የአማራ ድምጽ ራዴዮ የመጋቢት 2 2009 ዓ.ም ወይም የማርች 11 2017 ፕሮግራሞች

Print Friendly, PDF & Email

በዛሬው ዜና የተካተቱት
∘ በሰሜን ጎንደር በወገራ ወራዳ ችፋር በገና በሚባለው የገጠር ከተማ ግንቦት 7 “እስረኞችን አስለቀቅን” የሚለው ዜና ሐሰት እንደሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጹ።

∘ በሰሜን ጎንደር ዞን ጭልቅጋ ወራዳ ነጋዴ ባህር እየተባለ በሚባለው አካባቢ ከሱዳን ነዳጅ ጭኖ በሚመጣው ቦቴ መኪና ላይ የአማራ ማንነት ተጋድሎ አባላትና የከተማ ፋኖዎች ጥቃት ማድስረሳቸው ታውቀ።

∘ በጅማ ዩኒቨርስቲ መምህራን ኮሌጅ የ2ኛ ዓመት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪ የነበረው ወጣት አንገቱ ላይ አስሮት በነበረው መስቀል ምክንያት ከመምህሩ ጋር ተጋጭቶ የትምህርት ውጤቱ በመበላሸቱ እራሡን አጠፋ።

∘ በአሜሪካ ኮንግረስ የአፍሪካ ዴስክ ንዑስ ኮሚቴ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ በተዘጋጀው ቅሬታ የመስማት ፕሮግራም ላይ አቶ ቴወድሮስ ትርፌ የትግሬ ዘረኞች መንግስት በዐማራ ህዝብ ላይ ያደርሰውን ግፍ በዝርዝር አሰምተዋል።

∘ እሁድ መጋቢት 3 ቀን 2009 ዓ.ም በጎንደር ከተማ በቡና በፋሲል ከተማ የእግር ኳስ ቡድኖች መካከል የሚደረገውን የእግር ኳስ ግጥሚያ የጀግናውና የአረበኛ ጎቤ መልኬ መታሰቢያ ጨዋታ ለማድረግ  መወሰኑ ተሰማ።

ልዩ ፕሮግራሞች

∘ ብአዴን የወያኔ የትሮይ ፈረስ በሚል ርዕስ በቬሮኒካ መላኩ የተዘጋጀ አንድ ድንቅ ፅሁፍ እንዲሁም

∘ ከዐማራ አክቲቪቶች ከዶ/ር አቤል ጆሴፍና አቶ አቻምየለህ ታምሩ ጋር የተደረገ ውይይት ይቀርባሉ። ሁሉንም ዝግጅቶች የሬዲዮ ፕሮግራሙን በማዳመጥ ይከታተሉ።

ዐማራ ከጥፋት የሚድነው በራሱ በዐማራ ልጆች ብቻ ነው!
እናመሰግናለን።