ዐማራን ሃብትህን ጠብቅ በሉልኝ !!

Print Friendly, PDF & Email

(ራስ ሃመልማል)

በአማራ ክልል በወሎ ውስጥ የሚመረተው የኦፓል ምርት

ያለፈው ሳምንት አማራ ሙልጭ ያለ ድሃ ነው ጉልበቱን ይዞ ሃብት ያለበት ክልል እየዞረ ይሸቅል ያለው የህወሃት ተላላኪው ቅራቅንቦ ሃይለማርያም ደሳለኝ ነበር። ለነገሩስ የአማራን ስነልቦና የሰበረ መስሎት እንጅ አማራ በጉልበቱ ሰርቶ የሚኖርባት ሳይሆን በሄደበት የምትፋጅ ረመጥ የሆነችበትን ኢትዮጵያ ከሰሩ ሰንብተው የለ። አዎ ! እኛም ይህን ጠንቅቀን እናውቃለን። እናንተ እስካላችሁ ያችን ምድር ለአማራ የምታቃጥል እሳት የትቆረጥም በረዶ ለማድረግ ምላችሁ እንደተገዘታችሁ በሚገባ ገብቶናል።

እኛም እንደምናሸንፍ በሚገባ እናውቃለን። እናንተማ በተግባራችሁ ተስፋ ቆርጠን የተነሳን ቀን በአንድ ሌሊት መቃብር እንደምትወርዱ ስለምታውቁ ዙሪያ ገባውን ያለውን ወዳጅ ጠላት ለማድረግ፣ ወንድምን ከወንድሙ ለማናከስ ሌት ቀን እየለፋችሁ ነው። እኛም እንላለን ወንድምን ጠላት ለማድረግ ከሚደረገው ጥረት ውጤታማነት ወንድምነትን ለማስመለስ የሚደረግ ጥረት ውጤት ፈጣን መልስ አለው። አማራ ወዳጆቹን ማስመለስ የመጀመሪያው ስራው ነው። አማራ በሃሰት የጠለሸውን ስሙን ጥላሸት መግፈፍ ከሁለት አመት ያልዘለለ ጥረት የሚጠይቀው ስራ ነው። እናም እናሸንፋለን። ልበ ሙሉው አማራ ጠላቱን ድባቅ ይመታል።

ወደ ነጥቤ ልመለስና የአማራውን ስነልቦና ስበር ተብሎ የተላከው ትግሬው ሃይለማሪያም ደሳለኝ ፣(በተግባር፣ ለነገሩ በዘሩም ይሆናል ምክንያቱም ወያኔወች ዘር እየቆጠሩ እንደሚሾሙ ያደባባይ ሃቅ ነው )፣ አማራው ምንም አይነት የተፈጥሮ ሃብት የለውም በማለት ሁሉንም ብሄሮች ጠርተው አማራውን በመዝለል ሰፌድ ይዛችሁ ዙሩ ብለውናል። ለመሆኑ ምን አይነት የድንቁርና ደረጃ ላይ ብትሆኑ ነው እናንተ የምትሉትን የሚሰማ እና እናንተ እንዳላችሁት የሚፈስ ህዝብ አድርጋችሁ የምትገምቱት? አማራ እኮ እናንተን መስማት ካቆመ እና የራሱን መንገድ መስራት ከጀመረ ሰነበተ።

አማራ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ይገባኛል የሚለው ያራሱን ሃብት ያለው ህዝብ ነው። ያን ሃብትም እንዴት መጠቀም እንዳለበት እና መቼ መጠቀም እንዳለበት ግጥም አድርጎ ያውቃል። የአማራን ሃብት ደብቃችሁ ምንም እንዴሌለው ብታወሩ የሚሰማችሁ የለም። መስሚያው ጥጥ ነው። አማራ ያለውን ማእድን ያውቃል ። እናንተ ወርቁን፣ የከበረ ድንጋዩን ወይም ኦፓሉን፣ ጋዙን ፣ እጣኑን ፣ የ ቱሪዝም ሃብቱን ፣ ውሃ ሃብቱን ፣ የእርሻ ውጤቶች ምርቱን ፣ የቆዳ ምርቱን፣ ታንታለሙን ፣ ፖታሹን ፣ ሰሊጥ እና ሌሎቹን ሃብቶች ደብቃችሁ አማራን ሰፌድ ያዥ ማድረጋችሁ በናንተ ባዶ ፕሮፓጋንዳ የሚታለል አንድም ሰው እንደሌለ ማወቅ አለመቻላችሁ ነው። ሌላው ይቅርና አፈሩ ሲጨመቅ ነዳጅ እንደሚወጣው እንኳን ተመራማሪ ተመራማሪ አቡሀይ ውብሸት በሰሜን ተራራ አፈሩን አፈስ አድርጎ ሰርቶ አሳይቶናል። የአማራን ህዝብ ስነልቦና እና ጥበብ አማራ እና ተግባሩ ብቻ ናቸው ምስክሮቹ።

