ግንቦት 7 የሚባለው ድርጅት የመተዳደሪያ ህጉና የአማራ ብሄር አባላቱ መብቶች

Print Friendly, PDF & Email

እንደሚታወቀው ግንቦት 7 የተባለው ድርጅት ከመሰሩት አንስቶ ፀረ-አማራ የሆነ ድርጅት ነው። ለዚህም ማስረጃው ግንቦት 7 በውስጥ መተዳደሪያና ደንቡና የድርጅቱን የምክር ቤት አባላት እጩዎች ምርጫን በሚመለከት በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ ያስቀመጠው ጸረ አማራ የሆነ ህጉ ነው።

ግንቦት 7 እንደሚለው በግንቦት 7 የምክር ቤት አባላት ምርጫ ወቅት ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባ የግንቦት 7 የአባላት አይነት ይልና የሚከተለው ይላል።

“እድሚያቸው ከ18 እስከ 70 ዓመት ለሚደርሱ ከአማርኛ ሌላ በተጨማሪ በሀገራችን የሚነገሩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ አባላት” ለምክር ቤት አባላትነት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።” ይላል።

እንግዲህ በጎጃም፣ በጎንንደር፣ በወሎና በሸዋ የተወለድ የአማራ ብሄር ተወላጅ ከአማርኛ ቋንቋ ውጭ ሌላ ተጨማሪ ኦሮሞኛ፣ ጉራጌና፣ ትግርኛና ሌሎችንም ቋንቋዎች አይናገርም። በነዚህ አካባቢ የተወለደና ያደገ የአማራ ብሄር ተወላጅ በዚህ የግንቦት 7 የምክር ቤት አባላት ህግ መሰረት በግንቦት 7 ውሥጥ የምክር ቤት አባል ሆኖ የማገልገል እድሉ በህግ የተዘጋና ይግባኝ የለለው ጉዳይ ነው ማለተ ነው።

ግንቦት 7 እንደሚለው “ህብረ ብሄርዊ” ድርጅት ከሆነና ሰረ-አማራ የሆነ ድርጅት ካልሆነ እንደት እንደዚህ አይነት ዘረና የሆነና ቋንቋን መሰርት ያደረገ የአባላትን የምክር ቤት የመመረጥ መብት በህግ ዝግ በማድረግ ቋንቋን ምክንያት በማድረግ የአማራ ብሄር ተወላጆች የሆኑ የድርጅቱን አባት በምክር ቤት የመመረጥ መብት ይከለክላል?

ከዚህ ላይ ግን ማንኛውም የአማራ ብብሄር ተወላጅ የሆነ የግንቦት 7 አባልም ሆነ ከድርጅቱ ውጭ የሆነ የአማራ ብሄር ተወላጅ እራሱን የሚከተለው ጥያቄ ሊጠይቅ ይገባል። አማራ ከአማርኛ ቋንቋ ውጭ ሌላ ማለትም ኦሮምኛ፣ ትግርኛ፣ ጉራጌኛ፣ ሶማሌኛ እና ሌሎችንም ቋንቋዎች አለመናገሩ የአጋጣሚ ነገር ሆኖ ነው እንጅ አማርኛ ከሚናገሩ የጉራጌ፣ የኦሮሞ፣ የትግሬና ሌሎችም ብሄር ተወላጆች ያነስ አነስተኛ የአስተሳሰብ ችሎታ ( Low IQ ) ኖሮት አይመስለኝም በግንቦት 7 የምክር ቤት አባላት ተመርጦ እንዳያገለግል በድርጅቱ በህግ ተጽፎ አማራ በግንቦት 7 የሃላፊነት ቦታ እንዳይቀመጥ የተደረገበት ምክንያት።

በዚህ ዘረኛና ጸረ አማራ በሆነው የግንቦት 7 ህግ መሰረት በድርጅቱ ውስጥ በአባልነት የሚገኝ የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆኑ ሁሉ የተመደላቸው ክፍት የስራ ቦታ የግንቦት 7 እግረኛ ወታደር ወይም የግንቦት 7 ባለስልጣናት ጠባቂና ቦዲ ጋርድ መሆን ብቻ ነው ማለት ነው። ሌለው በግንቦት 7 ውስጥ ሆነው የሚገኙ የአማራ ብሄር ተወላጆች የተሰጣቸው ክፍት ቦታ ለድርጅቱ ገንዘብ ማዋጣት፣ የግንቦት 7 ስብሰባዎችና ዝግጅቶች በምኖሩነት ግዜ የስብሰባ አዳራሾችን ማጽዳት፣ ማሳመር፣ ወንብረ እና ጠረጴዛውችን ማዘጋጀት ነው ማለት ነው።
ግንቦት 7 ከላይ በተጠቀሰው የአማራ ብሄር ተወላጆችን ከድርጁት ስልጣን ሃላፊነት ከጨዋታ ውጭ ያደረገው የድርጅቱ የምክር ቤት አባላት ምርጫ ዝም ብሎ የተቀመጠ ሳይሆን በተግባርም እንደሚከተለው ይገለጻል።

የግንቦት 7 መሪዎች እነማን ናቸው?

1. ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ – ሊ/መንበር = ጉራጌ
2. አቶ አበበ ቦጋለ – ምክትል ሊ/መንበር = ኦሮሞ
3. አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ – ፀሃፊ (በወያኔ እስር ላይ ነው) = ኦሮሞ
4. አቶ ኤፍሬም ማዴቦ – የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ = ከምባታ
5. ዶ/ር ታደሰ ብሩ – የጥናትና ምርምር ሃላፊ = ጉራጌ
6. አቶ ቸኮል ጌታቸው = ጉራጌ
7. አቶ አንድነት ሃይሉ = ጉራጌ
8. አቶ አበራ አዳሙ = ጉራጌ
9. አቶ ሙሉነህ እዩኤል = ከምባታ
10. አቶ ነዓምን ዘለቀ = ኦሮሞ እና ኤርትራ

ከላይ እንደምታዩት ምንም እንኳን የግንቦት 7 ከ90% በላይ የሚሆኑት የግንቦት እግረኛና ጀሌ አባላቱ የአማራ ብሄር ተወላጆች ቢሆኑም በድርጅቱ የስልጣን ቦታ ግን አንድም የአማራ ብሄር ተወላጅ የለበት። በግንቦት 7 ውስጥ የሚገኙ የአማራ ብሄር ተወላጆች ወደ ግንቦት 7 የአመራር ቦታነት የማይሾሙት ለድርጅቱ ታማኝ ስላልሆኑ ይሆን?

“ሞኝ ባያፍር የሞኝ ዘመድ ያፍር” እንደሚባለው ሁሉ በግንቦት 7 ውስጥ የምንገኝ የአማራ ብሄር ተወላጆች በሙሉ ማፈሪያወች ነን ለነፍጠኛው፣ ለኩሩውና ለታላቁ የአማራ ህብረተሰብ።
እንግዲህ ከላይ እንደተመለከትነው ይህ ግንቦት 7 የሚባለ ድርጅት ከአፈጣጠሩ ጀምሮ ጸረ አማራ የሆነ ድርጅት በመሆኑ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ በማሳትና ከፍተኛ መሰዋትነትን በመክፈል የአማራ ህዝብ አሁን ለደረ የትግል ደረጃ እንደ ፋና ወጊ የሆኑትን የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ፎቶዎችና ምስሉን በየስብሰባውና በየገነዝብ መዝረፉ ዝግጅት የምታደርጉትን እንቅስቃሴ እንድታቆሙ እናሳስባልን።

የወያኔ ትግሉን ሲጀምረ ጸረ-አማራ የሆነ ማንፌስቶ ጽፎ የትግራይን ወጣት አስባስቦ ትግራይ ነጻ አውጥቶ ላለፊት 25 አመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በተለም ደግሞ በአማራው ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወምጀል እየፈጸመ መሆኑን ለአንተ ለማራው ህዝብ መንገር እንደመቀለድ ይቆጠራል። ታሪክ ራሱን ይደግማል እንደሚባለው ሁሉ ዘረኛው ወያኔ በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን በደል አሽቀንጥረን ስንጥል ከወያኔ ያላነሰና ጸረ አማራ የሆነው ግንቦት 7 ደግሞ ስልጣን ላይ ተቆናጦ የሰቆቃ ጊዜናን ህልውናህን እንዳያጨልመው ተጠንቀቅ።
የአማራ ብሄረ ተወላጅ የሆንሽ/ህ ወጣት ተደረጅና ታግለህ እራስህን ከዘረኖች ነጻ አውጣ።

የአማራ የነጻነት ትግል በራሱ በአማራ ቆራጥ ልጆች እና መሪዎች እንጅ በማንም አጭበርባሪና ሰላቶ ወደሚፈለገው ድል አይደርስም።

ድል ለሰፊውና ለጀግናው የአማራ ህዝብ!

ከነፍጠኛው የአማራ ልጅ ታደለ አለሙ
(ጸሃፉው በአሁኑ ሰዓት በግንቦት 7 አባልነት በድርጅቱ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ድርጅት የሚያወጣቸውን በርካታ ጸረ አማራ የሆኑ መረጃውችን እየተከታተለ ለህዝብ ይፋ ማድረጉን ይቀጥላል።)

ከግንቦት 7 የመተዳደሪያ ህግ የተወሰደው ክዚህ በታች ያንብቡ።