ስቃይ በማዕከላዊ እስር ቤት

Print Friendly, PDF & Email

ድጋሜ ባንገናኝ ትግሉን አደራ~የጎንደር ወጣቶች! ከጎንደር በትግሬ ወያኔዎች ታፍና ተወስዳ በማዕከላዊ እስር ቤት ትስራ እየተሰቃየች የምትግኘው እህታችን ወጣት ንግትስ ይርጋ

በተለያዩ የፖለቲካ እስረኞች ወያኔ ያለርህራሄ የሚፈፅመው ግፍ ከውስጥ ሲጋለጥ

ስቃይ በማዕከላዊ እስር ቤት!

በተለዩ የፖለቲካ እስረኞች ወያኔ ያለርህራሄ የሚፈፅመው ግፍ ከውስጥ ሲጋለጥ!

እውነት ወያኔ/ኢሀዲግ መንግስት ወይስ ማፍያ? ሰብዓዊነት በጭራሽ የማይሰማው ስለመሆኑ ብታምኑም ባታምኑም ከ3 ሳምንት በላይ በማዕከላዊ ዘግናኝ የሰቆቃ እስር ቤታቸው በቅርበት ከሚሠሩ ባልደረቦቻቸው ጋር በቅርበት መረጃ በመሰብሰብ በእውነታ የተገኘው መረጃ የሚከተለውን ይመስላል፡፡
በነገራችን ላይ ሰቆቃውን የሚያሳይ ፎቶ ብቻ ሳይሆን በስጋት በመቀረፁ ምክንያት ውስን እና ጥራት ባይኖረውም አለን ፡፡ነገር ግን ለባለውለታዎቻችን ስጋት ሲባል ይቆይና በሌላ ጊዜ እንዳስፈላጊነቱ የምንለቀው ይሆናል፡፡

ነግ በኔ በማለት አስባቹህ አንብቡት እና ቢያንስ ለአምላካችን እናስረዳ/እንፀልይ፡-

አዲስ አበባ ከቅዱስ ጊወርጊስ ቤተ ክርስቲያን ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው ዋናው አስፓልት በስተቀኝ ከሶር አምባ ሆቴል ቀጥሎ በተንጣለለ ነጭ ህንፃ የተገነባው ነው ማዕከላዊ የምንለው፡፡ሲጀመር ህንፃው ከማማሩ የተነሳ በሁሉም ጎን ስታዩት ከዚህ መታሰርማ የተሻለ ነው ብለን እንድናስብ ይጋብዛል፡፡ግን ሰው የጤንነትን ጥቅም የሚያውቀው ታሞ ሲያየው ሆነና ቅሉ። ከታች ሁሉም ታሳሪዎች በስተጀርባ በአለም ብርሀን ት/ቤት ፊት ለፊት አቅጣጫ በሚገኘው በጣም ጥልቅ ግራውንድ/የምድር ፈፅሞ ጨለማ ክፍል ነው ያሉት፡፡

ለመጠየቅ ስንገባ ከመጀመርያው የውጭ ጥበቃ ክፍል ከእስረኞች ፈፅሞ ከእይታ እና ከኢንፎርሜሽን በራቀ ሁኔታ የቆሙት ከትግራይ ብሔር ውጭ ያሉት በተለይም አማራ እና አሮሞ ብሎም ውስን የሌላ ክልል ብሔር ፖሊስና ፌደራል ወታደሮች ናቸው፡፡ ሲቀጥል ከውስጥ ይህ/ቺን ታሣሪ ለመጠየቅ ይችላሉ/ተፈቅዷል ወይ የሚለውን ለውጮቹ ጠባቂዎች ለመናገር የቆሙ በትንሹ ፊደል ቀመስ የሆኑት ናቸው፡፡በ3ተኛ ደረጃ ውስጥ እስረኞች በጨለማ መኝታ በሌለበት በረዷማ የሆነ ቅዝቃዜ ያለበት በፍፁም ያለህበትን ክፍል ልታውቀው በማያስችል ጥልቅ ገደል ጥቅጥቅ የጨለማ ቦታ ነው።

ቅርብ ሆነው በመቀመጥ የሚመርጁ የፈለጉትን ታሳሪ በፈለጉት መልኩ የሚያስቀጠቅጡ ካስደበደቡም በኃላ ተደብዳቢው ሊሞት ሲያጣጥር ለእርዳታ ሳይሆን ተጨማሪ መረጃ ከመሞቱ በፊት ለማግኘት ሲሉ ብቻ ሀኪም በማዘዝ የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ/1st aid/ ብቻ በመስጠት ለድጋሜ የስቃይ የሚያመቻቹ የብሔራዊ መረጃ ሰላዮች ናቸው። እንደታሳሪው የወንጀል ሁኔታ እየታየ እንዲመጡና የምርመራ ስራቸውን የሚያሳልጡ ሁሉም በተለይ መርማሪዎች የደህንነት ባለሙያዎች እና የስልክ መረጃዎችን የሚፈትሹ የIT ባለሙያዎች አጠቃላይ ትግሬ ናቸው፡፡

ሶስት ሳምንት በፈጀው ክትትል በአሁኑ ወቅት እጅጉን አብላጫ ስቃዩን የሚፈፀምባቸው አማራ በተለይም ጎንደርና የጎንደር ዙርያ ሰዎች ሲሆን አብሶም የሰሜን ጎንደር ህዝብ እና የኦሮሚያ ወጣቶች አካባቢ የተያዙት የሚከተሉትን የቁም ሞት ቅጣት ይቀጣሉ፡-
፨ በቅልብ አጋዚ ወታደሮቻቸው በተለይም ከግ.7 ጋር ግንኙነት አላቸው በማለት የጠረጠሩአቸውን ታሳሪዎች፡-

፨ 1) ታስቦ በተዘጋጀ ከአንድ ክፍል ዶርም ከኮርኒሱ ባሉ አግዳሚ ብረቶች በተበየዱ ሁለት
ብረቶች በተንጠለጠሉት ገመዶች ሁለት እግሮቻቸውን አስረው ጭቅላታቸውን ወደ ታች በመዘቅዘቅ ሳይበቃቸው በተጨማሪ 2ቱ እጆቻቸው ወደ ጎን ተወጥረው ይታሰራሉ፡፡ ልብ በል ወገኔ ወያኔ እውን ኢትዮጲያዊ ናቸውን? የሚያስብለው ተወጥረው በታሰሩት ሁለቱ እጆቻቸው ያሉትን አስሩንም ጣቶቻቸውን በስስ ፌስታል በመጠምጠም በብር ፕላስቲክ ካሰሩ በኃላ በክብሪት ይለኩሷቸዋል!!! ከዚያም የጣቶቻቸው የጥፋር ጫፍና ስጋቸው በከፊል ሲበላ አረመኔው ባዶ ጭንቅላት የቅርብ አጋዚ የሚባሉት ቅልቦች ያጠፉላችዋል፡፡ የሚዘገንነው እኮ እስከዚህ ድረስ የፈለጉትን መረጃ አምነውበትም ይሁን ተጨንቀው/ተገደው ካልተናገሩ እንደገና ጣቶቻቸው ይለኮሱ እና ጥፍር እስኪበላ ይጠብቃሉ፡፡ በዚህም ጊዜ ግፍ የሚፈፀምበት ታሳሪ በሞት ውስጥ ሆኖ ራሱን ይስታል። አዕምሮ የሌላቸው የወያኔ ትግሬ ሀኪም ተብየዎችም እንዳትድን ግን አገግመው ለቀጣይ የሰቆቃ ግፍ እንዲፈፀምበት ዝግጁ ያደርጉታል፡፡

