እንኳን ለ፪ሺ፱ኛው የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ – ሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት

Print Friendly, PDF & Email

ለተከበራችሁ ወድ ወገኖቻችን፤

የዚህን ዓመት የክርስቶስ ልደት በዓል ምክንያት በማድረግ ያለንን መልዕክት መላካችንን እያሳስብን በድጋሚ እንኳን ለ፪ሺ፱ኛው የጌታችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችህ እንላለን።
የዐማራ ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት
ማስታወቂያና ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

 ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት    ዐርብ  ታሕሳስ  ፳፰ ቀን ፪ሺህ ፱ ዓ.ም.   ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር  ፴፬

 ለመላው የክርስትና ኃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን በሙሉ!!

 እንሆ ፈጣሪያችን ልዑል እግዚአብሔር ፍጹም አምላክ ሲሆን፣ በፈጠረው ፍጡር የማይጨክን፣ ርኅሩኅ የባህርይ አምላክ መሆኑን እናምናለን። እኛን ከኃጢያት ዕዳ ሊያድነን ስለፈቀደ፣ ፍጹም ሰው ሆኖ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ። ስለዚህም  ዛሬ ታህሣሥ ፳፱ ቀን ፪ሺህ፱ ዓ.ም. የኢየሱስ ክርስቶስን ፪ሺ፱ኛ የልደት በዓል እናከብራለን። በዚህ አጋጣሚ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት መላው የክርስትና ኃይማኖት ተከታዮችን እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሣችሁ እንላለን።

ይህንን በዓል ስናከብር ማስታወስ ያለብን፣ በአሁኑ ዘመን ኢትዮጵያ አገራችን እና ሕዝባችን መስቀለኛ መንገድ ላይ መውደቃቸውን ነው። አገራችን ኢትዮጵያ ወደ መጨረሻው ጥፋት እና ውድቀት ፤ ሕዝባችንም ደግሞ ሊያባራ ወደማይችል የእርስ በእርስ እልቂት እንደከብት እየተገፉ እንደሆነ እናውቃለን። በእስካሁኑ የዐማራ ማንነት ጥያቄ ተጋድሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወንድሞቻችን ና እህቶቻችን በወያኔ-ትግሬ ጥይት ተደፍተዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ዐማራዎች ደግሞ ባልታወቀ ስፍራ እንደከበት ታጉረው በከፍተኛ እንግልትና የግፍ ስⷃይ ላይ ይገኛሉ። በጎንደር፤ በጎጃምና በጎረቤት አካባቢዎች የሚገኙት ወገኖቻችን ደግሞ የአባቶቻችን የጀግንነት ስሜት በመጠቀም ለዐማራው የማንነት ጥያቄ መልስ መገኘትና ለህልውናቸው ሲሉ የመጨረሻ ፍልሚያ በማድርግ ላይ ናቸው። ስለሆነም የዘንድሮውን የጌታችንን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓልን በዚህ አስፈሪ ድባብ ውስጥ ሆነን እንደምናከብረው ወገኖቻችን ትገነዘቡታላችሁ የሚል ጽኑ እምነት አለን። የትግሬ-ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ እግዚአብሔር በአምሣሉ የፈጠረውን እና ያከበረውን የሰው ዘር እንድ እንስሳ በመቁጠር ያለምንም ርኅራኄ ይጨፈጭፉታል። የአገራችንን ሉዓላዊ ግዛት በውጪ ኃይሎች በማስደፈር መሬታችንን ለሱዳኖች እና ለሌሎች ባዳን በማናለብኝነት አሳልፎ ስጥቷል።  እንዲሁም የዐባይ፤ የባሮ፣ ፣ የአዋሽ ፣ የዋቢ ሸበሌ ፣ የገናሌ ፣ የተከዜ፣ የኦሞና የመሳሰሉት ታላላቅ ወንዞች ባለቤት፤ የጣና ፣ የአባያ ፣ የሻላ እና ከ32 የማያንሱ ኃይቆች ምድር ዜጎች ሆነን ሣለ፤ በየጊዜው በረሃብ አለንጋ እንገረፋለን። በተለይም ባለፉት 25 ዓመታት በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ርሃብ እና ችጋር የኢትዮጵያውያን የመለያ ምልክት ለመሆን በቅተዋል። ከሁሉም በላይ “በእንቅርት ላይ. ጀሮ ደግፍ. “ እንዲሉ አዲስቷን እትዮጵያ ያለዐማራው ተሳትፎ እንገነባለን በሚል ደብቅ የዐማራ ጥላቻ ላይ በተጠነሰሰ ሴራ ና አድማ ያለምንም ስጋትና ጥርጣሬ ታላቁ የዐማራ ሕዝብን በአጠገብ የማያስደርስ ጥምር ተፈጥሮ የጎንዮሹ ትግል መጧጧፉ ክፉኛ ጠፍሮ ይዞናል። በዚህ ሁሉ እግዚአብሔር መንገድ አለው በሚል ጽኑ እምነት የዐማራውን ተጋድሎ የበለጠ አጠናክሮ ለማስመቀጠል የዐማራ ተውላጆች ቆርጠው ለመነሳታቸው ምስክር አያስፈልገውም።

