ወያኔ የቅማንትን ጉዳይ “በሪፈረንደም” መፍትሔ እሰጣለለሁ በማለት ካድሬዎቹን አሰልጠኗል

Print Friendly, PDF & Email

(ሙሉቀን ተስፋው)

• የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ የሚታሠሩ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል፡፡

በሰሜን ጎንደር ዞን በጎንደር ዙሪያ፣ በላይ አርማጭሆና አካባቢው ባሉ ወረዳዎች ከቅማንት የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ሪፈረንደም አካሒዳለሁ የሚለው የወያኔ አገዛዝ ለዚህ ይረዱኛል ያላቸውን ካቢኔዎቹን አሰልጥኖ በዚህ ሳምንት ጨርሷል፡፡ ከዚህ ቀደም ለቅማንት ልዩ ወረዳ ከተካለሉት ቀበሌዎች ውጭ በሆኑ አካባቢዎች ሪፈረንደም እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን የእርስ በእርስ ግጭት ለመፍጠር የሚደረግ እንቅስቃሴም አለ ተብሏል፡፡ የወልቃይት ጠገዴን የዐማራ ማንነጥ ጥያቄ የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየስ አሁን ሆን ተብሎ የሚጀመረው ሪፈረንደም ወደ ግጭት ሕዝቡ አስቀድሞ ይህን በመገንዘብ አንድነቱን ማሳየት እንዳለበትም መረጃውን ካቀበሉን አካለት አስተያየት ተሰጥቷል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ መፍትሔ ይሰጠዋል የተባለው የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ተወላጆችን ትግራይ ክልል ጥያቄ አቅርቡ እያሉ እየላኩ በማሳሰር ጥያቄውን ለማጓተት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ በጠገዴ ወረዳ አካባቢ ያለው የድንበር እና አጠቃላይ የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት ጥያቄ በሚል በሁለት ተከፍሎ ይፈታል በሚል በነሐሴ ወር 2008 ዓ.ም. በነበረው የኢሕአዴግ ጉባኤ ተቀምጦ ነበር፡፡ በጊዜው የድንበር ጉዳዩ በ15 ቀን እንደሚያልቅ ነበር ለሕዝብ ቃል የተገባው፡፡ በ15 ቀን ያልቃል የተባለው ጉዳይ ግን ከሰባት ወራት በኋላም ዜጎች እየተገደሉና እየታሰሩበት ነው፡፡ የሚከተሉት የወልቃይት ተወላጆች በእስር ከሚገኙት በጣም ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

በወልቃይት የታሰሩ የወልቃይት-ጠገዴ አማራ ማንነት አቅራቢዎችና ደጋፊዎች ስም ዝርዝር
ተ/ቁ ስም ፆታ ስራ የሚኖርበት ቦታ የታሰረበት ቦታ
1. ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ወንድ የግል ስራ ጎንደር ጎንደር አንገረብ
2. አታላይ ዛፌ ወንድ የግል ስራ ጎንደር አ/አ ማእከላዊ
3. ጌታቸው አደም ወንድ በጥሮታ የተሰናበቱ ጎንደር አ/አ ማእከላዊ
4. ነጋ ባንቲሁን ወንድ ባለ ሃብት ማይ ካድራ አ/አ ማእከላዊ
5. መብራቱ ጌታሁን ወንድ ገበሬ ባእከር አ/አ ማእከላዊ
6. አለነ ሻማ ወንድ ገበሬ ጎንደር አ/አ ማእከላዊ
7. አዲሱ አበበ ወንድ ገበሬ አዲስ አበባ አ/አ ማእከላዊ
8. ተሻገር ወ/ሚካኤል ወንድ የግል ስራ ጎንደር አ/አ ማእከላዊ
9. ዘውዱ ነጋ ወንድ የዩኒቨርስቲ መምህር ጎንደር ብርሸለቆ
10. ወረታው አዛናው ወንድ ባለ ሃብት ጎንደር ብርሸለቆ
11. ገ/መስቀል ማማይ ወንድ ባለ ሃብት ጎንደር ብርሸለቆ
12. ይልማ ፈርደ ወንድ ገበሬ ጎንደር ብርሸለቆ
13. አበበ ወንድ ባለ ሃብት ባእከር
14. ሞላ ሃይሉ ወንድ ገበሬ ዳንሻ ሁመራ
15. ሲሳይ ብርሃኔ ወንድ የግል ስራ ዳንሻ ሁመራ
16. አሊጋዝ አየለ ወንድ ነጋዴ ዳንሻ ሁመራ
17. አሻግሬ ወንድ ዳንሻ ሁመራ
18. ሰጠኝ አዛርበው ወንድ ዳንሻ
19. መኮነን ደስታ ወንድ ዳንሻ ሁመራ
20. ሰሎሞን ወንድ ዳንሻ ሁመራ
21. ኅይትኦም አማረ ወንድ ገበሬ ዳንሻ ሁመራ
22. መከተ መብራህቱ ወንድ ገበሬ ዳንሻ ሁመራ
23. ፀጋየ ረዳ ወንድ ገበሬ ጎንደር ዳንሻ
24. ገብሬ አባይ ወንድ ገበሬ ዳንሻ አይታወቅም
25. ጎይትኦም አማረ ወንድ ገበሬ ወልቃይት አይታወቅም
26. ባህታ ዋኘው ወንድ ነጋዴ ወልቃይት አይታወቅም
27. ጥጋቡ አማረ ወንድ ነጋዴ ድንሻ አይታወቅም
28. ወዲ ሰማሀኝ ወንድ ነጋዴ ዳንሻ አይታወቅም
29. ሰረበ ሙሉ ወንድ የግል ስራ ዳንሻ
30. ጉዐይ ታራቀኝ ወንድ ዳንሻ
31 አላቸው ወንድ ዳንሻ
32 አታላይ አለማው ወንድ ገበሬ
33 ክንድሽህ ሓጎስ ወንድ የመንግስት ሰራተኛ ጎንደር ጎንደር
34 ተስፋሁን ዋኘው ወንድ ገበሬ ጎንደር ጎንደር
35 ዘነበ ተስፋይ ወንድ የግልስ ስራ ዓ/ረመፅ ሁመራ
36 ሂባ አይችሉትም ሴት የቤት እመቤት ዓ/ረመፅ ሁመራ
37 ተስፋ ወንድ ወዛደር ዓ/ረመፅ ሁመራ
38 ርስቁ አለማው ወንድ ገበሬ ዓ/ረመፅ ሁመራ
39 ፈረደ ሸቱ ወንድ ነጋዴ ዓ/ረመፅ ዓ/ረመጽ
40 ማማይ አያና ወንድ ገበሬ ዓ/ረመፅ ዓ/ረመፅ
41 መላኩ ረዳ ወንድ ገበሬ ዓ/ረመፅ አይታወቅም
42 ሸሐይ ገ/ጨርቆስ ወንድ ገበሬ ዳንሻ ማይ ካድር
43 ባየው ካሳኝ ወንድ ገበሬና ሾፌር ማይ ካድር ሁመራ
44 ተገን መርሻ ወንድ ገበሬ ቃፍታ ሁመራ