፨ 2) እንደፈለጉ አጠላልፈው እጅ እግራቸውን ካሠሩ በኃላ አይናቸው እያየ ጥፍሮቻቸውን በጉጠት በኃይል በመሳብ ይነቅላሉ፡፡ ታድያ እስኪ አስቡ በእውን የትግራይ ባለስልጣት ኢትዮጲያዊ ነቸውን? ባልገባን ድብቅና ሚስጥራዊ አጀንዳቸው ምክንያት ሀገረ ኤርትራ እንድትገነጠል ከዚያም በመካከላችን ልዮነት ፈጥረው ጦርነትም አውጀው ምስኪኑ የሀገራችን ዜጋ ከትግራይ ዘማቾች ውጭ እንዲያልቁ የሌላው ማህ/ብ ቁጥር በጥበብ እንዲወርድ ነገር ግን ምርጦች የትግራይ ዜጎች ቁጥርን በማሳደግ አሁን ለደረሱበት የኃይል እና የኢኮኖሚ ሚዛን ተጠቀሙብን፡፡ ይቅርታ በኢትዮ..እና በኤርትራ መካከል ስላለው ላወራ አይደለም፡፡ ግን በጣሊያን ወረራ ጊዜ እነ አብራሀም ደቦጭ፡ ሞገስ አስክዶም ሌሎችም ለኢትዮ ሀገራቸው እጅግ ተቆርቋሪ ከመሆናቸው የተነሳ አቆራርጠው ገብተው በእነ ግራዚያኒ ስብሰባ ቦምብ ወርውረው ገለውም አቁስለው በማምለጥ በመጨረሻም ወደ ሱዳን ጠረፍ ለማምለጥ ሲሞክሩ ተይዘው በስቅላት ተቀጡ፡፡ አሁን አስቡ ለኔ ትናንትም ዛሬ ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ ዜጋ ከትግራይ በላይ ነበሩ፡፡ ለዚህ እኮ ነው እውን ኢትዮጲያዊ ናቸውን ? የምላችሁ፡፡ ለስልጣንና ለሰፋፊ ቦታዎች ሲሉ ብቻ ባንዳ በመሆን አፄ ቴወድሮስን አፄ ዮሃንስ አስገደሉ፡፡ ታድያ አሁንስ በዘር ከፋፍለው እያፋጁ ከዚያም ግጭት ፈጣሪዎች አሸባሪዎች ግ.7ቶች ኦነጎች ወዘተ በማለት ወደ ማዕከላዊ በማጓጓዝ አጉረው አሰቃይተው ይገሉናል፡፡

፨፡ 3) ይህ ቅጣት ደግሞ ወያኔ እንደሚያደርገው ቢያንስ በወሬ ሰምታቹህ ታውቃላችሁ።-ይኸውላቹህ ብታምኑም ባታምኑም ማዕከላዊ ውስጥ ቆራጭ ፈላጭ እንጂ ስቃዩን የሚካፈሉ ወድ የሚባሉት የትግራይ ዜጎች በጭራሽ የሉም፡፡ግን መስዋዕትነት በመክፈል እስረኛ በመምሰል አብረው በመታሰር ባዶ ቤት እና ማሠቃያ ክፍል በማስገባት ገላውን ሳይሆን ግድግዳን በመምታት ሌሎች የሲቃ ድምፅ የሚመስለውን የውሸት እንዲሰሙ በማድረግ ሌሎችን ወያኔ የሚፈልጋቸውን ባግባቡ እንዲመርጁ የሚያደርጉ ወንድም ሴቶች አፋቸው ብቻ ኦሮሞ ወይም አማራ የሚመስሉ ነገር ግን የትግራይ ወሳኝ የሆኑ መስዋዕትነት የሚከፋሉ ዜጎቻቸው እንዳሉ 100% አረጋግጠናል ፡፡ እኛ የግፉ ገፈት ቀማሾች ኦሮማና አማራ ታድያ ወያኔ በዚህ መልኩ ዘራችንን ከሚያጠፉ በመጨረሻም ሁሉንም የኢትዮጵያ ሀብት ሙጥጥ አርገው ከወሰዱ በኃላ አንቀፅ 39 መገንጠል በጃቸው ስለሆነ ይሰናበቱናል። አዲስ የሠፈራ እና የእርሻ መሬትም በገፍ የጎንደርን ህዝብ በመግደልና በማፈናቀል ለጊዜውም ቢሆን የተረከቡት አላቸው፡፡ ይቅርታ ወደ 3ተኛው የአማራና የኦሮሞ የማዕከላዊ ቅጣት ልመለስ፡-

