ዐማራው ከተደራጀ “ኢትዮጵያ ትፈርሳለች!”

Print Friendly, PDF & Email

(ቢል. ት.)

የዐማራው ሕዝብ የፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች ጥቃት ግንባር ቀደም ኢላማ ሆኖ በያለበት ሲጨፈጨፍ፣ ከትውልድ ቀብሌው ቤቱ ንብረቱ ተዘርፎ በጎሣ ታጣቂዎች በያለበት ሲፈናቀል በግልጽ እየታየና እየተሰማ ዝምታን የመረጡት አፈ ጮሌ ልሂቃን፣ ወያኔ ትግሬና ግብረ በላዎቹ ሁሉ ዘወትር የሚያላዝኑት “የዐማራው ሕዝብ መደራጀት ለኢትዮጵያ አንድነትና ሕልውና አደጋ ነው” እያሉ ማዘጥዘጥ ቋሚ ስራቸው እየሆነ ነው። ነገር ግን ምድር ላይ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ የሚያረጋግጠው ኢትዮጵያ ትባል የነበረው አገር ከ1983 ዓ.ም. ሰኔ ወር ጀምሮ ልክ ወራሪው ፋሽስት ጣሊያን አዘጋጅቶት በነበረው የጎሣ ሽንሸና ዕቅድ መሠረት በባንቱስታን አፓርታይድ የጎሣ ክልል ተከፋፍላ መበታተኗን ነው።

ከጠቅላላው ሕዝብ እስከ 45 በመቶ እጅ በሚሆነው የዐማራው ሕዝብ ኪሣራ እነ ኦነግ፣ ወያኔ ትግሬና ሻ ዕብያ ከልዩ ልዩ አናሳ ተለጣፊዎቻቸው ጋር በመሆን ዐማራውን ባቻ ለይተው ከፖለቲካና ኢኮኖሚያዊው መድረግ አግልለውታል። ከማግለላቸውና በሁለተኛ ደረጃ ከመፈረጃቸውም ሌላ በግልጽና በስውር የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ዘመቻ ይፈጽሙበታል።

ዐማራው ሕዝብ በብዛት በሚኖርባቸው ከተሞችና የገጠር መንደሮች ……. ( Read more )