አቶ ማሙሸት አማረ ለ11 ጊዜ ከወንድሙ ጋር በትግሬ ወያኔዎች ታፍኖ ተወሰደ

Print Friendly, PDF & Email

ሰላማዊው ታጋይ አቶ ማሙሸት አማረ ለዐሥራ አንደኛ ጊዜ ታሠሩ

አቶ ማሙሸት አማረ

(ከሙሉቀን ተስፋው)

የሕጋዊው መኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሸት አማረ ትናንት የካቲት 22 ቀን 2009 ዓ.ም. ከወንድማቸው ከአቶ ግዛቸው አማረ ጋር በወያኔ ደኅንነቶች ታፍነው ታሰረዋል፡፡ አቶ ማሙሸት አማረ ከመዐሕድ ጀምሮ በቆራጥነት ሙሉ እድሜያቸውን ለትግል የሰጡ ጀግና ሲሆኑ በተለያዩ ጊዜያት በጠቅላላው ለ11 ዓመታት በወያኔ እስር ቤቶች አሳልፈዋል፡፡

በ2006 ዓ.ም በመኢአድ ጠቅላላ ጉባኤ ከፍተኛ ድምጽ አግኝተው የፓርቲው ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡ ቢሆንም የሕወሓት ምርጫ ቦርድ ለእነ አቶ አበባው መሐሪ መስጠቱ ይታወቃል፡፡ ይህን ተከትሎም አቶ ማሙሸት አማረ ለአራት ወራት ያክል ታስረው በ2007 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ተፈተው ነበር፡፡

አቶ ማሙሸት አማረ የተቃውሞ ትግሉን የተቀላቀሉት በመላው አገሪቱ የዐማራ ተወላጆች የሚደርስባቸውን እልቂት ለመታደግ የዩንቨርሲቲ ትምህርታቸውን አቋርጠው በ1984 በሚያዚያ ወር ሲሆን ከፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ጋር ለ8 ዓመታት ታስረው ተፈተዋል፡፡ አቶ ማሙሸት እስካሁን ድረስ ለዐሥር ጊዜ ያክል በድምሩ 11 ዓመት ያክል የሚሆነው ዘመናቸውን ያሳለፉት በወያኔ እስር ቤቶች ሲሆን አሁንም ለዐሥራ አንደኛ ጊዜ በወያኔ ደኅንነቶች ትናንት መጋቢት 22 ቀን 2009 ዓ.ም ታፍነዋል፡፡ አይበገሬው ታጋይ አቶ ማሙሸት የወጣነት ጊዜያቸውን በወያኔ ማጎሪያ ቤቶች ቢያልፍም ከጸና አቋማቸው ወደ ኋላ ብለው አያውቁም፡፡

የወያኔ አገዛዝ የመኢአድ ዐማራ የሆኑ አባላትን በከፍተኛ ሁኔታ እያሳደደ ሲሆን በቅርቡ እንኳ አቶ ዘመነ ጌጤን፣ አቶ ለገሠ ወልደሃናንና ወጣት ክንዱ ዱቤን አስረው ከፍተኛ ስቅይት እየፈጸሙባቸው ነው፡፡ አቶ ዘመነ ምሕረት ላይ ደግሞ የግድያ አዋጅ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