ዐማራ ተጠንቀቅ!

Print Friendly, PDF & Email

የዐማራ ሕዝብ ሆይ ጠላቶችህ ና ቅን ገዥው የትገራይ ወያኔ የትግል ሥልታቸውን በመቀየር አሁን ደገሞ ሊያጠቁህ እየሞከሩ ያሉት ፊት ለፊት በመገጠም ሳይሆን፤አንተ የምትናገረውን ቋንቋ እየተናገሩ፤አንተ የምትገልጸውን ብሶት እየገለጹ፤ ስለአንተ ተቆርቋሪ መስለው እንዳንተው ተላብሰውየደረሰብህን ችግርና መከራ ዋየታና ሰቆቃ እያቀነቀኑ ሰረጎ በመግባት እንድሆነ ልታጤን የገባሃል።

• የዐማራ መደራጀት ያስደነገጠው እና ያስበረገገው ፋሽሸቱ ወያኔን እና ተከታዮቹን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ፀረ ዐማራ ሐይሎችን ጭምር ነው።

• እኛ የዐንድነት ሐይል ነን ደገሞ ዐማራ ብሎ ድርጀት ይሉ የነበሩ ሁሉ ዛሬ በዐማራው ድርጀት ሥር ለመታቀፍ ሲሯሯጡ የታያል።ይህ ሁኔታ በበጎ ጎኑ ስናየው ቀና ቢመሰልም፤ በሌላው ጎኑ ደግሞ ዐማራው ለረዥም ዘመን እንዲጠፋ ሲያቀነቅኑ ከነበረው ከወያኔ ኢሀደግ ጋር እጀና ጓንት ሆነው ሲሰሩ የነበሩ ሃይሎች ናቸው። የእንዚህ ሃይሎች የሚስጥር ተለዕኮ በሰረጎ ገብነት በዐማራው ህብረተ ሰብና በመታገያ ድርጅቶቹ በመስረግ እርስ በርስ ሊያንቁሩትና እንደሆነ ከአንዳንድ የመርጃ ባለሙያዎች ይነገራል ።

• የህዝብ ንብረት የዘረፉ ፤ያዘረፉ ያጭበረበሩ ፤ ከወያኔ ቱባ ቱባ ባለሰልጣኖች ጋር ሲነገዱ የነበሩ፡ተራ አጭብርብሪዎች እያጭበረበሩ የቀሟቸው ወገኖችበመካከላችን እያሉ ዛሬ ደግሞ የጥፋት ተልዕኳቸውን በዐማራዊነትን በዐማራ ተቆርቋሪነት ስበብ እየሰረጉ በመካከልህ በመገባት ላይ ናቸው። እንዚህነ ዐይን ያወጡ ቀምኞችና ዘራፊዎችን ከወዲሁ የመረጃ ልውውጥ በማፋጠን ማንነታቸውንም በሚገኘው የመገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም መግለጽን ህዝባችንን ማንቃት ይገበሃል። ይህን ስታደረግም በየአካባቢው ላሉ ወገኖቹ የማስጠንቀቂያ ደወል በመሆኑ ችግሩ ሳይባባስ መቅጨት ትችላለህ።

• በየጊዜው የዐማራውን ህዝብ ስብሰባ በመጥራት፤ገነዘብ በማሰባሰብ፤ ለዐማራው አንድነት እንታገላለን በሚል በፌስ ቡክና በፓልቶክ መደረኮች ተጠራረተው በዐማራው ስም በመሰባሰብ የሕልውናህ ጠበቃየሆኑት ድርጀቶችህን ለማቃቅር አንዱን ድርጅት በማወድስ ሌላውን በማራክስ እያከናወኑ ይገኛሉ። ይህ አዝማሚያ እያደገ ከመጣ ውጤቱ አስከፊ በመሆኑ ግልጽ አቋም መውሰድን ይሻሀል።

• ድረጀቶችን ለማሰባሰብ፤ ልዩነቶችን ለማጥበብ በሚል በየጊዜው በተለያዮ እስቴቶች የሚደረጉ ስብሰባዎች እንዳሉ ታውቃለህ። የእነዚህ ስብሰባ መነሻና መዳረሻ ውጤቱን ሳታውቅ መሳተፉም ከላይ የዘረዘርናቸው ችግሮች የጥቃት ሠለባ ሊያደርግህ ስለሚችል በብርቱ መመርመር ይገባሃል።

• የተደበቀ ዐላማን ከበስተጀርባቸው አንግበው የዐንተን አንድነት እናጠናክር ከሚሉ ደላላዎች ጋር ከመሰባስቡ በቀጥታ ድርጅቶቹ እንድሰለጠነ ስው ተገናኝታችሁ ቢያንስ ቢያንስ በዐማራው ላይ እየደረስ ያለውን ጥቃት ብትመክቱ ሠርጎ ገቦችንና የጎደፈ ታሪካቸውን ይዘው ሊቀላቀሉህ የሚሞክሩትን ሁሉ ለማጥራትና በሕዝባችን ላይ ያጠላውን ደባ ልትቋቋም ትችላለህ።

በክሊቭላንድ ኦሃዮ የዐማራ ተወላጆች የጥናት ክበብ የቀረበ