ለመረጃ ይህል

1)ፖታሽ በአፋር አማሮች አገር ዳሎል እንደሚገኝ እየታወቀ በትግራይ ዳሎል እያሉ ለጥናት አድራጊወች እና መረጃ ፈላጊወች የሚናገሩት የሃሰት ጌቶቹ የትግሬ ባለግዜወች ናቸው (መረጃው በምስሎቹ ላይ ይገኛል ) ።

2) እጣን በተመለከተ አብዛኛው እጣን በአማራ እና በኦጋዴን እንደሚገኝ ቢታወቅም ከሃገር ሲወጣ የትግራይ እጣን የሚል ብራንድ ተለጥፎለት መሆኑን በአይኔ አይቻለሁ። በነገራችን ላይ እጣን እጂግ በጣም ውድ የሆነ ዘይት የሚሰራበት ሲሆን አንድ 250 ml ( ሚሊ ሊትር ) የእጣን ዘይት ከ 1000 ዶላር በላይ እንደሚያወጣ ጥናቶች ያመላክታሉ። ይህን ሃብት ደብቀው የሚጠቀሙበት በናዝሬት ስውር የሆኑ ስምንት የእጣን ማከማቻ መጋዘኖች በመክፈት ወያኔ ትግሬወች ናቸው።

3) በወሎ መካነሰላም እና መቅደላ ዘይት መሰል ነገር በምድር ገጽ ላይ እንደምንጭ ሲፈስ ይኖራል። ጂኦሎጂስቶች ይህን አጥንተው ዘይት እንደሆነ ለመንግስት ሲያሳዉቁ ወያኔ ቀድሜ ትግራይ ባስቆፍረው እዛ አገኘዋለሁ በማለት ትግራይ ላይ ለማስቆፈር ብዙ የአገር ሃብት አውድመው በባዶ ቀርተዋል። ለሽፋን የሰጡት ምክንያትም ምንጩ ትግራይ ነው የሚል ነበር።

4) በወሎ የሚገኘው የ ኦፓል ሃብት ያለ አግባብ በወያኔ ትግሬ ሌቦች እየተዘረፈ ነው። የወሎ ኦፓል በአለም እጂግ የተደነቀ እና የተወደደ በመሆኑ ለጣት የምትሆን መጠን ብቻ እስከ 45,000 ዶላር (በአሁኑ ምንዛሬ 1, 026, 967.50 ብር ) ትሸጣለች። ወያኔ ግን ኩንታል ኦፓል በ 1000 ብር ይገዛል ከገበሬወች። አማራ ይህን ማስቆም አለብህ።

( ከታች እንደምት መለከቱት በምስሎቹ ላይ ኦፓሎቻችን ከነዋጋቸው ይገኛሉ )

[Link: http://www.ethiopiaopals.com/ ]

ለማጠቃለል ያህል ከትግሬ ወያኔው ሃይለማርያም ንግግር ለማትረፍ የታሰበው ፕሮፓጋንዳ

ሀ) አማራው የተፈጥሮ ሃብት እያለው እንደሌለው ለማስመሰል እና ምንም አይነት የሃብት ተጠቃሚነት ጥያቄ እንዳይጠይቅ ለማድረግ

ለ) ሌሎች ብሄሮች ያንን አይነት አስተሳሰብ ስነልቦና እንዲያዳብሩ እና አማራውን በዚህ መልኩ እንዲ ያሸማቅቁ ማስተማር እና

ሐ) የአማራውን ስነልቦና ለመስበር ( አማራ ሲመቱት የሚጠብቅ ሚስማር መሆኑን አላወቁም ) ነው ።

የመጨረሻ መልእክቴ

አማራ በያለህበት ያለህን የተፈጥሮ ሃብት ባለቤትነት አስከብር ፣ የተፈጥሮ ሃብት አላቂ ነውና በርካሽ ለወያኔ መጠቀሚያ አታስረክብ ( ወይ አትሽጥ አልያም በውድ ሽጥ )፣ ያለህን የተፈጥሮ ሃብት አይነት፣ የሚገኝበትን ቦታ እና መጠን ለይተህ እወቅ።

አማራ ያሸንፋል!!

ድል ለመላው የአማራ ህዝብ!!

 

 

Source: www.ethiopiaopals.com