እግዚአብሔር በመልኩ እና በአምሣሉ ሲፈጥረን ያጎናጸፈን ፀጋዎች፦ ሁላችን የእርሱ ልጆች እንደሆንን፤ እንድንዋደድ እና እንድንፈቃቀር፤ እርስ በእርሣችን እንድንተዛዘን እና እንድንከባበር ነበር። ሆኖም በሃያ ስድስቱ ዓመት የትግሬ-ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ዘመን ሁላችንም ኢትዮጵያዊ ሆነን ሳለ በጥላቻ እና በዘር የመከፋፈል ፖለቲካ መርዝ ተመርዘን አብረን በጋራ በአንድነት ተፈቃቅረን እንዳንኖር ተደርገናል። ለዚህ የጥላቻ መርዝ መሻሪያው መድኃኒት ምን ይሆን? መርዙ የሚሽረው ምንጩ ሲደርቅ ብቻ ነው። ምንጩም የትግሬ-ወያኔ  የፖለቲካ ቡድን ሲሆን ማስፈጸሚያውም የኢትዮጵያ ሕዝብ በጎሣ እና በነገድ እንደ ቅርጫ ሥጋ በመመደብ ተከፋፈሎ እንዲተላለቅ በዚህ ቡድን የፖለቲካ መግለጫ አንቀጽ 39 የተደነገገው ነው። ስለዚህ ይህ የእርስ በእርስ ፍጅት እና መተላለቅ የሚያቆመው የትግሬ-ወያኔ ሥርዓት ከሥር መሠርቱ ተነቅሎ ሲወገድ ብቻ መሆኑ አያጠራጥርም።

የትግሬ ወያኔ ቡድን ለ17 ዓመታት በሽፍትነት፣ ለ26 ዓመታት ደግሞ በገዥነት ተፈናጥጦ የኢትዮጵያን ሕዝብ የደም እንባ ሲያስነባ ቆይቷል። በተለይ በዐማራ ሕዝብ ላይ ባደረሰው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ክ5ሚሊዮን ያላነሱ አማሮች እንዳለቁ እና በዘር ማጽዳት ዘመቻው ደግሞ ከ10 ሚሊዮን የማያንሱ ዐማሮች መፈናቀላቸውን በየጊዜው የሚወጡ ዘገባዎች ያረጋግጣሉ።

ይህ የአገዛዝ ቡድን ገና ሥልጣን በጠመንጃ ኃይል እንደተቆጣጠረ፣ በበደኖ ፣ በአርባጉጉ እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች የዐማራ ተወላጆች «ከእኛ ዘር አየደላችሁም» ተብለው ዐይናቸው በጨርቅ እየተሸፈነ በጭካኔ ከመቶ ሜትር ጥልቀት በላይ በሚሆኑ ገደሎች ውስጥ ከእነሕይዎታቸው ተወርውረዋል። ከእነዚያ የግፍ ሰለባዎች መካከል ነፍሰ ጡር እናቶች ፣ ጨቅላ ሕፃናት ፣ አቅመ ደካሞች እና አረጋውያን ይገኙበታል። በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ዐማሮችን ቤታቸውን በላያቸው ላይ እየዘጉ በእሣት አጋይተዋቸዋል።

