ቆሼ ሰፈር ለደረሰው የንፁሃን ዜጎች እልቂት የወያኔው መንግስት ተጠያቂ ነው! – ዳግማዊ መዐሕድ

Print Friendly, PDF & Email

መጋቢት 5 2009 ዓ.ም.

ቆሼ ሰፈር ለደረሰው የንፁሃን ዜጎች እልቂት የወያኔው መንግስት ተጠያቂ ነው። በአዲስ አበባ ከተማ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ “ቆሼ ሰፈር” ተብሎ በሚጠራውና የከተማው ቆሻሻ መጣያ በሆነው ቦታ ከ100 በላይ የሆኑ ወገኖቻችን በዘረኛውና ፋሺስቱ የወያኔ መንግስት በተቀነባበረ የዘር ማጥፋት ወንጀል ዘዴ ቅዳሜ መጋቢት 4/ 2009 ዓ/ም ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በቆሻሻ ተራራ መናድ ከነነፍሳቸው ተቀብረዋል።

ቆሼ ሰፈር ላለፉት 50 ዓመታት የአዲስ አበባ ከተማ ቆሻሻ የሚጠራቀምበት አካባቢ ነው። ይህ ቦታ ለብዙ በሽታዎች መንስኤ የሚሆኑ አደገኛ የኬሚካል ውጤቶችም ጪምር በየቦታው ከሚሰበሰበው ቆሻሻ ጋር የሚገኙበት ፣ በመጥፎ ጠረኑ ምክንያት የሰው ልጅ ቤት ሰርቶና ትዳር መስርቶ ሊኖርበት ቀርቶ ለአንዴኳ በአካባቢው በኩል ለማለፍ የሚያስቸግርና፣ ለጤና ጠንቅ የሆነ ሰፈር ነው።

በዚህ ሰፈር ውስጥ ቤት ቀልሰውና ቤተሰብ መስርተው የሚኖሩት ሰዎች አብዛኞቹ የአማራ ብሔር ተዎላጆች ናቸው። እነዚህ ሰዎች መሃል አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የነበረ ቤታቸውን ተነጥቀው ከትግራይ ለመጣና መልሶ የማይከፍለው በሚሊዬን የሚቆጠር ብር ከኢትዮዽያ ብሔራዊ ባንክ በነጻ ለተሰጠው አዲስ “ኢንቨስተር” እንዲሁም ለዘረኛውና ፋሽስቱ የወያኔ ስርዓት አባላትና ደጋፊዎች የተሰጠባቸው፤ ለዘመናት ጥረው ግረው መስርተው ከኖሩበት ሰፈራቸው ተባረው ሌላ መጠጊያና መሄጃ ሲያጡ እዚህ ማንም የማይፈልገው የቆሻሻ መጣያ ቦታ ከውሻና አሞራ ጋር እንዲኖሩ የተፈረደባቸውና ምርጫም ሲያጡ በህጋዊ መንገድ ካርታ አውተው ቤት ሰርተው የሚኖሩ የተገፉ ሰዎች ናቸው።

የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚያስረዱትና አንድ በደረሰው አደጋ ቤተሰባቸውን ያጡ እናት መጋቢት 3, 2009 ለተላለፈው የ አሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት በሰጡት ቃለመጠይቅ እንዳረጋገጡት የዚህ ከ100 በላይ ለሆኑ የሰው ለጆች እልቂት መንስኤ ከሆነው የቆሻሻ ተራራ መናድ ከሶስት ቀን ቀደም ብሎ ባልተለመደ ሁኔታ ብዛት ያላቸው የመከላከያ ሰራዊትና የፌድራል ፖሊስ በተደረመሰው ተራራ አካባቢ መታየታቸው፣ ሰውም ወደተራራው እንዳይሄድ መከልከል መጀመራቸው ለሰፈሩ ሰዎች እንግዳ እንደሆነባቸው፣ ከአደጋው መከሰት በፊት ትልቅ የፍንዳታ ድምጽ መስማታቸው፣ ይህንን የሰሙና የተመለከቱ በተናደው የቆሻሻ ክምር ከነነፍሳችው የተቀበሩ ሰዎችን ለማትረፍ ሲጥር በአካባቢው በነበረ የፌድራል ፖሊሶች መከልከላቸውን በሃዘንና ቁጭት ይናገራሉ። …… (Read more)