“ኢትዮዽያዊነት የሰዉ ዘር ቀዳሚ የነፃነት ሕገ መንግሥት ነዉ”።

Print Friendly, PDF & Email

ኢትዮዽያዊዉ ጥቁር ሰዉ “ከኢትዮዽያ ኣልፎ ለኣፍሪቃና ለመላው አለምታሪክ ነው።ሐቅ ነው። በዚህ የሚያፍር ራሱ ሃፍረት ነው፤ መቃብር ። በዘር ማሰብ የደካማነት ሁሉ የ መጨረሻው ኑዛዜ ነው። አንድ ሰው አቅም ሲያጣ ሮጦ የሚወሸቀው በዘር ስብስብ ውስጥ ነው። መዳንም መሞትም በጅምላ አይደለም። በሰማይም በምድርም ለፍርድ የምንቀርበው በግል እንጂ በዘር ስብስብ አይደለም። “ኢትዮዽያዊዉ ጥቁር ሰዉ “ ታሪክና የነፃነት ዝክረ ገድል ኣፍሪቃና መላው የኣለም የሰዉ ዘር ይኮራበታል”። በታሪካችን ኣናፍርም ሰንደቅ አላማችን ነው፤ ኣረንጓዴ ቢጫ ቀይ። አገርን ኣንድ የማድረግ የታላቋ ኢትዮዽያ ትግል ኣፄ ቴዎድሮስ አሀዱ ኣሉት ኣፄ ዮሃንስ ቀጠሉት ኣፄ ምኒልክ ተረከቡት ትውልዱ ተቀባበለው እነ ዘርአይ ድረስ ኣስተጋቡት በኣራቱም ማዕዘናት የማይበገሩ ጥቁር የኢትዮዽያ ኣንበሶች ጀግኖች ተወለዱ :: ይህ እዉነት ነው !!! ኣለም ያረጋገጠዉእዉነት“ኢትዮዽያዊዉ ጥቁር ሰዉ ይህ ነዉ ሌሎችም ያዜሙለትና የምናዜምለት ይህነዉ ኣቦተውን ! ገናይዜምለታል “ኒልሶን ማንዴላ የልቤ ደስታ ብለው ያዜሙለት የታላቋ ኢትዮዽያ ጥቁሩ አንበሳ ኢትዮዽያዊነት “ በዩኒቨርስ ገና ይዜምለታል ዘርና ዘረኞች በድንበር የማይገድቡትና በልብ ውስጥ ያለ በደም ዉስጥ የሠረፀ የአእምሮ ልጓም መዝገብ ታላቋ ኢትዮዽያ ኢትዮዽያዊነት !!! የኢትዬጵያ ህዝብ እንደህዝብ መነሻ ትልቅ የሆነ ትልቅ ህዝብ ነው

ታላቋ ኢትዮጵያ እንደገና ትነሳለች ኢትዮጵያዊነት ዋና በር ነው!ኢትዮጵያ ወደብ አልባ የሆነችበት፤ አንድነት የጠፋበትና ለዘመናት አብረው በሰላምና በፍቅር በአንድነት የኖሩ ነገደ ኢትዮጵያውያን በጥርጣሬና በጥላቻ የሚተያዩበት ሁኔታ ጊዜውተስፋ አስቆራጭ ቢሆንም አንድነት ተቃርቧል እውን የሚሆንበት ጊዜው በጣም ረዥም አይሆንም ምክንያቱም ኢትዮጵያዊነት የደም ዕምነት እውነት መሬት ከነካች በኋላ ከዚህ በላይ ስለማይኖር ኢትዮጵያ እንደገና ትነሳለችና፡፡“ሩቅ አይሆንም” ለአገራችን ኢትዮጵያ አንድነት በጋራ ተደጋግፈን ኢፍትሃዊነትን ተረት ለማድረግ እንተባበር። ኢትዮጵያዊነት ዋና በር ነው።ዘለዓለማዊ ማንነትም ነው።ኢትዮጵያዊነትታሪካዊ ጉዞ የማያወላውል ጠንካራ አቋም “ኢትዮዽያዊነት የሰዉ ዘር ቀዳሚ የነፃነት ሕገ መንግሥት ነዉ”።

ይህ ዘመን ለኢትዬጵያና “ለኢትዮዽያዊዉ ጥቁር ሰዉ” የሃዘን ዘመን  ነው ::በእጅጉ የምገረምበት ነገር ቢኖር ጩኽቴ፤አገሪቱ በወያኔዎቹእጅ ወድቃ እየተበጠበጠች የኢትዮጵያ ምድር የየደም ዕንባ ቋት ሆና ከማንነታችን የወረደ በኢትዮጵያ በየቀኑ የጭካኔ ወሬ እንሰማለን ምንም አናደርግም። ይህ ምንም ያለማድረግ ውሳኔና ይህ በኅብረተሰቡ ኑሮ ውስጥ ያገባኛል የሚል ስሜት መጥፋት አቅም ያጣን ለግፍ፤ ለበደልና ለጥቃት እንድንገብር፤ ግፍን በደልንና ጥቃትን አየሰማንና እያየን ለኢትዮጵያ ነፃነት ምንም እንዳናደርግ የሚያደርገን ምንድን ነው? እግዜኦ

ዳገት ላይ ሰው ጠፋ፤ አቀበት ከበደ፤
ሁሉም በሸርተቴ ቁለቁለት ወረደ፤ ሰው ተዋረደ፤
ወደ ጨለማ ቤት ኢትዮጵያ ወረደ፤
ያጴጥሮሳዊነት ወዴት ተሰደደ ::
ኢትዮጵያበቆራጥልጆቿታፍራናተከብራትኖራለች !!!
ሰልፍየጀግናድልየእግዚአብሄርነው።

(ገብርኤል ብዙነህ)