች የበዙን የግድብ ክንዋኔ #EBC የብርሃን አብዮት …መጋቢት 16/2009 EBC Documentary https://youtu.be/JzexDIYmO-o

የሚል ሲሆን፤ ወያኔዎች ይህንን ሲጋብዙን እኛም ይህንን ከዚህ በታች ያለውን አንዲመለከቱ አንጋብዛቸዋለን።

አስገራሚ የሚያደርገው ደግሞ የግድቡ ዋና ቀያሾች/መሃንዲሶች አማራዎች ሲሆኑ፤ “ነፍጠኛ” እያለ አማራን ሲሳደብ የነበረው በጸረ አማራው በመለስ ዜናዊ አስተዳዳር፤ በትግሬዎች ዘመነ መንግሥት በሚሊዮን የሚቆጠሩ አማራዎች ከሚኖሩባቸው ከተሞች እና ገጠሮች “ውጡ” እየተባሉ ሲባረሩ፤ እናቶችና እርጉዞች በገጀራ እና በካራ ሆዳቸው እየተቀደዱ፤ አንዳንዱም ከነህይወታቸው ወደገደል ተገፍትረው ለሞት ሲዳረጉ፤ አንዳንዱም ሥጋቸው በሰው አራዊቶች ተቀቅሎ ሲበላ፤ ነግድቡ ቅየሳ የተሰማሩ እነኚህ እና እነኚህ የመሳሰሉ ምሁራን አማራዎች ፤ በዚህ በጸረ አማራ በሆነው በወያኔን ሥርዓት ሥር በተለያዩ የመስክ ሥራዎች በመስራት ወያኔን ሲያገለግሉ፤ አንዳንዱም ጥብቅና ቆመው ሲሟገቱለት ማየት ላስተዋይ ሰው እጅግ ይገርማሉ።

ያንዳንዶቹ አማራዎች ንግግር በትዝብት ሳደምጥ ጭራሽኑ በፋሺስት ሥርዓት ተስልፈው ሂትለር ባቀደው የግንባታ ሥራ ተሰማርተው ያገለግሉ የነበሩ አይሁዶችና የጀርመን ምሁራን ተመሳሳይነት አላቸው። ይህ የብርሃን አብዮት ተብሎ የተሰየነው ግድብ ከ2,000,000-እስከ 5,000,000 አማራ በወያኔ የሕዝብ ቆጠራ መስርያቤት ሚኒስቴር የታመነ ከምድረገጽ መጥፋቱ ስናስታውስ፤ ይህ የብርሃን አብዮት የተባለው ብርሃን አመንጪ ግድብ በሚሊዮኖች የተሰወሩበት እውን ሲሆን የተሰውሩበት ምክንያት ግን አላወቅንም ብሎ ወያኔ የነገረንን ዜና አማረዎች ከተጣሉበት “ገሃነበ ጭለማ” አብርቶ ያሳየን ይሆን? መልሱ በግድቡ ለተሳተፉ አማራ መሃንዲሶቹ እንተወው።

በኛ በኩል የወያኔ ካድሬዎች የመለስ ዜናዊ ማስታወሻ ግድብ እንድንመለከት ሲጋብዙን እኛም ይህንን እንዲመለከቱት የመረጥንላቸው የሚከተለው የቆቃ እና የሞጆ የሃይቅ ብከላ በኗሪዎች ላይ የደረሰው ሃዘን፤ እናት 4 ልጆቿን ያጣችበት ክስተት በዚህ ማሕደር ተዘግቧል። አብረን እንመልከት።
ትግሬዎች ሃይቃችንን በመርዝ በከሉት።

የሸዋ አማራና ኦሮሞዎች እያለቁ ነው። part 1