የወንድ ልጅ ጡር አምላክ ይፍረድባቸው እንጂ ወንዶችን ከላይ ሁለት እጆቻቸውን አንጠልጥለው በማሰር ከታች ሁለት እግሮቻቸውን ወደ ጎን እርቃናቸውን አድርጎ በማሰር ብልታቸውን ሳይሆን የዘር ፍሬ ማመንጫ እና ማጠራቀሚያ የሆነውን በአማርኛ ማህደረ ቆለጥ/ቆለጠ ቋር ብለን የምንጠራውን የመራብያ ክፍላቸውን የአምቦ ውሃ ጠርሙስ እንደሞላ በሲር ገመድ ላይ አስሮ በማንጠልጠል ከ1:30- 2:00 ሰዓት ቆይታ የታሰረው የአካል ክፍል መሬት እስኪነካ እና ደም እስኪንጠባጠብ በማሰቃየት እያስለፈለፉ መረጃ ይቀበላሉ። በመጨረሻም ከጥቅም ውጪ ሆነው እራሳቸውን ሲስቱ ተፈተው ይወርዳሉ። የሚገርመው ለዚህኛው ቅጣት የማገገሚያ ህክምና እንኳ አይደረግላቸውም፡፡

፨ 4) ሌላኛው ቅጣት እጅና እግራቸው ከታሰሩ በኃላ በተጠና የሙቀት መጠን ውሃ አፍልተው እንዳይሞቱ ግን የተወሰነ የአካል ክፍላቸው ላይ ሌሊት በማውጣት ለይተው በመድፋት ቆዳቸው እንዲላጥ እንዲነፍር ይደረጋሉ። ከዚያም የበለጠ እንዲያቃጥላቸው እጅግ የቀዘቀዘ የፊሪጅ ውሃ ይደፋባቸዋል፡፡ ምስኪኖቹም የድምፅ ሲቃቸውን ከፍ አድርገው እንዳያሰሙ ትንንሽ ኳሶች በአፋቸው ይጨመራል። አለበለዚያም ጥልቅ በረዷማ እና ጥቅጥቅ የጨለማ ክፍል ቤታቸው ይወረወራሉ፡፡

፨5) በከስክስ ጫማ ኩላሊታቸውን የመራቢያ አካላቸውን ወዘተ ለቀጣይ ሒወታቸው በሚጎዳ መልኩ ይቀጠቅጧቸዋል፡፡

፨ 6) ይህኛው ሁልጊዜ የምንሰማው የማውሰቃያ ቅጣት በኤሌትሪክ ከገላህ ጋር በማጣበቅ/ቶርች/ በማድረግ ከፍተኛ የኤሌትሪክ ሙሌት/ቻርጅ/ በመጨመር ሙሉ አካላቸውና አዕምሮአቸውን እንዲስቱ በማድረግ ማሰቃየት ነው፡፡ የምርመራ ጥያቄው ያው ሌሊቱን እና ቀኑን ሙሉ የተጎዱትን ባሉበት ክፍል ያልተጎዱትን ደግሞ በውስጥ የቢሮ ክፋላቸው በማመላለስ ያንገላቷቸዋል፡፡ ምግብና ውሃ ስቃይ ነው። በቀን አንድ ጊዜ ለመብላት አይደለም ለማየት የሚከብደውን የጠቆረ የቆየና እምክ እምክ የሚለውን ይወረወርላቸዋል፡፡ ከውጪ ጠያቂ የሚያመጣውን ከማጉላላት በኃላ እስረኛው የተገረፈ እና የተጎዳ ካልሆነ እንድትሰጥና በአይንም እንድትተያዮ ይፈቀዳል፡፡ ታድያ መልዕክት እንዳትለዋወጥ ፓሊስ በመኸከልህ ይደነቀራል። ጠያቂዉና እስረኛውም ሳያወሩ ይለያያሉ ማለት ነው፡፡

ይህ የፃፋኩት ቀናትን ወስጀ ከተቆርቋሪ የማዕከላዊ (…….) ጋር በተገኘ መረጃ ነው፡፡
©©©©©©©©©©©®®®®®®®®

ምስጋናው ለብርቱው ቋሚ አምደኛየ ይድረስ

ሙሉነህ ዮሃንስ