ከፋሽስት ወያኔ ጋር ሆናችሁ የአማራ አርበኞችን ለምትጨፈጭፉ አማሮች

Print Friendly, PDF & Email

(አቻምየለህ ታምሩ)

ጀግኖቹ የአማራ አርበኞች እንደሻማ እየነደዱ በአማራ ላይ የተጫነውን ከልክ ያለፈ የፋሽስት ወያኔ ግፍና መከራ ፣ እልቂትና ጭፍጨፋ ለማስወገድ ዱር ቤቴ ካሉ ውለው አድረዋል። ሆኖም ግን አንዳንድ ወገኖቻችን ወያኔን እንደ አማራ መንግስት በመቁጠር የወያኔ መሳሪያ ሆናችሁ አማራነኝ ያለውን የራሳችሁን ወገን በመግደል የፋሽስት ወያኔ ስኬት የሆነውን የአማራ እልቂት አብራችሁ እየደገሳችሁ ትገኛላችሁ።

እንዴት ብሎ አማራ የሆነ አንድ ሰው አማራን አጥፍቶ በአማራ መቃብር ላይ የትግሬ ሪፑብሊክ ለመመስረት ጫካ ከገባውና ስልጣን ከያዘ በኋላ ከአምስት ሚሊዮን በላይ አማሮችን በግፍ ካጠፋው የትግሬ ነጻ አውጪ ቡድን ጋር ሆኖ ለአማራ ህልውና የህይወት መስዕዋትነት እየከፈሉ ያሉትን አማሮች የወያኔ መሳሪያ ሆኖ አብሮ ይጨፈጭፋል?

ምናልባት ሳይገባችሁ ቀርታችሁ ጨካኑኝ ወያኔን እንደ አማራ መንግስት በመቁጠር የአማራ ተጋድሎ አብረኞችን ከወያኔ ጋር ሆናችሁ እየጨፈጨፋችሁ ላላችሁ ይህ መልዕክት ለናንተ ነው።

የአማራ ተጋድሎ መላው አማራን በቅኝ ይዞ ግፍና መከራ ከሚያወርድብን ከሰው አውሬው የትግሬ ቅኝ ገዢ ወራሪ ጋር ብቻ ነው። የአማራ ልዩ ኃይል፣ መከላከያ፣ፖሊስ፣ ሚሊሻ ሆናችሁ የህዝብ አገልጋይ ከሆናችሁ ትግሉ እናንተንም ጭምር ነጻ የሚያወጣ ገጸ በረከት ነው። እናንተ እውነተኛ የህዝብ አገልጋይ ከሆናችሁ ዛሬ ወያኔ ባሪያ ሊያደርጋችሁ የሰጣችሁን የምስለኔነት ስልጣንና ጥቅም ከድል በኋላ የአማራ ህዝብ በክብር ይሰጣችኋል።

ይህንን አውቃችሁ እናንተንም ሆነ ህዝባችንን ለመጨረስ ሰራዊት ባሰማራብን ጨካኝ አገዛዝ ላይ ተጋዳዩን ህዝባችንን በመደገፍ ረገድ የምትችሉትን ሁሉ ማድረግ ሲገባችሁ ከወያኔ ጋር አብራችሁ ወገናችሁን መግደላችሁን ማቆምና ለማንነታቸው ከሚጋደሉ ወገናችሁ ጎን መሰለፍ አለባችሁ። ይህ ጥሪ ከተራ የቀበሌ አስተዳደር እስከ ሚኒስትር ደረጃ እንዲሁም ከሚሊሻ እስከ ከፍተኛ ወታደራዊ ስምሪት ላላችሁ እውነተኛ የአማራ ልጆች የተላከ የወገናችሁ ተማጽኖ ነው። ተጋድሎው ካሁን በኋላ ወደኋላ ቢመለስ አደጋው ለህዝባችን ብቻ ሳይሆን ለናንተም ጭምር ነው። እንደምታውቁት ወያኔ ገርፎ የማይጠግብ፤ ገድሎ የማይረካ ቂመኛ አረመኔ ነው። በ1997 ዓ.ም. የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ ቅንጅትን ትደግፋላችሁ በተባሉ አማሮች ላይ ወያኔ የወሰደውን የበቀል እርምጃ ሁላችሁም ታውቁታሏችሁ። የወያኔ ተፈጥሮ ከበቀልተኛነትና ከቂመኛነት ተለይቶ አይታይም።

ወያኔ በታሪኩ ሙሉ ያላወራረደው ቂምና በደል የለም። የወያኔ ስልትና ግብ አማራን ከምድረ ገጽ ማጥፋት ነው። ዛሬ ላይ አማራ እያካሄደው ያለው ተጋድሎ ወደኋላ ቢመለስ ወያኔ ህዝቡን ገድሎና አስሮ ሲጨርስ የቅጣት በትሩን የሚዞረው ወደ እናንተ አማሮች ነው። ዛሬ በሆዳችሁ አድራችሁ ወንድሞቻችሁን ስለገደላችሁ ወያኔ እናንተን የማያሳድድስችሁ እንዳይመስላችሁ። ይህ ስለመሆኑ የምትጠራጠሩ ብትኖሩ በቀድሞው «የኢህአዴግ» አባል በነበረው ሀብታሙ አያሌው ላይ ወያኔ የወረወረውን የበቀል ሰይፍና እያደረሰበት ያለውን ግፍና ሰቆቃ አስታውሱ። ከዚህ በተጨማሪ ዛሬ እናንተ በምትወስኑት ታሪካዊ ውሳኔ ነገ የናንተ ልጆች በታሪክና በትውልድ ፊት ወይ የጀግና ልጆች እየተባሉ ሲኮሩ ይኖራሉ አልያም የሎሌ፣ የወንጀለኛና የከሃዲ ልጆች እየተባሉ ሲሸማቀቁ ይኖራሉ!

ዛሬ የጠላቶቻችን ሎሌ ሆናችሁ ስለማንነታቸው እየተዋደቁ ያሉ የማንነት ወንድሞቻችሁን አማሮቹን ለመውጋት ሽርጉድ ለምትሉ የአማራ ባንዶችን ሳስብ ታላቁ አርበኛና ደራሲ ሀዲስ አለማየሁ በፋሽስት ጥሊያን ወረራ የኢትዮጵያ መንግስት በፈረሰ ጊዜ ከራስ እምሩ ኃይለ ስላሴ ጋር ሆነው ስለነጻነታቸው በሚጋደሉበት በዚያ ወቅት፣ ቆመውም፣ ተቀምጠውም፣ ተኝተውም፣ የሚያቃጥላቸው ያገር ፍቅር እየቀቀላቸው፤ እንፋሎታቸው እየገነፈለ፤ አይናቸው እንባ እየሞላ ስላስቸገራቸው በናታቸው ስም «የኢትዮጵያ ስቅሶ» ብለው ሀዘናቸውን ለወንድሞቻቸው ለማካፋል ሲሉ በንባቸው የጻፉት ግጥም ይታወሰኛል።

የወያኔ አገልጋይ የሆናችሁ የአማራ ልጆች ከአራጃችን ከወያኔ ኋላ እየተጎተታችሁ ወያኔ እንዲጠፋ የሞት አዋጅ አውጆ በዱልዱም እያረደው ያለውን አማራ ለማረድ አስካሪስ ሆናችሁ ከማየት በላይ ውርደትና ክሽፈት የለም። የአርበኛ የሀዲስ ግጥም ምንም እንኳ በዚያ ዘመን የተቋጠረ ቢሆንም ዛሬ እናንተ ሆዳሞች እያደረጋችሁት ያለውን አይነት ባንዳነት ለፈጸሙ ሆዳሞች [ከመጠነኛ ማሻሻያ ጋር] እንዲህ ብለው ነበር. . .

የአማራ እናት ልቅሶ!

ልጆቼን በማመን ባለመጠራጠር፣
የሚደፍረኝ የለም፣ ብዬ እመካ ነበር፤

ግን አሁን ተደፈርሁ ላልቅስ ፣ እርሜን ላውጣ፣
ጀግኖች ያለቁብኝ ፣ ስለሆንሁ አይቶ አጣ፤

አድምጡኝ ልጆቼ ፣ ላስጠንቅቃችሁ፣
ሳምናችሁ ብትከዱኝ ፣ ስመካበችሁ ፣
ዘላለም ውርደት ነው ፣ ደመወዛችሁ።

አየ ዋዬ ፣ ልጆቼ አየ ዋዬ ፣ ከዳችሁኝ ወዬ ።
ጀግና አልተተካም ወይ ፣ በቴዎድሮስ ስፍራ፣
ጎበዝ አልቆመም ወይ ፣ በነበላይ ስፍራ፣
ሰው የለበትም ወይ ፣ በምኒሊክ ስፍራ፣
ጠላቴ ሲወርረኝ ፣ ከቀኝ ከግራ፣
የሚሰማኝ ያጣሁ ፣ ብጣራ ብጣራ፤
ወይ እኔ እናንተየ የጀግኖች እናት፣

ሁሉም አለቁና ፣ ትተው ባዶ ቤት፣
ደርሶብኝ የማያውቅ ፣ አገኘኝ ጥቃት።
አየ ዋዬ ፣ ልጆቼ አየ ዋዬ፣ ከዳችሁኝ ወዬ ።

ገንዘብ እዬዘራ ሲመጣ ጠላት፣
ከማታለል ጋራ ፣ ከውሸት ስብከት፣
ባጠመደው ወጥመድ ፣ እንድትገቡለት፣
ተንኮሉን ሳታውቁ ፣ መስሎዋችሁ እውነት፣
በግ ካራጁ ሁዋላ ፣ እንደሚጎተት፣
ትጎተታላችሁ፣ እናንተም ለሞት።

አየ ዋዬ ፣ ልጆቼ አየ ዋዬ ፣ ከዳችሁኝ ወዬ።

ገንዘብ ተበድሮ አሁን ሲሰጣችሁ፣
ሁልጊዜም እንደዚያው ፣ የሚያደርግ መስሎዋችሁ፣
እንዳትታለሉ ፣ ሁዋላ ወየላችሁ፤

አሁን ገንዘብ ሰጥቶ ፣ እንዳትታገሉት ካረገ በሁዋላ፣
እንኩዋንስ የራሱ ፣ ገንዘቡን ሲበላ ፣
የናንትም ይሄዳል ይሰጣል ለሌላ።
አየ ዋዬ ፣ ልጆቼ አየ ዋዬ ፣ ከዳችሁኝ ወየ ።
አሁን ቢሰጣችሁ ገንዘብ ተበድሮ፣
በጁ ስትገቡለት ፣ እንዲህ ጥሮ ግሮ፣
ከያዘ በሁዋላ ክንዱን አጠንክሮ፣
ያጠፋውን ገንዘብ ፣ አንድ ባንድ ቆጥሮ፣
ይቀበላችሁዋል ፣ ወለዱን ጨምሮ።

አየ ዋየ ፣ ልጆቼ አየ ዋዬ፣ ከዳችሁኝ ወይ።
አይ ሞኞች ልጆቼ ፣ ተላላዎች ሆይ፣
ድርጅት ያቆመ በህዝባችሁ ላይ፣
እናንተን ለማክበር ፣ መሰላችሁ ወይ?

አሁን ስነግራችሁ ፣ ቢመስላችሁ ዋዛ፣
በሁዋላ መከራው ስቃዩ ሲበዛ ፣
ሞትን ብትፈልጉት፣ በወርቅ አይገዛ፤

አየ ዋዬ ፣ ልጆቼ አየ ዋዬ ፣ ከዳችሁኝ ወየ ።
ፀፀቱ ይውጣልኝ እስቲ ልንገራችሁ፣
ምናልባት ብትሰሙኝ፣ ትንሽ ቢቆጫችሁ፣
ጠመንጃው ጥይቱ ፣ እያለ በጃችሁ፣
ዱሩ ሸንተረሩ ሳለ በጃችሁ፣
አሁን ጊዜው ሳያልፍ ፣ካልተጋደላችሁ፤
ይህን ሁሉ በጁ ፣ ካረገ በሁዋላ ፣ አጥቂው ጠላታችሁ፣
ቢጭኑት አጋስስ ፣ ቢያርዱት ሰንጋ ናችሁ ።

አየ ዋዬ ፣ ልጆቼ አየ ዋዬ ፣ ከዳችሁኝ ወየ ።
ከዚህ ወድያ በቃኝ ፣ መክሬያችሁዋለሁ፣
ለኔም ለናንተም ሞት ፣ እርሜን እውጥቻለሁ፤

መክሬያችሁዋለሁ ፣ ጠላትን በህብረት እንድትቃወሙ፣
አሁን ይህን ጊዜ ፣ በጣም ሳትደክሙ፣
የናትነት ምክሬን ፣ ቃሌን ብትፈፅሙ፣
እግዜር ይባርካችሁ ፣ አብቡ ለምልሙ፣
ግን ይህን ጨኸቴን ፣ ልቅሶየን ባትሰሙ፣
በመልእልተ መስቀል ፣ የፈሰሰው ደሙ ፣
ርጉም ያድርጋችሁ ፣ እስከ ዘላለሙ ።

አየ ዋዬ ፣ ልጆቼ አየ ዋዬ ፣ ከዳችሁኝ ወዬ።
_____
ቢዘገይ አልመሸምና ልብ ያለው ልብ ይበል!