ግፉ እና አረመኔያዊ ጭፍጨፋው ያልደረሰበት የኢትዮጵያ ግዛት ክልል የለም።  ይሁን እንጅ በዐማራው ለይ የሚፈጸመው የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ዘመቻ በፍፁም በተለዬና በፖሊሲ ተቀርጾ ነው። ሰሞኑን ዐማሮች በሁለት አቅጣጫ፣ ማለትም፦ በአንድ ወገን በቀጥታ በትግሬ-ወያኔ ካድሬዎች ታጣቂዎች እንዲሁም በሌላ ወገን «የትግሬ-ወያኔን መሪ ዕቅድ እንቃወማለን» በሚሉ ኃይሎች፣ ዐማራ ወገኖቻችን ቤታቸው እና አንጡራ ንብረታቸው ተቃጥሎ እንዲፈናቀሉ ከመደረጉም በላይ ብዙዎችም ተገድለዋል። ይህ ታሪክ ይቅር የማይለው አረመኔያዊ ግፍ የሚፈጸመው፣ በኢትዮጵያኖች እጅ ኢትዮጵያውያን በሆኑ የዐማራ ተወላጆች ላይ ነው። በመሆኑም የቂም በቀል ስሜት እና የዘረኝነት ደመና የአገራችንን ሰማይ እና የሕዝባችንን ልብ በሸፈነበት ወቅት፣ ፊታችንን ወደ እግዚአብሔር በንጹህ ልብ ማዞር እንድሚገባን አያጠያይቅም።

ባለፉት 25 ዓመታት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የትግሬ-ወያኔ ያሣረፈው የማፈራረስ ዱላ ከአገር ቤት አልፎ በውጪ አገሮች በስደት ላይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን የኃይማኖት ነፃነት ሣይቀር በእጅጉ ጎድቶታል። ሲጀመር ወያኔ በፓትርያርክ ላይ ፓትርያርክ ሾመ። በዚያ ሣይገታ የቤተክርስቲያኒቱ ካህናት እና ምዕመናን ሊሸከሙት የሚከብድ የግፍ ጫና አወረደባቸው። አልፎ ተርፎም ውቅያኖሶችን ተሻግሮ በስደት ዓለም ያሉ ኢትዮጵያውያን ያቋቋሟቸውን አብያተክርስቲያናት የአመፅ እና የብጥብጥ አውድማ አደረጋቸው። በዘረጋው የካድሬ-ካህናት መዋቅር በመጠቀም፥ ምዕመናንን ከካህናት ፣ ካህናትን ከካህናት ፣ ምዕመናንንም ከሌሎች ምዕመናን ጋር እንዲበጣበጡ አድርጓል። ስለዚህ የቤተክርስቲያኒቱ ምዕመናን ለቤተክርስቲያናቸው ኅልውና ፣ አንድነት እና ሰላም መቀጠል ሲሉ ድምፃቸው እንዳይሰማ በኃይል ከታፈኑት እውነተኛ አባቶች ጎን ሊቆሙ ይገባል።

ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ በሳምራዊያን እና በአይሁዳዊያን መክካል የነበረውን የነገድ ልዩነት ግድግዳ እንዳፈረሰው ሁሉ ፣ በእኛ በኢትዮጵያውያንም መካከል በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ የተረጭብንን የዘረኝነት መርዝ ሽሮ፣ የመከፋፋሉንም ግድግዳ ያፈርስልን ዘንድ የዘወትር ፀሎታችን ይሁን። ስለሆነም እውነተኛ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ተረባርበን የትግሬ-ወያኔን የጥቁር አፓርታይድ የባርነት ሰንሰለት መበጣጠስ ይገባናል። ይህንን በማድረግ እግዚአብሔር የሰጠንን አንዲት ታላቅ ኢትዮጵያ ከጨርሶ ጥፋት እና መፍረስ አድነን ሕዝባችንንም ከታሪክ ውርደት እና ማቅ ነፃ ለማውጣት እንችላለን። በዚህ አጋጣሚ «ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች» የተባለው የተስፋ ቃል ይፈጸም ዘንድ፣ እኛ ኢትይጵያውያን እጆቻችንን ከልባችን ጋር ወደ ፈጣሪያችን ወደ እግዚአብሔር እንድንዘረጋ ሞረሽ ወገኔ የአደራ ጥሪዉን ያቀርባል።

ወስብሐተ እግዚአብሔር