ጀግና ብርሌ ነው! አዎ! ጀግና ብርሌ ነው! – ሞረሽ ወገኔ

Print Friendly, PDF & Email


ጀግና ብርሌ ነው! አዎ!  ጀግና ብርሌ ነው!

አርበኛ ጎቤ መልኬ

ጀግና ሞት እልፍ አላፍ ጀግኖችን ይወልዳል።

ፈሪ ተራራ ነው ዘወትር ይኖራል፣
ጀግና ብርሌ ነው ተሎ ይሰበራል።

የሚለው የአባቶቻችን የሃቅ መገለጫ ሽለላ ዛሬ እውን ሆነ።

ለትግሬ ወያኔ የእግር እሳት በመሆን ባለፈው አንድ አመት ውስጥ የዐማራውን የህልውና የማንነት ጥያቄ አንስው በግንባር ቅደምትነት ከተሰለፉት የዐማራ ሕዝብ ጀግኖች አንዱ የሆነው አርበኛ ጎቤ መልኬ የካቲት 20 ቀን 2009 ዓ.ም በገንዘብ በተግዛና ወገን መስሎት አብሮ በተሰለፈ ከሃዲ ባንዳ ከተኛበት ገድሎት መሰወሩን የሰማነው በታላቅ ቁጭትና እልህ ነው።

አርበኛ ጎቤ ሃብት ንብረቱን፣ ትዳር ልጆቹን ጠብ እርግፍ አድርጎ ለዐማራው ህልውናና ማንነት ሁነኛና ዘላቂ መልስ ለማስገኘት ድር ቤቴ በማለት በወያኔ አገዛብ ብርቱ ክንዱን፣ ቆራጥ አቋሙን፣ ጀግነነቱና ለዓላማው ፅናቱን በተግባር ያሳየ የዐማራው ሕዝብ አለኝታ አርበኛ ነበር።

አርበኛ ጎቤ ለዐማራው ሕዝብ ህልውና መረጋገጥ ደኑን፣ አጥንቱን፣ ገነዘብህን ከመክፈሉ በላይ ዛሬ ደግሞ ምትክ የለሽ ህይወቱን ሰውቷል።

አርበኛ ጎቤ መልኬ ለመጭው ትውልድ አርያነት በሚሆን መልኩ ለነጻነት ህይወቱን ሰጥቶ በማለፉ በዐማራው መጭና ወጣት ትውልድ ውስጥ ዐማራና የዐማራ ተጋድሎ ታሪክ የሚኖረው ታሪክ እጅግ ታላቅና ከሁሉም የከበረ ይሆናል።

አርበኛ ጎቤ መልኬ ሃብትና ንብረት ያልቸገረው፣ የሞላለት ባለጻጋ ነበር። እርቦት ወይም ጠምቶት፣ ወይም ታርዞ አልነበረም ድር ቤቴ ያለው። የአርበኛ ጎቤ ርሃብ፣ ጥማትና እርዛት የዐማራ ማንነትና ህልውና አደጋ ውስጥ መግባት፣ ዐማራው በዘረኛው የትግሬ ወያኔ መገደል፣ መታሰር፣ መንገላታትማ ሰርቶ የመኖር ዋስትና ማጣት ነበር።

ይህን ርሃብና ጥማቱን ለመወጣትም በወያኔ አገዛዝ ላይ ክንዱን በማንሳት፣ ወያኔን የራሱን ህገመንግስት አግዶና ሽሮ አስቸኳይ የወታደራዊ አገዛዝ አዋጅ እንዲያውክ ካስገደዱት ቆፍጣና አርበኞች መካከል አርበኛ ጎቤ መልኬ አንዱ ነበር።

የአርበኛ ጎቤ መልኬ እነደ ይሁዳ በገንዘብ በተገዛ ከሀዲ በዚህ መልክ መስዋት መሆን የዐማራውን የህልውና ትግል በመቶ ሺህ እጥፍ የሚያሳድገው እንጅ የሚገታው አለማሆኑን በታሪክ የተረጋገጠ ሀቅ ነው። የአርበኛ ጎቤ መሰዋት በቋፍ ላይ ያለውን የዐማራ ወጣት ወደ ትግል ጎራው የሚጠራው ደወል ሆነ እንጅ አንገድ ማስደፊያ ፈጽሞ ሊሆን አይችልም።

በመሆኑም የዐማራው ወጣት የአርበኛችንን ፈለግ በመከተል ለዐማራው ተጋድሎ የማይከፍለው የመስዋትነት አይነት አይኖርም። እድሜ ልክን በባርነት ቀንበር ስር ከመኖር በነፃነት አንድ ቀን መኖር የተሻለ ምርጫ ነውና ወጣቱ የዐማራ ልጅ የጀግኖች አባቶቹን ፈለግ በመከተል እንደ መዥገር ተጣብቆ በዐማራ ህልውና ላይ አደጋ የጋረጠውን የወያኔ ዘረኛ አገዛዝ አሽቀንጥሮ ለመጣል በተሰውት አርበኞች ስም ቃሉን እንደጋና ያድሳል።

ጀግና ረጅምና አስደናቂ ታሪክ እንጅ ረጅም እድሜ የለው። የአርበኛ ጎቤ ህይወትም ይኸው በመሆኑ በጭር አድሜው አስደናቂና አንጸባራቂ ታሪክ ሰርቶ አልፏ። ታሪኩ የእኛ የቀሪዎቹ መኩሪያና መመኪያ ብቻ ሳይሆን የእንቅስቃሲያችን መመሪያም በመሆኑ ገዳዮቹን እና አስገዳዮቹን ከኢትዮጵያና ከዐማራው ጫንቃ መንጭቆ በመጣል የየአርበኛ ጎቤን ዓላማና ራዕይ እውን ለማድረግ ከምንግዘውም በላቀ ቁርጠኝነት እየተደረገ ያለውን የነጻነት ትግሉን  ልንቀላቀል ይገባል።

ድል ያለመስዋትነት አይታሰብምና የጎቤ መሰዋት ወደ ድላችን መቃረቢያ እየመራን መሆኑን ተመዝግበን ለትግሉ አስፈላጊውን ድጋፍ እንድናደርግ በመስዋቱ አርበኛ ጎቤ ስም ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ሕዝብ ድርጅት ጥሪውን ያቀርባል።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
የአርበኛ ጎቤ ሞት የዐማራው የህልውና ትግል ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግረዋል!